Get Mystery Box with random crypto!

ግእዝ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ learngeezethiopia — ግእዝ ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ learngeezethiopia — ግእዝ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @learngeezethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

ግእዝ ሚዲያ የታላቂቱን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥበብና ታሪክ ለትውልድ ለማስቀረትና የኢትዮጵያን ስልጣኔ ፣ ዕውቀት ፣ ስነ ስርዐት እና ጥበብ ለልጆቿ እንዲሁም ለአለም ህዝብ ለማሳየት የተከፈተ ቻናል ነው። ቻናሉ በረከት ያሉ ይዘት ያላቸውን መረሀ ግብሮችን ያካተተ ሲሆን በታሪክ ፣ በአዳዲስ መረጃዎች ፣ በትምህርት ፣ በወቅታዊ እና በተለያዩ ለህይወት ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ይሰራል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-24 17:42:34
642 views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 17:42:25 የዋግ ሕምራ ቤተክርስቲያኖች ይጣራሉ፡፡
#ዕጣን #ዘቢብ #ጧፍ #ሻማ # ከተቻለ ሶላር ላይት! ለዋግኽምራ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት ትብብር እንድታደርጉ በብፁዕ አቡነ በርናባስ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ የሚያስፈልጉ #ዕጣን #ዘቢብ #ጧፍ #ሻማ በማጣት የቅድስት ቤተክርስቲያን ስርዐተ አምልኮ እንዳይስተጓጎል የበኩልዎን ያድርጉ፡፡
በዋግ ሕምራ ሀገረ ስብከት በአሁኑ ጊዜ #600 (፮፻) አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን
ዕጣን የለ?
ዘቢብ የለም?
ጧፍ የለም?
ሻማ የለም?
ክብሪት እንደሰማይ ርቃለች።
#ዘቢብ ዋጋ በኪሎ _250 ብር
#ዕጣን ዋጋ በኪሎ 450 ብር
#ጣፍ ባለ 2 ብር ባለ 5 ብር ባለ 14 ብር
#ሻማ= በባኮ ከ80 ብር ጀምሮ
የተቻለው መጠነኛ በፀሐይ የሚሠራ መብራት/ሶላር ላይት/
በችግር በጨለማ ውስጥ ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት እንድረስላቸው።
ከተቻለም ቅድስት ማርያም አካባቢ እና አራት ኪሎ ማከማቻ ስፍራ አዘጋጅተናል። ካልቻሉ ይደውሉልን መጥተን እንረከባለን፡፡
በገንዘብ መደገፍ ለምትፈልጉ በሀገረ ስብከቱ ገንዘብ ማሰባሰቢያ የባንክ ቁጥር መጠቀም ትችላላለችሁ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000449333717
+251911639619 መጋቤ አእላፍ ፋሲል ታደሰ=
+251944241999 መ/ር ኃይሉ በላይ
አዲስ አበባ
631 views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 12:15:08 https://www.facebook.com/112543957994420/posts/112619877986828/?sfnsn=mo
523 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 15:56:10
752 views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 15:55:48 #አፋልጉኝ
#ከታች_የሚታየው_የካናዳ_ቪዛ

የአትናስያ ሙሉጌታ ታደሰ
የአብ ሥራ ሙሉጌታ ታደሰ

ዛሬ 19/04/2014 ዓ.ም 6:30 አካባቢ ከፍልውሃ ወደ ባልደራስ ራይድን አስቁመው ወደቤት ሲሄዱ ኮሮላ ውስጥ ጥለው የወረዱ ሲሆን የፊታችን ዓርብ ወደ ካናዳ ጉዞ ያላቸው በመሆኑ ያገኛችሁት ከታች በተቀመጡት ስልኮች በአንዱ ደውላቹ ትሰጡን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንለምናለን። አግኝቶ ለሰጠን ወረታውን ከፋይ ነን።

+251911982000 አትናስያ ሙሉጌታ

+251910791521 ሚካኤል ሙሉጌታ

+2510911740841 ሙና ሰዒድ
683 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-25 07:00:15 መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ


የግእዝ ቋንቋ ታሪክና አመጣጥ
ክፍል ፩(1)

