Get Mystery Box with random crypto!

በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሥራው ተጠናቆ ግንቦት1 በ2012 ዓ.ም ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደስ | ልሳነ ተዋህዶ

በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሥራው ተጠናቆ ግንቦት1 በ2012 ዓ.ም ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ እየተገለገልን እንገኛለን፡፡ ነገር ግን በአካባቢው ያለንው ህዝበ ክርስቲያን በቁጥር በጣም አናሳ ስለሆኑብን እና የሚማርም የአብነት ተማሪ ስለሌለ በወር እንድ ጊዜ ብቻ ወር በገባ በ16 ቅዳሴ እየተቀደሰ አገልግሎት ስናገኝ ቆይተናል፡፡ ከመጋቢት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በበጎ አድራጊዎች አማካኝነት ወር በገባ የመጀመሪያውን እሁድ እና ወር በገባ በመጨረሻው እሁድን የሚያገለግሉ 5 አገልጋዮች በወር 200 ብር ለአንድ አገልጋይ በመክፈል በወር 3 ጊዜ እንድንገለገል እና እመቤታችን እንድትወደስ፡ ቅዳሴ እንድቀደስ አድርገዋል፡፡ አሁን አገልግሎት እያገኘን ያለንው አካባቢው በጣም ገጠር በመሆኑ ምክንያት ከኮሌት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተነስተው በእግር 2፡00 ሰዓት የሚፈጀውን መንገድ ተጉዘው እየመጡ ወር በገባ የመጀመሪያውን እሁድ፡ የኪዳነ ምሕረት ዕለት ማለትም ወር በገባ በ 16 እና ወር በገባ በመጨረሻው እሁድ በወር 3 ቀን ብቻ ቤተ ክርስቲያኑ ተከፍቶ ቅዳሴ ለማስቀደስ ለአንድ አገልጋይ በወር 200 (ሁለት መቶ) ብር እየከፈልን ነው፡፡ ይህ አገልግሎት ተጠናክሮ እድቀጥል አገልጋዮቻችንም ተማረው አገልግሎቱን እዳያቋርጡብን በሰዓቱ ክፍያዉን ለመክፈል ና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያኑ የራሱ ገቢ እስከሚኖረዉ ድረስ የተቻለዎትን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100-03-79-16-14-84 ጉብሪት ወይብላ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ብለው ገቢ በማድረግ የገጠሩን ምእመን በማገልገል የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ::

ለበለጠ መረጃ ፡ በ 09-09-43-94-70 ይደውሉ::

#ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሸር ያድርጉ::