Get Mystery Box with random crypto!

(በላይ በቀለ ወያ) ከለታት አንድ ቀን ከማጣህ ከምሞት? ፣ የሚል ምርጫ አቅርባ የራሷን ጥያቄ ፣ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን📖

(በላይ በቀለ ወያ)

ከለታት አንድ ቀን
ከማጣህ ከምሞት? ፣ የሚል ምርጫ አቅርባ
የራሷን ጥያቄ ፣ በእንባዋ አጅባ
ብሞት ይሻለኛል ፣ ብላ ነገረችኝ
ስትነግረኝ አመንኳት
እፈትናት ብዬ ፣ እንድትሞት ራኳት ፣ ሳትፈልግ አጣችኝ
።።።
ከእለታት ሁለት ቀን ፣
እሷ ዋሽታ አታውቅም ፣ ለቃሏ ታማኝ ነች
እንዳጣችኝ አውቃ ፣ ይሔኔ ሞታለች
በማለት አስቤ ፣
ለቀብሯ ስዘጋጅ ፣ እሷ ትኖራለች
።።።
ከእለታት ብዙ ቀን ፣
እንዴት አልሞተችም ?
የሚል የእምነት እዳ ፣ መች አብሰለሰለኝ?
አጥታኝ ስትኖር ባያት
እየኖረች መሞት ፣ ምታውቅ መሠለኝ
አምናታለሁና
እሷ አትዋሽምና


@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen