Get Mystery Box with random crypto!

እግር ኳስ የሰነጠቃቸው ሁለት ከተሞች ጉምቱ አሰልጣኞች ስድብ ያመረቱበት ገናና ተጨዋቾች አንጨባበጥ | Loserpool (ሼባዎቹ)

እግር ኳስ የሰነጠቃቸው ሁለት ከተሞች ጉምቱ አሰልጣኞች ስድብ ያመረቱበት ገናና ተጨዋቾች አንጨባበጥም ያሉበት ደማማ የእግር ኳስ ጦርነት ከሁለቱም አቅጣጫ እሳት በየዘመኑ ይወረወራል ጨዋታው የ90 ደቂቃ ብቻ አይደለም ከዛ የዘለለ ትርጉም ይሸከማል....

በተቀናቃኞቻቸው የሞት ክስተት ላይ እንኳን ሹፈትን ለመፍጠር የማይመለሱ ነውጠኛ ደጋፊዎች የሚታዩበት ታሪክም ወቅታዊ ሁኔታም ጋዝ ሇነው የሚያቀጣጥሉት አሰልጣኞችም ተጨዋቾችም ከስሜት የማይፀዱበት ልጅም አዋቂም እኩል ጎራ ከፍለው የሚሻኮቱበት የፖለቲካም የኢኮኖሚም የስፖርት የበላይነት ጥያቄም ያልተለየው የእግርኳስ ጦርነት ቀዩ ትንቅንቅ the red rivalry
#ሊቨርፑል_ከ_ማንቸስተር_ዩናይትድ

"የኔ ፈተና አንድ ብቻ ነው ሊቨርፑልን ሁሌም በሚኩራሩበት ሜዳ መደቆስ ከዛ ቀሪውን እናንተ ትፅፉታላችሁ. ይህ የሰር አሌክስ የአንድ ወቅት ንግግር ነው"

"እኔ ስለ ሊቨርፑሎች ምን አገባኝ ደጋፊያቸው ስታዲየማቸው ምናቸውም ደስ አይለኝም እነሱን ስናሸንፍ የሚሰማኝን ደስታ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው" ጋሪ ኔቭል

"ያደግኩት ሊቨርፑልን እየጠላሁ ነው" ዋይን ማርክ ሩኒ

ወደ አንፊልድ መንደርም እናምራ በአንድ ወቅት ስቴቭን ጀራርድ ወደ መኖሪያው አንድ የቀረፃ ቡድን ይዞ ሄደ እነዚህ የምትመለከቷቸው መለያዎች በርካታ የተቃራኒ ክለብ ቲሸርቶችን እያሳየ ከጨዋታ ቡሀላ የተቀያየርኳቸው መለያወች ናቸው ግን አንድም የዩናይትድ መለያ አታገኙም አንድም የዩናይትድ መለያ ቤቴ አይገባም አለ ጀራርድ....

ሁለቱን ከተሞች ከአንድ ሰአት ያነሰ መንገድ ብቻ ያላያያቸዋል ማህበራዊና ታሪካዊ ዳራወች ያጠሉበት እግር ኳስ ግን የዘላለም ተቀናቃኝ አድርጓቸዋል
የሰሜን ምዕራብ እንግሊዝን የበላይነት ለመቆጣጠር ሁለቱ ከተሞች ፍልሚያ ያደርጉ ነበር ማንቸስተር በማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ትመራለች ሊቨርፑል በወደብ ከተማነት ትንቅንቅ ውስጥ ገቡ

ያ የከተማ ተቀናቃኝነት ኢኮኖሚያዊ ሽኩቻ በቀላሉ ወደ እግር ኳስ ሜዳወች መጣ ሁለቱ ክለቦች የእንግሊዝ ሀያሉ ክለብ እኔ ነኝ በማለት ይቆራቆዛሉ
ሁለቱ ክለቦች በጋራ 135 ዋንጫወችን ጥርግርግ አርገው አጣጥመዋል

ሊቨርፑል ከ1975 እስከ 2020 12 የሊግ ዋንጫወችን ያነሳባቸውን አመታት በኩራት ያነሳል
ማንቸስተር ከ1993 እስከ 2013 ፍፁም በነገሰባቸውና 13 የኘሪሚየር ሊግ ዋንጫወችን ባነሳባቸውን አመታት በመኩራራት የእንግሊዝ ሀያሉ ክለብ እኔ ነኝ ይላል....

ሁሌም ከሜዳ ውጭ የሚጫወተውን ክለብ ለመደገፍ ትኬት ማግኘት ከባድ ነው ቀድሞ ትኬት ይጠናቀቃል በጠላት ድንበር ገብተህ እንደመዘመርና እንደ መቦረቅ ምን የሚያስደስት ነገር አለ የሚሉ ደጋፊዎች ብዙ ናቸው

ሁለቱ ሲጫወቱ በብስጭት የተገኘ ነገር ሁሉ ይወረወራል ፈርጉሰን በሊቨርፑል ደጋፊዎች በእንቁላል ተደብድበዋል በ2011 የታዳጊዎች FA ጨዋታ ተቋርጧል ብዙ ብዙ...

የሁለቱን ክለቦች የመረረ ጥላቻ የሚያሳይ ሌላም መገለጫ አለ
በ1964 ፊል ቼዝናል የተባለ ተጨዋች ከዪናይትድ ወደ ሊቨርፑል ከተዛወረ ቡሀላ በዚህ ሁሉ ግዜ ውስጥ ማለትም ከ 54 አመታት ባለፋ ግዜያት ውስጥ በሁለቱ ክለቦች መካከል አንድም የተጨዋቾች ዝውውር በቀጥታ ተፈፅሞ አያውቅም።

የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ልጅ ሲወልዱ "Born to hate Liverpool/ሊቨርፑልን ለመጥላት የተወለደ/የተወለደች እያሉ ልጆቻቸው ላይ ሳይቀር ከእግርኳስ ባለፈም ያላቸውን ጥላቻ ለትውልዶቻቸው ያስቀጥላሉ! የሊቨርፑል ደጋፊዎችም በተመሳሳይ!

ዩናይትድ በእንግሊዝ ምድር ሁለት ከደርቢነት ባለፈም እንደ ዋንኛ ጠላት የሚያዩት ሁለት ክለቦች አሉ እነሱም ሊቨርፑልና ሊድስ ዩናይትድ ናቸው!

ብዙዎች በዩናይትድና በማንሲቲ በኩል ያለው ፉክክር የሚያመዝን ይመስላቸዋል ሆኖም የማንቸስተር ደርቢ ከከተማ ተቀናቃኝነት የዘለለ ትርጉም የለውም!

ሊቨርፑል Vs ዩናይትድ!
ይህ ጨዋታ ያለጥርጥር በአውሮፓ ካሉ ሀያል ፋክክሮች አንዱ ነው ......ነገ ምሽት 1:30 በአንፊልድ የሚፋለሙ ይሆናል

YNWA
GOOD LUCK FOR REDS