Get Mystery Box with random crypto!

kehulum lehulum bufe ከሁሉም ለሁሉም ቡፌ

የቴሌግራም ቻናል አርማ lehulumbufe — kehulum lehulum bufe ከሁሉም ለሁሉም ቡፌ K
የቴሌግራም ቻናል አርማ lehulumbufe — kehulum lehulum bufe ከሁሉም ለሁሉም ቡፌ
የሰርጥ አድራሻ: @lehulumbufe
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

ትረካዎች፣ስሜትን ሰቅዘው የሚይዙ ልብ ወለዶች፣ጣፋጭና መሳጭ ታሪኮች፣ድንቃድንቅ ወሬዎች፣አስገራሚ እውነታዎች፣ታሪካዊ ሁነቶች፣ፍልስፍናዎች፣ከታዋቂ ሰዎች ጋር የተደረጉ ቃለ ምልልሶች፣ሳቅን የሚያጭሩ የኮሜዲ ስራዎች፣በተለያዩ ደራሲያን የተጻፉ የግጥም ስራዎች፣የዜማ፣የግጥም፣የኮሜዲ ባለተሰጦዎች ተወዳድረው የሚሸለሙበት ፕሮግራሞች የሚቀርቡበት። ሊንኩን ለማግኘት @lehulumbufe
የሚለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-01 10:21:06
በአልጄሪያ በሰርጓ እለት በሙሽራዉ እናት አስቀያሚና አጭር ነሽ በሚል ትዳሬ ተበተነ ያለችዉ ግለሰብ መነጋገሪያ ሆናለች

ባለፈው ሳምንት ቱኒዝያዊቷ ላሚያ አል ላባዊ በፌስቡክ ገጿ ላይ ምርጡ ቀኔ ወደ ቅዠት የተቀየረበትን አሳዛኝ ታሪክ እወቁልኝ ስትል አካፍላለች።እሷ እና የአራት አመት የፍቅር አጋሯ ጋብቻ ለመፈጸም ሁሉም ነገር ተስተካክሎ በእቅዳቸዉ መሰረት እየሄደ ይመስላል፡፡ ለሰርጋቸዉ ድምቀት ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተዋል፡፡

ነገር ግን አንድ ነገር ግምት ውስጥ ያላስገቡት የሙሽራው እናትን ነበር፡፡ ላሚያ ከዚህ በፊት ሴትየዋን በአካል አግኝታት እንደማታውቅ ተናግራለች ሆኖም ከባሏ ቤተሰብ ሞቅ ያለ አቀባበል ጠብቃለች፡፡የሠርጉ ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ እንግዶቹ ቦታቸዉን ይዘዉ ተቀምጠዋል፡፡ የሙሽራዉ ወላጅ እናት ወደ ፊት በመዉጣት ሙሽራዋ "በጣም አጭር እና አስቀያሚ" እንደሆነች እና ልጄን ለማግባት አትችልም ሰርጉ እንዳልተደረገ በመቁጠር መሰረዙን ትናገራለች፡፡

ይህችዉ ሴት እሷ ከዚህ ቀደም የላሚያን ፎቶዎች ብቻ እንደተመለከተች እና በአካል ካየቻት በኋላ በጣም መበሳጨቷን ገልጻለች፡፡ሴትየዋ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው በሚችል ክስተት ላይ የነበራትን ንዴት መቆጣጠር አለመቻሏ አስደንጋጭ ቢሆንም በሙሽራው ምላሽ ግን ይበልጥ ተገርመዋል፡፡ከእናቱ ጎን በመሰለፍ በሰርጉ ላይ የተገኙ በርካታ ሰዎች ቢለምኑም፣ ላሚያን ትቶ ከእናቱ ጋር ሄዷል።

ቻናሉን ለመቀላቀል @lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot ን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!
203 views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 20:59:14 ለፈገግታ!

ለአካል ክፍሎቼ ስም እያወጣሁ ነበር ዓይኔን ቦጋለ አልኩት ደረቴን ወሰን የለህ አልኩት እጄን ለገሰ አልኩት መሽኛዬ ላይ ስደርስ እድሉን ለሚስቴ ሰጠኋት እናም ሚስቴ አናጋው አልያም ዳምጠው ትለዋለች ብዬ ገመትኩ እሷ ግን ያወጣችለት ስም....

#ቢያድግልኝ ነበር

በእቀቱ ስዩም!
ቻናሉን ለመቀላቀል @lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot ን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!
444 views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 09:00:08 የአይዛክ ኒውተን የስበት ህግ እና አልበርት አንስታይን:

የ 22 አመቱ የብሪታኒያ ተወላጁ አይዛክ ኒውተን በመኖሪያ ቤት ግቢው ከሚገኘው የአትክልት ስፍራ ውስጥ አንዱ የፖም ዛፍ ስር ተቀምጧል። እንደድንገት
ከደረሱት ፖሞች ውስጥ አንዱዋ ከዛፉ ላይ ወድቃ የአይዛክ ኒውተን ራስ ላይ ታርፋለች። ያቺ ቅፅበት አሁን ላለንባት የፊዚክስ የላቀ ምጥቀት ምክንያት ሆነች። አይዛክ ኒውተን ከተቀመጠበት ተነስቶ ማሰላሰል ጀመረ። 'ፍሬዋ እንዴት ልትወድቅ ቻለች?'፤ 'ወደመሬቱስ እንድትወድቅ ያደረጋት ምንድነው?'

እነዚህ ጥያቄዎች አእምሮውን ይከነክኑት ጀመር። ከወራት ጥናት በሗላ ፍሬዋን እንድትወድቅ ያደረጋት የስበት ሀይል (Gravity) እንደሆነ አረጋገጠ። ከጥቂት አስርት አመታት በፊት ታዋቂው የጣልያን ተወላጁ የጠፈር ተመራማሪ ጋሊሊዮ ጋሊሊ እንዲሁ ስለ ስበት ሀይል መኖር ሲያስተምር የነበር ቢሆንም የኒውተን ግን በሂሳባዊ ቀመር የተደገፈ እና የተብራራ በመሆኑ ተቀባይነትን አገኘ። ኒውተን በዛው አመት 'ፕሪንሲፖ ማትማቲካ' የተባለ መጣጥፍ አሳተመ። በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ስለ ስበት ሀይል አብራርቶ ከሂሳባዊ ቀመር ጋር አስደግፎ ፅፎ ነበር።

ኒውተን የስበት ሀይልን ያየበት አቅጣጫ በግዜው የነበሩ ሌሎች ተመራማሪዎችን ያስደመመ ነበር። ፍሬዋን ከዛፉ ላይ እንድትወድቅ ያደረጋት ሀይል እና ምድራችን በፀሀያችን ዙሪያ እንድትዞር ያደረጋት ሀይል አንድ አይነት ናቸው ብሎ አሰበ፤ ይህ ሀይል የስበት ሀይል(Gravity) እንደሆነ አመነ። ፀሀይን ለአፍታ ማጥፋት ብንችል በቅፅበት ምድራችንም ሌሎች ፕላኔቶች ከምህዋራቸው ይወጣሉ ብሎ አሰበ። ይህ ንድፈሀሳብ ለ 250 አመታት ያክል ተቀባይነት አግኝቶ ነበር።

አልበርት አንስታይን

ይህ የኒውተን ንድፈሀሳብ ለጀርመን ተወላጁ የ20 አመት አፍላ ወጣቱ አልበርት አንስታይን ሊዋጥለት አልቻለም። በግዜው(1930ዎቹ) የታላቁ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ቲዮረቲካል ፊዚክስ ተማሪ የነበረው አንስታይን ለኒውተን ስራዎች ትልቅ አድናቆት የነበረው ቢሆንም ኒውተን የስበት ንድፈሀሳቡ ላይ ፀሀይን ብናጠፋት 'ከመቅፅበት' ፕላኔቶች ምህዋራቸውን(orbit) ይስታሉ ያለው አልተዋጠለትም። 'ከመቅፅበት' የምትለዋ
ቃል ናት ጥርጣሬ ያሳደረችበት። አንስታይን ይህን ሀሳብ መሰረት በማድረግ ለአስር አመታት ያህል አዲስ ንድፈሀሳብ ለማግኘት ጣረ። በመጨረሻም ዩኒቨርስን በሌላ አቅጣጫ እንድናይ የረዳንን የ ጀነራል ሪላቲቪቲ ንድፈሀሳብን አገኘ(General relativity theory)።

በዚህ ንድፈሀሳብ መሰረት ከኒውተን ጋር ላልተስማማበት ሀሳብ መልስ አገኘ። በአንስታይን ንድፈሀሳብ መሰረት ግዜ እና ቦታ አንድ ላይ የተሰፉ ምንጣፍ ናቸው። ግዜ ከቦታ ቦታ ከግዜ አይለዩም። ይህንን ስፔስ ታይም ፋብሪክ(Space-time fabric) ብሎ ጠራው። ክብደት ያላቸው ቁስ አካሎች በግዜ-ቦታ ድር ላይ ስርጉደት እንደሚያመጡም ይገልፃል። ምድራችን የምትዞርበት ምህዋር ፀሀያችን ድሩ ላይ በፈጠረችው ስርጉደት ውስጥ ነው ብሎ አመነ።

ስለዚህ ፀሀያችንን ለአፍታ ማጥፋት ብንችል በፀሀያችን ክብደት ሰርጉዶ የነበረው ድር ወደቦታው ሲመለስ የሚፈጥረው ሞገድ ይኖራል። ልክ ወንዝ ውስጥ ድንጋይ ስንወረውር ጫፍ ድረስ እንደሚመጡት የውሀ ሞገዶች ሁሉ ይህም ሞገድ ከፀሀይ ተነስቶ መላው ስርአተ-ፀሀያችንን ያካልላል። ይህን ሞገድ የስበት ሞገድ(gravitationnal wave)
ብሎ ጠራው። የሚጉዋዝበትም ፍጥነት በብርሀን ፍጥነት እንደሆነ በሂሳባዊ ስሌት አረጋገጠ። ስለዚህ ምድራችን ከምህዋሩዋ የምትወጣው 'ከመቅፅበት' ሳይሆን ይህ የስበት ሞገድ ከፀሀይ አቅጣጫ መጥቶ ምድራችንን ሲነካት እንደሆነ ተናገረ። ከፀሀይ የመነጨ ብርሀን ምድራችን ለመድረስ 8 ደቂቃዎች ይፈጅበታል፤ የስበት ሞገድ ፍጥነት ከብርሀን ፍጥነት እኩል ነው ማለት ምድራችንን ምህዋሩዋን ለመሳት 8 ደቂቃዎች ያስፈልጉዋታል ማለት ነው።

አልበርት አንስታይን ይህንን ንድፈሀሳብ ጀነራል ሪላቲቪቲ ብሎ ጠራው። በዚህ ንድፈሀሳቡም ትልቅ ዝናን ተቀዳጀ። የኒውተንን የስበት ንድፈሀሳብ ከራሱ ሪላቲቪቲ ንድፈሀሳብ ጋር አዋሀደ።

ቻናላችንን ለመቀላቀል @lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!!
ለሀሣብ አሥተያየት ደግሞ @lehulum_1bot የሚለውን ይጠቀሙ. ሼር ማድረጉም እንዳይረሣ!!
361 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 14:01:32 ራምቦ በአፍጋኒስታን
----
አፈንዲ ሙተቂ
----
ረጅሙ የአፍጋኒስታን ጦርነት የብዙዎችን ህይወት ከመቅጠፉ ባሻገር ጥበባዊ አበርክቶዎችም አሉት። ይህ ጦርነት ልክ እንደ ቪየትናም ጦርነት የብዙ ሲኒማዎች፣ መጽሐፎች እና መጣጥፎች መነሻ እና መቸት ለመሆን የበቃ ነው። የአፍጋኒስታን ጦርነትን እንደ መቼት በማድረግ ከተሰሩት ፊልሞች መካከል እጅግ ዝነኛ ለመሆን የበቃው Rambo-III ይሰኛል።
----
የራምቦ ክፍል ሶስት ፊልም ዋና አክተር ታዋቂው የሲኒማ ሰው ሲልቨስተር ስታሎን ነው። የፊልሙ ስክሪፕት ጸሐፊም ስታሎን ራሱ ነው። ይህ ፊልም የሙጃሂዲን አማጺያን ከሶቪየት ህብረት ጦር ሃይል ጋር በገጠሙት ትንንቅ ሊረዳቸው ወስኖ ወደ አፍጋኒስታን በገባ ማግስት በሶቪየቶች የተማረከ አንድ አሜሪካዊ ኮሎኔል የሚደርስበትን ስቃይ እና የኮሎኔሉ ታማኝ ወታደር የነበረ አሜሪካዊ ኮማንዶ አለቃውን ለማስለቀቅ የሚፈጽማቸውን ጀብዱዎች የሚያሳይ ነው። ኮማንዶው (ራምቦ) የሶቪየቶችን የጦር ካምፕ የሚወረው ሙሳ ጋኒ በተባለ አፍጋኒስታናዊ ሙጃሂዲን እና "ሀሚድ" በሚባል የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ ታግዞ ነው።
------
ይህ ፊልም በመላው ዓለም ተወዳጅ ሆኖ ነበር። የቦክስ ኦፊስ ገቢውም 189 ሚሊዮን ዶላር ያህል ነው። አሜሪካዊያን ግን ፊልሙን አልወደዱትም። ብዙ ሐያሲዎች ለፊልሙ የሰጡት ነጥብ ከግማሽ ያነሰ ነው። ፊልሙ በዋናነት የተተቸው "ሰቆቃ እና ስቅየት (violence) ይበዛበታል" በሚል ነው። እኛ በልጅነታችን ፊልሙን ስናይ ግን በድብድቡና በኮማንዶው ጀብዱዎች ተደስተን ለፊልሙ ቆመን አጨብጭበንለታል።


ቻናሉን ለመቀላቀል @lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot ን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!
306 views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 06:00:32 ለፈገግታ! ! የስንት አመት ፍቅረኛዬን የኔ ፍቅር ሽማግሌ ልልክ ነው እላታለሁ ከማን ጋር ተጣልተህ ነው ብላኝ እርፍ

ቻናሉን ለመቀላቀል @lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot ን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!
274 views03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 16:01:49 አስገራሚ እውነታዎች
═══ ═══

የሌሊት ወፍ ብቸኛዋ መብረር የምትችል አጥቢ እንስሳ ስትሆን፤ የእግር አጥንቶቿ ከመቅጠናቸው የተነሳ መብረር እንጂ መራመድ አትችልም። የሌሊት ወፎች ምንጊዜም ከዋሻ ሲወጡ ወደ ግራ ይበራሉ።

ንቦች አምስት ዓይኖች አላቸው። አንዲት ንብ አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ለማዘጋጀት ከ4,000 በላይ አበቦችን መጎብኝት (መቅሰም) አለባት።

ለሚስቱ ታማኝ የሆነ እንስሳ ቀበሮ ብቻ ነው።

ጉንዳኖች ፈፅሞ አይተኙም፣ ሳንባ የላቸውም። ሠራተኛ ጉንዳን እስከ 7 ዓመት ሊኖር ይችላል። ንግሥቷ ግን እስከ 15 ዓመት ልትኖር ትችላለች።

እባብ ዓይኖቹ ቢከደኑም በዓይኖቹ ቆብ ማየት ይችላል።

ኦይስተር (Oyster) የተባለ የዓሳ ዝርያ ከአንዱ ፆታ ወደ ሌላኛው እንዲሁም ወደ ነበረበት ለወሲብ በሚመቸው ፆታውን መቀየር ይችላል።

ቀንድ አውጣ ለ3 ዓመት መተኛት ይችላል።

ሻርክ ብቸኛው የማይታመም እንሰሳ ነው። ምንም ዓይነት በሽታ አያጠቃውም ካንሰርን ጨምሮ። ትልቁ ነጭ ሻርክ ከሶስት ወር በላይ ሳይበላ መጓዝ ይችላል።

