Get Mystery Box with random crypto!

ትላንት በተደረገው ላንክሻየር ደርቢ ጨዋታ ወደ ሜዳ ዘሎ የገባው ደጋፊ በቁጥጥር ስር ውሏል። ትና | Loserpool (ሼባዎቹ)

ትላንት በተደረገው ላንክሻየር ደርቢ ጨዋታ ወደ ሜዳ ዘሎ የገባው ደጋፊ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ትናንት ምሽት በአንፊልድ ዩናይትድን ባሸነፍንበት ጨዋታ የ16 አመት ታዳጊ ወደ ሜዳ በመግባቱ የመርሲሳይድ ፖሊስ ማሰሩን አረጋግጧል።

በጨዋታው ሮበርቶ ፊርሚኖ ሰባተኛውን ጎል ካስቆጠረ በኋላ ወጣቱ ደጋፊ ወደ ሜዳ የገባው ደስታውን ከተጨዋቾች ጋር አብሮ ለመግለፅ ወይም ለሌላ ነገር እንደሆነ አይታወቅም ግን በውሀ ረጥቦ የነበረው አንፊልድ አንሸራቶት በመውደቁ የሮበርትሰንን እግር መቷል በዚህም ምክንያት ሮበርትሰን ቁርጭምጭሚቱን ይዞ ታይቶ ነበር ወዲያው በፀጥታ ሀይሎች ተይዟል ከሜዳ ይዘውት ሲወጡ የክሎፕ ምላሽ ጩኸት የተሞላበት ነበር።

የመርሲሳይድ ፖሊስ በዚህ ጉዳይ ከክለባችን ጋር በጋራ ምርመራ እያካሄደ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እድሜ ልኩን ወደ የትኛውም የእንግሊዝ ስታዲየም እንዳይገባ ይታገዳል።

የታሰረው ግለሰብ ስም ያልተጠቀሰ ሲሆን የሚኖረው ግን በሊቨርፑል ዊንስፎርድ አካባቢ ነው።

ክለባችንም በይፋዊ ደህረ-ገፁ በተጨዋቹ ላይ ምርመራ እንደጀመረ አስታውቋል። ''ትላንት ወደ ሜዳ የገባውን ደጋፊ ለማወቅ ምርመራ ተጀምሯል በቁጥጥር ስር የዋለው ሰው ከ7ኛው ጎል በኋላ ወደ ሜዳ ሮጦ ገብቶ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ደስታቸውን ሲገልፁ በመጋጨቱ ጉዳት አድርሷል። የተጨዋቾች የስራ ባልደረቦች እንዲሁም የደጋፊዎች ደህንነት ከሁሉም በላይ ነው''

ክለባችን አሁን የተከፈተው ምርመራ ሳይጠናቀቅ ይህ ሰው ስታዲየም እንዳይገባ እገዳ ጥሎበታል።

ለሙሉ መረጃው: [ዴይሊ ሜይል]

@liverpool4321 @liverpool4321