Get Mystery Box with random crypto!

اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው | ሊላህ/for Allah

اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡

خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ

ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡

اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ

አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤

ይኼው ተዓምራዊ ተነባቢ መፅሃፍ ቁርኣን መልዕክቱን የወጠነው ''አንብብ '' በሚል ቃል ነዉ ። የማገርማችሁ የሰው ልጅ በመጨረሻ ዓለም የስራ መዝገቡን በሚሰጥበት ጊዜ በምድራዊ ህይወቱ የሰራቸውን ደግና ክፉ ስራዎችን ዝርዝር ራሱ ያነብ ዘንድ መጠየቁ የማይቀር ነው።
፦ አስተውሉ ይህ አንቀጽ አንድ አማኝ ""አንብብ ""በሚል መለኮታዊ ትዕዛዝ ህይወቱን ጀምሮ ''ተነባቢ ''የሆነውን ተዓምራዊ መፅሐፍ በማንበብና በመረዳት ሕይወቱን በፍኖቱ መርቶ በመጨረሻም የስራ መዝገቡን አንብብ ይባላል ።በንባብ ተጀምሮ በንባብ የሚቋጭ ሕይወት ውስጥ ያለ ሰው ስለንባብ ሊኖረው የሚችለውን በጎ ምልከታ እያስተዋላችሁ ነው?
ምንጭ ፦ለውጥ መፅሐፍ
ታድያ እኛ ሙስሊሞች የት ነዉ ያለነው ከንባብ መራቃችን ለምን ይሆን ?