Get Mystery Box with random crypto!

ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች ***** | WMG Biomedical (Lemon Healthcare)

ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች
***************

• ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዓላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና ለሽብር ቡድኖች ዓላማ መሳካት አስተዋፅዖ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር ንግግር በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጨት የተከለከለ ነው

• በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ በተዋረድ ውክልና ከሰጣቸው አካላት ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የተከለከለ ነው

• ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ሌሎች ፈቃድ ከሚሰጣቸው የፀጥታ አካላት ወይም ከነዚህ አካላት እውቅናና ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው

• በከተሞች አካባቢ የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው

• ማንኛውም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ የተከለከለ ነው።

ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም