Get Mystery Box with random crypto!

ተወዳጆች ሆይ !! … ለሁላችሁ ይድረስ ዘንድ ከዋልድባ አባቶች የመጣውን መልእክት እና የጻፉትን | ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ተወዳጆች ሆይ !!

… ለሁላችሁ ይድረስ ዘንድ ከዋልድባ አባቶች የመጣውን መልእክት እና የጻፉትን ደብዳቤም እነሆ ለጥፌላችኋለሁ። የዋልድባ አባቶች የችግራቸውን ዝርዝር ሁኔታ አንድ ሁለት ብለው ገልጸውላችኋል። የባንክ ደብተራቸውንም ልከዋል። እናም በተጠቀሰው የባንክ አካውንት በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም ያላችሁ እስከ ነገ ረቡዕ ድረስ እያስገባችሁ ጠብቁኝ። ገንዘቡ በሦሥተኛም በሁለተኛም ሰው እጅ አይነካካም። በዚያ በኩል ስጋት አይግባችሁ።

… እናንተ ከያላችሁበት ሆናችሁ የተቻላችሁን አስገቡላቸው። አስገቡና ያስገባችሁበትን ሪሲቱን የክርስትና ስማችሁን እየጻፋችሁበት በውስጥ መስመር ላኩልኝ። ነገ ረቡዕ በመረጃ ቲቪ፣ በኢትዮ ቤተሰብ፣ በዘወንጌል እና ( አግኝቼ አላስፈቀድኩትም ነገር ግን በኋላ ደውዬ እነግረዋለሁ) በወንድሜ በዲን ዓባይነህ ካሤ የፅዋዕ የዩቱዩብ ቻናሎች ላይ ለታላቁ ገዳማችን ለዋልድባ አብረንታንት ገዳም የገቢ ማሰባሰቢያ እናደርግላቸዋለን።

… እግዚአብሔር የፈቀደልን አሁኑኑ መስጠት እንጀምር። ከበረከቱም ለመሳተፍ እንሽቀዳደም። ጀምሩ … እንጀምር።

… ማነው?  የዋልድባ ወዳጅ የመጀመሪያው ፈር ቀዳጅ? እኔ ነኝ በልማ። ፍጠን፣ ፍጠኚ።

ጎንደር ዐቢይ ቅርንጫፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር 1000018796779
SWIFT = CBETETAA
ዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበር