Get Mystery Box with random crypto!

አሁንም ጥንቃቄ ያስፈልጋል #DrLiaTadesse የጤና ሚኒስቴር ሚ | WMG Biomedical (Lemon Healthcare)

አሁንም ጥንቃቄ ያስፈልጋል

#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ በኢትዮጵያ " ዴልታ " የተሰኘውን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መመርመር አለመጀመሩን አሳውቀዋል።

ምርመራው እስካሁን ያልተጀመረው ዝርያውን ለመመርመር የሚያስፈልገው ኬሚካል ወይም " ሪኤጀንት " እስካሁን አገር ውስጥ ባለመኖሩ ነው ብለዋል።

መስሪያ ቤታቸው ኬሚካሉን ከውጭ አገር ለማስገባት በሂደት ላይ በመሆኑን የገለፁት ዶ/ር ሊያ ፥ በቅርቡ ምርመራው ይጀመራል ብለዋል።

በሌላ በኩል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር በአዲስ አበባ 59 በመቶ ከአዲስ አበባ ውጪ 20 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ሊያ ፥ ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ ዜጎች፣ በቫይረሱ የሚያዙ እና ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ፦
• ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ ዜጎች በ2.5 በመቶ ጨምሯል።
• በቫይረሱ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር ከ2.8 በመቶ ወደ 7.4 በመቶ ከፍ ብሏል።
• ህይወታቸው የሚያልፍ ዜጎች ቁጥር ከ13 በመቶ ወደ 36 በመቶ አሻቅቧል።

የመረጃ ባለቤት ፡ አል አይን


Telegram
https://t.me/lemonhealthcare


Face book: https://facebook.com/lemonhealthcare/