Get Mystery Box with random crypto!

Fasika Tamiru እውነት እላችኋለው ብዙዎች ነቢያት እና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አ | ✞✞የንግስ መዝሙሮች👏👏👏

Fasika Tamiru እውነት እላችኋለው ብዙዎች ነቢያት እና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም÷የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮዎቻችሁም ስለሚሰሙ ብጹአን ናቸው።
ማቴ 13÷16-17


#ቃል_ኪዳን :-ስፍራውን የረገጠ ወንድ የ40ቀን
ሴት የ80ቀን ንጹሕ አደርገዋለው
:-በእለተ ምጽአት ቀን አያልፍም

:-የማልምረውን ስፍራውን አላስረግጠውም

:- በዚሕ ስፍራ የለመነኝን አልነሳውም
የጠየቀኝን አልከለክለውም

:-ሲኦልን አያያትም ባሕረ እሳትን አቅፌ አሻግረዋለው።


እነዚህን የተቀደሱ ስፍራዎች በማየት ለመባረክ የታደለ ማን ነው?ሰባት ድንቅ ገዳማት


#እመጓ_ኡራኤል
ይህ ገዳም መንዝ ውስጥ የሚገኝ /እመእጓል ቆጵሮስ ኢየሱስ ቅዱስ ኡራኤል /ገዳም
፩-ድንግል ማርያም ከልጅዋ ጋር በተሰደደች ግዜ የተቀመጠችበት ቦታ ነው፡፡

፪-የቦታውን ስም እራሱ ጌታችን ነው ስሙን ያወጣው /እመእጓል/ብሎ፡፡እመእጓል ሲለው /የእኔና የአንች ሀገር (የእናትና የልጅ)ሀገር ብሎታል

፫-በቦታው 2ተራራ አለ:----
1-ገሊላ(ክሊና)ተራራ:-ይህ ተራራ እመቤታችን የተቀመጠችበት ና ጌታችን ኢትዮጵያን አስራት ሀገርሽ ትሁንሽ ብሎ ያረገበት ቦታ ነው፡፡በተራራው ላይ በአየር ላይ የቆመ ድንጋይ ይታያል ፡በድንጋው ላይ ተወጥቶ 3ግዜ ይዞራል።

2-ቆጵሮስ ተራራ:-ይህ ተራራ ቅዱስ ኡራኤል የጌታን ደም የረጨበት ጽዋ(መነሳነስ)የሰወረበት ተራራ ነው የሰወረበት ቦታ ይታያል።
፬-በዚህ ቦታ ጌታችን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን አስራት ሀገርህ ነች ብሎት ያረገበት ቦታና የቅዱስ ጊዮርጊስ የፈረሱ የ4ቱ የእግሩ አሻራ በድንጋይ ላይ ታትሞ ይታያል፡፡
፭-በቦታው ላይ ዋሻ አለ ::በዋሻው ውስጥ:-
-/ የድንግል ማርያም የእጅዋ አሻራ በድንጋይ ታትሞ /ይታያል
-ያልፈረሰ;ያልበሰበሰ ክንፍ ያላቸው አፅመ ቅድሳን አጽም ይታያል
-የድንግልና የልጅዋ ልብስ እንዳለ ይነገራል።
-የሚጠበቀው ዋሻው በነጭ ነብርና በነጭ አንበሳ ነው ይታያሉ
፮-በዚሁ አካባቢ የማርያም ገዳም አለ የማርያም ቤተክርስቲያን ያረፈበት ቦታ ድንግል የተቀመጠችበትን ቦታ ቅዱስ ኡራኤል በክፉ የጠረገው ቦታ ነው ቤተክርስቲያን የተሰራው።
የቦታው ቃልኪዳን :-ቦታው የረገጠ (የቦታውን አካባቢ አሻግሮ ያየ)189ትውልድ እምረዋለሁ የጠየቀውን የሀሳቡን እሰጠዋለሁ እምረዋለሁ ተብሎ ቃል እንደተገባ አባቶች ይጠቁማሉ፡፡


✟ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ ታላቅ የበረከት ጉዞ ተዘጋጅቷል።✟

የጉዞ መነሻ ቀን መስከረም20/2015 ዓ.ም
መመለሻ ቀን መስከረም 22/2015 ዓ.ም

መነሻ ሰአት ንጋት 11:30 ሰአት

መነሻ ቦታ 1.ታጠቅ ገብርኤል
2. ልኳንዳ
3.18 አደባባይ


#በጉዞ_ላይ_የምንሳለማቸው_ገዳማት

1/ሀርባራ መድሀኒያለም
2/ጻድቃኔ ማርያም
3/ዘብር ገብርኤል


የጉዞ ዋጋ:-
#ሁሉንም_ማደሪያ_ቀን_እና_መስተንግዶን ጨምሮ

#1500ብር_ነው
ለበለጠ መረጃ በነዚ አድራሻ ያናግሩን
ስልክ:- 0902347665


@hayelewa
ማሳሰቢያ❀
°ማንኛውም ምእመን ሲመጣ ክርስታናዊ አለባበስ
ለብሶ ይምጣ/ትምጣ !!!
በተጨማሪም ሰአት ይከበር!!!


#ሼር_በማድረግም_ለኦርቶዶክስ_ወገኖቻችን_ለሌሎችም_በማካፈል_የበረከቱ_ተካፋይ_ይሁኑ።