Get Mystery Box with random crypto!

አዕምሮህን የሚያድስ የግብ ዕውቀት ➲ ጥልቅ ህልም ግብን ይቀድማል፤ ስለዚህ ግብህን ከመያዝህ | Life Wisdoms College📚

አዕምሮህን የሚያድስ የግብ ዕውቀት

➲ ጥልቅ ህልም ግብን ይቀድማል፤ ስለዚህ ግብህን ከመያዝህ በፊት ጥልቅ ህልም እንዳለህ እርግጠኛ ሁን። ግብ ከጥልቅ የህልም ባህር የሚቀዳ አንኳር አቋም ነው ወይም ግብህ የህልምህ ፍሬ ነውና።

➲ ህልሞችህን እና ግቦችህን በወረቀት ላይ በመመዝገብ፣ በጣም የምትፈልገውን ሰው የመሆን ሂደትን አንቀሳቅስ። በዚህም የወደፊት ዕጣህን በራስህ እጅ ላይ ጠንቅቀህ በመያዝ ነገህን በግቦችህ ውስጥ ልትሰራው ትችላለህ።

➲ ግቦችህን በጥንቃቄ አጠናቅቀህ ያዝ። እነርሱን ለማሳካት እቅድ አውጣና እራስህን አዘጋጅ። ከዚያም በከፍተኛ እምነት፣ ቆራጥነት እና መሰናክሎችን በማለፍ የአሸናፊነት አቅም የሌሎች ሰዎችን ትችትና ፍርሃትህን ችላ እያልክ እቅድህን ፈጽም።

➲ ወዳጄ ከዋክብት በነፍስህ ውስጥ ተደብቀዋልና ወደ ውስጥ ተመልከት። ዛሬና ነገ ደስተኛ ህይወትን ከፈለግክ ከሰዎች ወይም ከነገሮች ጋር ሳይሆን ከግብህ ጋር ራስህን አጣብቅ።


ግብህን ለመምታት ከራስህ ጋር ብቻ ተወዳዳሪ ሁን!


Touch it & then Join it.

@LifeCollege
@LifeCollege