የጸሐፊው ሀደራ ከድንቅ ኢትዮጵያውያን (ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን) የደም ጅረት የተቀዳን የመስዋዕትነት ደም ፍሬ እና ከአጥንታቸው ተፈልጠን ፣ ከሥጋቸውም ተቆርሰን በተዋችው ነፍሳቸው ነፍስ የዘራን የወጣት ጉብሎቻችን እና የሽማግሌ አባቶቻችን ተወካዮችና ሀደራቸው የተጣለብን መሆናችንን አንርሳ። በዱር በገደሉ ያልደከመው ጉልበታቸው ፣ በቁር በሀሩሩ ያልዛለው ኢትዮጵያዊነታቸው ፣ እንደ ውኃ የፈሰሰው ደማቸው ፣ እንደ እንጨት የደረቀው አጥንታቸውና በቁራና በአውሬ የተቆረሰው ሥጋቸው ለእኛና ለእኛ ብቻ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቢመቸንም ባይመቸንም ባለንበት ሥፍራ ሆነን ለእናታችን ለኢትዮጵያ በግብ ሕይወት ለመኖር እንትጋ። : : : Touch it & then Join it! https://t.me/LifeCollege https://t.me/LifeCollege 102 viewsክብረክርስቶስ የአብ, edited 11:00