Get Mystery Box with random crypto!

​ ሳገባህ ላፍቅርህ ክፍል አዘጋጅ➛ Hema የመጨረሻ ክፍ | , 🖤 girls pride

​ ሳገባህ ላፍቅርህ

ክፍል

አዘጋጅ➛ Hema

የመጨረሻ ክፍል
.
.
.
.
...ይሄው ጅማ ከገባሁ 4 ወራትን አሥቆጠርኩ...ከዚያ ከብቸኝነትና ከሥቃይ ኑሮ ተገላግዬ እናቴ ጉያ ተወሽቄ የማያልቅ የእናትነት ፍቅሯን እያገኘሁ..ጠረኗን እየማግሁ እገኛለሁ.....እናቴy ከምንም በላይ ኮርታብኛለች.. በቆራጥነቴና ለዚህ በመብቃቴ "አጃኢብ ነው..ከወለዱሥ እንደ ሠሚራ አይነት"የማይል የለም.....አከራዬ እንኳን ባጠገቤ ሲያልፍ በሀፍረት አንገቱን ደፍቶና ተሸማቆ ነው የሚሄደው..እኔ ግን ይቅር ብዬዋለሁ..በሱ ምክንያት አይደል ዛሬ ሙሉ ሰው ለመሆን የበቃሁት...

ደሥታ እኛ ቤት እንደጎርፍ አጥለቅልቆናል...
ዛሬ ቤታችን ከወትሮው በተለየ ድምቅምቅ ብሏል..ግቢያችን በሠፈር ሠው ተሞልቷል...አከባቢው ምግብ ምግብ ይሸታል.....ድንኳን ሁለት ቦታ ተጥሏል.......ጓደኞቼ እኔን ውብ ለማድረግ ሽር ጉድ እያሉ ነው...... ይሄ ሁሉ ለምን እንደሆነ መቼም ገብቷችሁዋል..የልጅነት ህልሜን ሁሲን የማገባበት ቀን ነው ......በሚያፈቅሩት ሠው መፈቀር፤ልብ ለልብ መገናኘት...የሚያፈቅሩትን ሠው የግል ማድረግ ከዚህ በላይ ምን አለም አለ እናንተዬ......ፌቪ አንደኛ ሚዜዬ ናት....ጉድ ጉድ ማለቱን ተያይዛዋለች...

ዲጄው ቤቱን በሰርግ ነሽዳ አድምቆታል..

ባረከላሁ ለኩማ ወባረከ አለይኩማ ወጀመአ በይነኩማ ፊል ከይር.......

ማሻአላህ ማሻአላህ ማሻአላህ ማሻአላህ......(3*)

ብቸኛ መሆንን በትግእሥት አልፋችሁ
አላህ አድሏችሁ ጥንድ አደረጋችሁ
ማሻአላህ ብለናል እንኳን ደሥ ያላችሁ
ኢላ የውሚል ቂያም ፍቅር አይለያችሁ
ሪዝቃችሁ ከሡ ነው ከጀሊል ከአላህ
እኛም ደሥ ብሎናል ብለናል ማሻአላህ.................

ሁሲ በአንደኛ ሚዜው ማሜ በቢና በሌሎች ሚዜዎቹም ታጅቦ እየገባ ነው....እልልታው ደመቀ ሴቶች በተፈቀደላቸው ቦታ ላይ ሆነው ሙሾ ያወርዳሉ...ዜማ እንደጉድ ያዘንባሉ...............
በድንገት ግን ካሊዶ ከመጠን በላይ ጠጥቶ ሲለፈልፍና እየጮኸ ሲሳደብ ሰማሁ...."ሰሙ የኔ ናት.....ማንም ሊወስድብኝ አይችልም....ህልሜንና ህይወቴን ሊነጥቀኝ የተዘጋጀውን እንዲኖር አልፈቅድለትም" አለ
ወዲያው የጥይት ድምጽ ቤቱን አደበላለቀው...በደመ ነፍሥ ካለሁበት ቦታ እየሮጥኩ ሥመጣ የሆነ ሠው ዝንፍል ብሎ ተኝቷል..አይኔን እየፈራሁት ወደ ከበቡት ሠዎች ሳመራ ሁሲ "ወይኔ ማሜ ወይኔ ወንድሜ እኔ ልጋደምልህ" እያለ...ይጮሃል ይንፈራፈራል.....ለሁሲ የተተኮሰችው ጥይት የጓደኛችንን የማሜን ህይወት ቀጠፈችው...በጓደኛው አለም ሊደሠት የመጣው ማሜh ባላሠበውና ባልጠበቀው መንገድ ህይወቱን አጣ።እዚህች ምድር ላይ ስንኖር የሠከንዶች ያህል የመኖሪያ ፍቃድ እንዳለን እንኳን እርግጠኛ መሆን አንችልም...ሞት ሣያማክረንና ሳያሥጠነቅቀን ድንገት ብቅ ይላልና.....አያችሁ ህይወት እንደዚህ ናት በቅጽበት ደሥታ በቅጽበት ሀዘን....እንደዚያ በደሥታና በፍንደቃ ጣሪያ ነክቶ የነበረው ቤት በሠከንዶች ልዩነት በዋይታና በሀዘን ድባብ ተውጧል። ጽልመት ነግሶበታል.................

/////////////********//////////

ህይወት ትቀጥላለች...የማሜ ሀዘን ክፉኛ ቢጎዳንም የወደፊት ኑሯችንን የተቃና ለማድረግና ደሥተኛ ጥንዶች ለመሆን እየሞከርን ነው.....አሁንም ማሜ ከሞተ ከ40 ቀን በሁላ የብቻችን የፍቅር ጊዜ እንዲኖረን በማሰብ ሀዋሳ ከትመናል....ሀዋሳ እጅግ ውብ ናት...አየሯ መንፈሥን ያድሳል...የሁሲ እቅፍ ውሥጥ ገብቼ ከሀይቁ ማዶ በቃኝ ብላ ልትጠልቅ የተቃረበችውን ጸሀይ እየተመለከትኩ ነው...እየመሸ ሥለሆነ አየሩ ማጉኝ ማጉኝ ይላል...በድንገት ሁሲ"የኔ ፍቅር ብንገባ አይሻልም" አለኝ ከምሽቱ 1 ሰአት አከባቢ....
እሺ ብዬው ከእቅፉ ወጣሁና እጅ ለእጅ ተያይዘን መንገድ ጀመርን..
እራት እየተጎራረሥን በላንና ወደ ክፍላችን አመራን...በጣም ደሥተኛ ነኝ በህይወቴ የመጀመሪያውን ጣፋጭ የፍቅር ምሽት በውቢቷ ሀዋሳ ላይ አሣለፍኩ ..መቼም የማይረሣ ትዝታ.....


////////////*******//////////////

ከ 9 ወር በሁዋላ.........

ፌቪ ዘንድሮ ጅማ ካሥመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዷ ሆናለች..
ሚኪ ትዳር ይዞ የልጅ አባት ሆኗል...
ካሊዶ 18 አመት ተፈርዶበት ከርቸሌ ወርዷል...
እኔም የመጀመሪያ ወንድ ልጄን ለመገላገል ቀናቶችን እየቆጠርኩ ነው........ዶክተሬ በሆዴ የተሸከምኩት ወንድ ልጅ እንደሆነ አብስሮኛል...ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ እየጮኸ ሊቀላቀለን በመሆኑ ሁሲ ከመጠን በላይ ተደስቷል።.... ልጃችንንም በኛ ደሥታ ላይ በተሠዋው ማሜ ሥም ልንሠይመው በጉጉት እየጠበቅነው ነው....


ከችግር በሁዋላ በእርግጥም ምቾት አለ።.....ሰደቀላሁል አዚም(አላህ እውነት ተናገረ)...
.

.
.
​​•════•••ተፈፀመ•••════•
    

ወዳጆቼ ሳገባህ ላፍቅርህ እንዴት ነበር...?
ያላችሁን ማንኛዉንም አስተያየት comment የሚለዉን በመጫን አድርሱኙ...ያበረታፈኛል

╔═══❖• •❖═══╗

╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@Pisces_m