Get Mystery Box with random crypto!

ልጩህበት ክፍል~~~~ሶስት(3) አዘጋጅ፦ HEMA . . . ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለ | , 🖤 girls pride

ልጩህበት

ክፍል~~~~ሶስት(3)

አዘጋጅ፦ HEMA
.
.
.
ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ
ንዴቴን
ብሶቴን
ናፍቆቴን ባከስመው
እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!!
••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ•••

"አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ •••

እኔ ከባጃጅህ አልወረድኩ አንተ ግን ከገባሁ ጀምሮ ዝም ብለህ ትጮሀለህ ስማኝ የት እና መቼ እንደምትጮህ ካላወክ ዝም ብትል ይሻላል
ያለበለዚያ ሰሚ ሳይኖር ዝም ብለህ ብትጮህ የራስህ ጩኸት እራስህን ያደነቁርህ እንደሆን እንጂ ምንም አታመጣም !"
ብሎኝ ሲያበቃ ደሞ ወድያው ወደሷ ዞረና

"አንድ ግዜ ብቻ ልጩህ በናትሽ ?"
ሲላት ቀርታኝ የነበረችው እንጥፍጣፊ ትግስት ተሟጠጠች •••

አቦ ባባ ክብር ካልወደደልህ እንዴት እንደምትወርድ ላሳይሀ እንግዲህ ብዬ እጄን ለፀብ እያሰናዳሁ ወርጄ ስጠጋው

"ተው ተው ተው ቦክስ አታባክን ወጣቱ መጀመሪያውኑ እንደዚህ ወንድ ብትሆን ኖሮ አንተ ባጃጅ ውስጥ እስካሁን ማን ይቀመጥ ነበር ፈሪ ፈሪ ነገር ነህ !"
እያለ ከባጃጇ ሲወርድ ልጅቷ በሳቅ ፈነደቀች

ግራ ቀኝ እየተወዛወዘ ትንሽ ከባጃጇ ራቅ እንዳለ ዘወር አለና
"ሞት ይርሳኝ ቻው እሺ የኔ ልጅ ልጅ አልኩ እንዴ አንቺን እንኳን አላደርስም !
ቻው እሺ የኔ ልእልት አንቺን የመሰለች ልጅ ከዚህ አስቀያሚ ሹፌር ጋር በማየቴ ደንግጫለሁ !
ፍችው በናትሽ! " እላት።

"እሺ "አለችው በሳቋ መሀል

"ግን መች ትፈችዋለሽ በናትሽ! እ••• እ ••እ ንገሪኛ?" እያለ ሊመለስ ሲል እኔም እየሳኩ ወደሱ ስጠጋ ፊቱን አዙሮ ከቆምንበት በስተቀኝ መንገድ ዳር ወዳለችው የማትዘጋዋ መጠጥ ቤት አመራ።
ባጃጃን አስነስቼ ከዩንቨርስቲው በቅርብ ርቀት
ጨለማ ውስጥ አቆምኳትና ከመሪው ላይ ተነስቼ እሷ አጠገብ ተቀመጥኩ ። ፊቷ ተቀያየረ።
ካቆምንበት እንቀጥላ አልኳትና
ቅድም የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነበር ?

"በቃ ከፈለክ ልትሰድበኝም ከፈልክ ልታወርደኝም ትችላለህ ሌላ ምንድን ነው?" አለችኝ የጭንቀቷን
ወደ ዩንቨርስቲው ዞሬ ተመለከትኩ አጠገባችን ነው ግቢው ከሩቅ ይታያል ሳቄ መጣ አብራኝ ሳቀች።
ሀይ ስትደርሺ ነው እንዴ ልታወርደኝ ትችላለህ እምትይው? ስላት•••

ጭንቅላቷን ወደ ግራ ሰበቀችና በዝምታ እጇን እያፍተለተለች አይን አይኔን ታየኝ ጀመር
የሆነ ስሜት ተሰማኝ
ታውቂያለሽ ሁለት ወንድሞች አሉኝ ግን እህት የለኝም ቢሆንም እናት አለኝ የማይሆን ቢሆንም እናትም ባይኖረኝ እራሱ አንቺ ላይ የሚጨክን አንጀት የለኝም
ምንም አልደርግሽምም አልሰድብሽምም አላወርድሽምም እሺ መጀመሪያውኑ ብር እንደለለሽ ብትነግሪኝና በነፃ እንዳደርስሽ ብትጠይቂኝ ለስራ ብወጣም ከሰአቱ አንፃር ላውሬ ጥዬሽ አልሄድም ነበር ።

እያሰብኩ የነበረው ምናልባት መጥፎ ባህሪ ያለው የባጃጅ ሹፌር አጋጥሟት ቢሆን ኖሮስ እያልኩ ነው።

ግን ምን አጋጥሞሽ ነው ማለቴ
በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ?ስለራስሽም ብትነግሪኝ ደስ ይለኛል
"አጋጣሚው ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው ኬቱ ጋር ልጀምርልህ?
ከፈለግሽው።

"በናትህ አሁን መሽቷል ሞባይሌን ዶርም ጥዬው ወጥቼ ነው ከፈለክ ስልኬን ያዝና ነገ ወይ በሚመችህ ቀን ደውልልኝ አወራሀለሁ!"
እዚሁ ባጃጅ ውስጥ እናድራታለን እንጂ አልፋታሽም አልኳት ኮስተር ብዬ

" እያስገደድከኝ ነው ማለት ነው አለች እሷም በስሱ ከስተር ብላ
ስትስቅም ስትኮሳተርም የሚያምርባት ሴት እሷን አየሁ።
አሁን ከተለያየን ቡሀላ ልታገኝኝ ፍቃደኛ ሁኚ አትሁኝ እርግጠኛ ስላልሆንኩ አሁኑኑ እንድትነግሪኝ እየለመንኩሽ ነው! ከተጫንኩሽ ይቅር ብትነግሪኝ ግን የመጣሽበትን ሂሳብ እንደከፈልሽ እቆጥረዋለሁ አልኳትና አሁንም እኩል ሳቅን።

"ክትክትክትክት ኧረ ባክህ
እሺ ግን ባጭሩ ነው በደንብ እንድትረዳው ገባ ብዬ ብጀምርልህ ይረዝምብኛል?"

አቦ ንገሪኝኛ አታጓጊኝ!።

" እኔ
እኔ
እኔ ማለት እኔ ደሀ ከሚባል ቤተሰብ ነው የተወለድኩት ።

አባቴ አናፂ ነው እናቴ ደግሞ ሽንኩርት ቲማቲም ምናምን ነው ጉሊት ውስጥ የምትቸረችረው
ሁለቱም ፀሀይ ላይ ውለው ፊታቸው ጠቁሮ ከሚያገኙት ገቢ ውስጥ አብዛኛውን እኔን ከሰፈሬ እና ከትምህርት ቤት ጓደኛቼ እኩል ማድረግ ባይችሉ እንኳን ክፍተቱን በመጠኑ አጥብበው ብዙ ሳይሰማኝ እንዳድግ ለማድረግ አውለውታል።

ሳይለብሱ ያለብሱኛል
ለነሱ ርካሽ የተባለውን ጫማ እየተጫሙ ለኔ ውድና ሁለት ሶስት ቅያሪ ጫማ እንዲኖረኝ ለማድረግ ለነሱ የሚያስፈልጉዋቸውን ሁሉ ወደ ጎን ትተዋል !
ሳይደሰቱ እኔን ለማስደሰት የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል!
ቢኮራረፉ እኔ ፉት ይስቃሉ!
ቢያዝኑ እኔ ፊት ደስተኛ ለመምሰል ይሞክራሉ!

በአጠቃላይ ለራሳቸው ሳይኖሩ ለኔ ደክመው ለኔ ኖረው ያስተማሩኝን ቤተሰቦቼን ለማስደሰት የምችለው በትምህርቴ ስጎብዝ ነውና ምንም ነገር ሳያታልለኝ በርትቼ በመማር ወደ ዩንቨርስቲ መግቢያ የሚሆን ውጤት አምጥቼ ባስደሰትኳቸው ማግስት ነበር አባዬ እኔ ወደዚህ ለመምጣት የሚያስፈልገኝን ነገር ለሟሟላት ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ ያገኘውን ስራ በሙሉ እየሰራ ገንዘቡን እኔው ጋር ማጠራቀም የጀመረው •••"
አለችና ዝም አለች።

ምነው ቀጥይ እንጂ ስላት

"ስላባዬ ሳወራ ጨነቀኝ !
ትንሽ ዝምታ ተፈጠረ በመሀላችን።
ሲጨንቀኝ ደሞ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ?"
ምን ትዝ አለሽ ?
አንዴ ልጩህ እሚለው የቅድሙ ሰካራም ።

አንዴ ልጩህ እንዴ?"
ስትለኝ ሁለታችንም ባንድ ግዜ ከነበርንበት ሙድ ወጥተን ከባጃጇ ጣራ በላይ ሳቅን።

በናትሽ ቀጥይልኝ ? አልኳት ሳቄን ስጨርስ። ካሳቁ መልስ ደሞ ባንዴ ፍቷን ቅጭም አርጋ ቀጠለች•••
አባዬ ድካሙና እንቅልፉ ተደራርቦበት ነበር ።
ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ

ይቀጥላል......

━━━━━━━━ ✦
✎ ክፍል 4 በኋላ ይቀጥላል....





╔═══❖• •❖═══╗
Hema
╚═══❖• •❖═══╝

❥❥________⚘_______❥❥