Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ነገር ልበላችሁ አሁን ቦቢ በአመቱ መጨረሻ ክለቡን ለቆ ይወጣል። ማለትም ከዛ በኋላ ለፈለገው | Loserpool (ሼባዎቹ)

አንድ ነገር ልበላችሁ አሁን ቦቢ በአመቱ መጨረሻ ክለቡን ለቆ ይወጣል። ማለትም ከዛ በኋላ ለፈለገው ክለብ ውል መፈረም ይችላል። አውቃለሁ ቦቢ የሊጉ የምንግዜም ምርጦቹ ሀሰተኛ ዘጠኝ ቁጥር ውስጥ አንዱ ነው። ለሳላህና ማኔ ምርጥ መሆን ሚስጥሩም እሱ ነው። በሊቨርፑል ቤት በስኬት ላይ ስኬት ደራርቧል። ይሄን ሁላችንም እናቀዋለን ነገር ግን አንድ ተጫዋች አንድ ክለብ ላይ መቶ እድሜ ልኩን መጫወት የለበትም። ቦቢም ጊዜው ደርሷል ሊለየን ነው መልካሙን ሁሉ እንመኝለታለን። በማኔም አይተነዋል። የማኔ አለመኖር አዎ ጎድቶናል ግን በቃ ሄዷል። አሁን ሊቨርፑል ሲሸነፍ ወይ አቻ ሲወጣ ማኔ ፣ የማኔ ግፍ ፣ ማኔን ስለሸጡት ነው ይባላል። ነገር ግን ይህ ማለት የክለቡ ሳይሆን የተጫዋቹ ደጋፊ መሆን ነው። በብዙ ክለቦች ደግሞ አንድ ተጫዋች ጊዜውን ከጨረሰ በክብር ይለያያል አለቀ። ቦቢም ሊቨርፑል መቶ መብላት ሚችለውን ዋንጫ ሁሉ በልቷል። ስኬታማ ሆኗል። እድሜው እየሄደ ነው። ስለዚህ ለተተኪዎቹ ቦታ መልቀቅ አለበት። ጋክፖ የመጣው ለሱ ምትክ ነው። አንድ ተጫዋች ላይ የሙጥኝ አንበል። ቦቢን ጠልቼው አይደለም ሊቨርፑልን ስለምወደው ነው ቦቢ እንኳን በሊቨርፑል ደጋፊ አደለም በተቃራኒም ደጋፊዎች ሳይቀር ተወዳጁ ተጫዋች ነው። ትናፍቀናለህ። ጊዜውም ደርሷልና ልንለያይ ነው።

ያስማማል ብዬ አስባለሁ።

#SiSeñor

@Liverpool4321 @Liverpool4321