Get Mystery Box with random crypto!

ከጤና ሚኒስቴር ፦ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤ | WMG Biomedical (Lemon Healthcare)

ከጤና ሚኒስቴር ፦

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤና መኮንን፣ ሚድዋይፈሪ፣ ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ ቅድመ ሙያ ፍቃድ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ ጤና ባለሙያዎች በህዳር/2014 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና ምዝገባ ከጥቅምት 05-20/2014 ዓ.ም የሚካሄድ ስለሆነ አዲስም ሆነ ዳግም ተመዛኞች በኦንላይን hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የተቀመጠውን መመሪያ (Instruction) በጥንቃቄ በማንበብ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ እያሳሰብን የኦንላይን ምዝገባው እስከ ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም ብቻ የሚቆይና ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምንም አይነት የምዝገባ ጥያቄ የማንቀበል መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ፎርም Print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦ ምዝገባው ለአዲስም ሆነ ነባር ተመዛኞች፣ ለመንግስትም ሆነ የግል ተቋም ተመራቂዎች ሙሉ ለሙሉ online የሚካሄድ በመሆኑ ተመዛኞች ይህንን አውቃችሁ በመመሪያው መሰረት የትምህርት ማስረጃችሁን (ዲግሪ) በማያያዝ (Upload በማድረግ) እንድትመዘገቡ እያሳሰብን፣ የግል የትምህርት ተቋማት ተመዛኞች ለፈተናው ለመመዝገብ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ህጋዊነት እና ትክክለኛነት በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ (HERQA) በኩል ማረጋገጥ (Authenticate ማስደረግ) እንዲሁም ስማችሁ ከHERQA ወደ ጤና ሚኒስቴር እንዲተላለፍ ማድረግ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

@tikvahuniversity