Get Mystery Box with random crypto!

'ፈተና ወይ ይሰብረናል ወይም ሪከርድ ያሰብረናል ' በአንድ ሀገር ውስጥ ተመሳሳይ ክስተት ተከስቶ | Lomi

"ፈተና ወይ ይሰብረናል ወይም ሪከርድ ያሰብረናል "

በአንድ ሀገር ውስጥ ተመሳሳይ ክስተት ተከስቶ ገሚሱ ሲቸገርበት ሌላው ደግሞ ያድግበታል ፣ አንድ ተቋም ውስጥ አንድ ቤተሰብ ውስጥ ፣ አንድ አይነት ንግድ ውስጥ ፣ እና ሌላም ስፍራ ተመሳሳይ ክስተት ለሰዎች ግን የተለያየ የውጤት ምንጭ ይሆናል ። ለምን ?????
በሁለቱ ውጤቶች መሀከል ያለው ልዩነት ለገጠመን የምንሰጠው ትርጉም ነው። ለፈተናው ምላሽ መስጠት እና መፍትሄ መስጠት ይለያያል። መፍትሄ በሰከነ ፣ አስተውሎት በተሞላበት እና ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር የሚደረግ ውሳኔ ሲሆን ምላሽ መስጠት ግን የገጠመንን ክስተት ተከትሎ በስሜት እና በጭንቀት የሚደረግ ምን ላድርግ ታዲያ ተብሎ ተገዶ ለመመለስ የሚሰጥ መልስ ነው። አሁን በህይወቴ ላይ እየገጠመኝ ላለው ፈተና ምን እያደረኩኝ ነው ? ሰከን ብለን እናስብ እና ወደሚቀጥለው ምዕራፍ የሚያሻግረንን መፍትሄ እንመልስ። መፍትሄ ምላሽ እንደመስጠት ( እንደ ማማረር ፣ ሰው ላይ እንደመፍረድ፣ እንደማሳበብ ፣ እንደመተው ) ቀላል አይደለም ውጤቱ ድንቅ ስለሆነ ብቻ የሚመረጥ የብልሆች ምርጫ ነው።
መፍትሄ ሂደቱን አይተን ሳይሆን መጨረሻውን አይተን የምንጀምረው ድንቅ ተግባር ነው።

ክስተት + ምላሽ = የማንፈልገው ውጤት
ክስተት + መፍትሄ = ስኬት

መልካም  ዕለተ ሰኞ!

መስከረም 16, 2015 ዓ.ም

https://t.me/kebezgreat_0872123