ቢራቢሮዎች የሚቀምሱት (taste) በኋላ እግራቸው ነው።

የዱር አይጦች (Rat) በፍጥነት መራባት የሚችሉ ሲሆን በ18 ወራት ብቻ 2 አይጦች 1 ሚሊዮን ዘመዶችን ማፍራት ይችላሉ።

ሰማያዊ ዓሳነባሪ (Blue whale) በመጠን እስካሁን በዓለማችን ከነበሩ እና ካሉ እንሰሳዎች ትልቁ ነው።

ዝሆኖች ከ3ማይል ርቀት ላይ ያለ ውሀ ማሽተት ይችላሉ። አብዛኞቹ ዝሆኖች በክብደት ከሰማያዊ ዓሳነባሪ (Blue whale) ምላስ ያንሳሉ።

አይጥ ከተራበች የራሷን ጅራት ትበላለች።

ዶልፊን ውሃ ውስጥ ከ24 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለ ድምፅ በቀላሉ መስማት ይችላል።

የአህያ ዓይን አቀማመጥ በአንድ ጊዜ አራቱንም እግሮቹን ማየት ያስችሉታል።

በረሮ በርሀብ እስኪሞት ድረስ ለሳምንት ያህል ጭንቅላቱ ተቆርጦ በሕይወት መቆየት ይችላል።

የአሳማ ተፈጥሮ (physical) ወደ ሰማይ ማየት አያስችለውም።

━━━━━━━━
ቻናሉን ለመቀላቀል @lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot ን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!
290 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 11:20:20 በህንድ ማዕዛ ያለዉን ኮንዶም አፍልተዉ የሚጠጡ ወጣቶች ቁጥር መበራከቱ ስጋት ፈጥሯል ተባለ

በህንድ በምዕራባዊ ቤንጋል ዱርጋፑር ከተማ ተማሪዎች ኮንዶም የመጠቀም ሱስ ዉስጥ ወድቀዋል ተብሏል፡፡የተለየ መዓዛ ያለዉ ኮንዶም ሽያጭ በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች በሚያስገርም ሁኔታ ጨምሯል፡፡ በዱርጋፑር ከተማ ቢድሃናጋር፣ ሙቺፓራ እና ቤናቺቲ፣ ሲ ዞን፣ ኤ ዞንን በተባሉ አካባቢዎች በሚገኙ የመድኃኒት መደብሮች ዉስጥ የኮንዶም ሽያጩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተጠቁሟል፡፡

ተማሪዎቹ ኮንዶም በሞቀ ውሃ ውስጥ እየነከሩ ያቆያሉ፤ ከዚያም በኋላ ከ 10 እስከ 12 ሰአታት ድረስ ፈሳሹን እንደሚጠጡ ተነግሯል፡፡መዓዛ ያለዉን ኮንዶም ለመስራት ጥቅም ላይ የሚዉሉ ንጥረ ነገሮችን በሙቅ ውሃ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በማቆየት የአልኮሆል ውህድ እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ድርጊቱ ግን ዘላቂ ሱስ ከማስያዝ ባለፈ ለጤና እጅግ ጎጂ ስር የሰደደ እክል ሊፈጥር እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከሶስት እስከ አራት ፓኬቶች ኮንዶም በአንድ ሱቅ በቀን ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ግን አንድ ጥቅል ሙሉ ኮንዶም በየቀኙ እንደሚሸጡ የመድኃኒት መደብር ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡


ቻናሉን ለመቀላቀል @lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot ን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!
267 views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 04:53:06
እንኳን ደስ አለን !

ኢትዮጵያውያን የበላይ ሆነው አጠናቀዋል !

እጅግ በጣም የሚደንቅ የቡድን ስራ በታየበት የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር በጉዳፍ ፀጋይ አማካኝነት ወርቁ ወደ ኢትዮጵያ ገቢ ተደርጓል።

ነሀስም በዳዊት ስዩም ተገኝቷል።

ከፍተኛውን የቡድን ስራ የሰራችው የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ንግስቷ ለተሰንበት ግደይ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ኬንያ ብር አግኝታለች።

እንኳን ደስ አለን !!

@lehulumbufe
292 viewsedited  01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 04:50:29
274 views01:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 04:49:49
261 views01:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