Get Mystery Box with random crypto!

ወድ ቅዱሳን እንዲሁም የጌታ ባሪያዎች እንኩዋን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳ | Lewi arts team

ወድ ቅዱሳን እንዲሁም የጌታ ባሪያዎች እንኩዋን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም, የፍቅር,የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን
የጌተ ቤተሰቦች በዚሁ አንድ ነገር አናሳስባቹ በዓሉን ስታከብሩ እነዚህን ነገሮች በማሰብ እንዲሁም በመተግበር አሳልፉ
1,የተቸገረቱን ባለን ነገር በመረዳት
2,የሞተልንን ክርስቶስንን በዙሪያችን ላሉ በመናገር
3,ከመብል እና ከመጠጥ ባለፈ ያዳነንን ጌታ በማክበር
እናሳልፍ አንላለን
እንግዲህ ራሱ አሳልፎ ተሰጥቷ የፍቅር ጥግ አሳይቶናል ።


(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53)
----------
5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6፤ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።

7፤ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም

@Lewiartstemi
#ሌዋዊያን #የስነጽሁፍ #ህብረት