ቋንቋ ማለት መግባቢያ ማለት ነው ፡፡ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ ከአንዳንድ ቀደምት የታሪክ ጸሓፊዎችና የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍትን ጽፈው ካስረከቡን ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶችና የቋንቋው ባለቤቶች እንደምንረዳው፦ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ በኢትዮጵያ መነሻ ሊሆነን የሚችለው ክርስቶስ ከመወለዱ ከ800 ዓመት ጀምሮ ነገደ ሴም (የሴም ዘሮች/ወገኖች) ቋንቋቸውን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ሴማዊ ቋንቋ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ቋንቋ ሆነ፡፡ ነገደ ሴም ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ቋንቋቸውን በመግባቢያነት አሳድገው፣ ሥነ ጽሑፋቸውን አስፋፍተው በባቢሎን ፣ በአካድና በአሶር ይኖሩ ነበር፡፡ በኋላ ግን ለሁት ተከፍለው ግማሾቹ ሴማውያን ሰሜንና ምስራቅ እስያን፣ ግማሾቹ ሴማውያን ደግሞ ደቡብ እስያን ይዘው ይኖሩ ነበር፡፡

የሰሜን እስያ ሴማውያን ቋንቋ (የአካድ ቋንቋ)፦ አማራይክ፣ ዕብራይስጥን እና ፊንቄን ሲያስገኝ የደቡብ እስያ ሴማውያን ቋንቋም (አካድ ቋንቋ)፦ ሳባን ግእዝንና የተለያዩ በኢትዮጵያ ውስጥ በመግባቢያነት የምንጠቀምባቸውን ሴማውያን ቋንቋዎች አስግኝቷል፡፡ በደቡብ እስያ ይኖሩ የነበሩ ነገደ ሴም በተለያየ ምክንያት እየፈለሱ ወደ ደቡብ ዐረብ ወደ የመንና ወደ አካባቢዋ መጥተዋል ከዝያም ፈልሰው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአክሱምና በአካባቢዋ ሰፍረው ይዘዋቸው ከመጡት ቋንቋዎቻቸው መካከል በታሪክ ጎልተው የሚታወቁና አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩትና በአሁኑ ሰዓትም በአገልግሎት ላይ የሚገኙት ቋንቋዎች የሳባ እና የግእዝ ቋንቋዎች ናቸው፡፡


ነገደ ሴም(ሴማውያን) ቋንቋዎቻቸውን /ሳባና ግእዝን/ ከነገደ ካም ቋንቋ ጋር አስማምተው በመያዝ ሁሉንም ቋንቋዎች ሲናገሩዋቸው ኖረው ነበር፡፡ በኋላ ግን ሳባና ግእዝ እየተለመዱና እየተስፋፉ እየዳበሩም ከመሄዳቸው የተነሣ የነገደ ካምን ቋንቋ እየዋጡት መጥተው ሁለቱ ሳባ እና ግእዝ ቋንቋዎች ብቻ ሀገራዊ ቋንቋዎች ይሆኑ ጀመር እየቆዩ ግን ሁለቱ (ሳባና ግእዝ) በጣም ተመሳሳይና ተቀራራቢ በመሆናቸው እንደ አንድ ቋንቋ ሆነው ይነገሩ ጀመር፡፡ ይኸም ጽሑፉ (ፊደሉ) በሳባ እንዲጻፍ እና መነጋገሪያ ቋንቋውን ደግሞ በግእዝ እንዲሆን በመደረጉ ነው፡፡ ነገደ ሴም በሳባ ቋንቋቸው ፥ሳባውያን፥ በግእዝ ቋንቋቸው ደግሞ ፥አግአዝያን፥ ተብለው የሚጠሩት ከዚህ መነሻነት ነበር፡፡

ለዚህም መረጃ የሚሆኑን ሳባና ግእዝ ቋንቋዎች ተጽፈውባቸው የሚገኙት ጥንታውያን የኢትዮጵያ ቅርሶች እንደ የአክሱምና የላሊበላ ሐውልቶች በየሐ እና በአዱልስ ወዘተ….. የተለያዩ በድንጋይ ላይ የተቀረጹ ጽሑፎችና ቅርጻ ቅርጾች እስከ አሁን ቆመው የሚገኙ የዚህ ቋሚና ግልጽ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ የሳባና የግእዝ ቋንቋዎች በዚህ ሁኔታ እስከ 324 ዓ.ም. አካባቢ ድረስ አብረው ሲነገሩ ቆይተዋል በኋላ ግን የሳባ ቋንቋ እየተዳከመና በግእዝ ቋንቋ እየተዋጠ ይሄድ ጀመር እንደ ምንም እየተንገዳገደ እስከ 350 ዓ.ም. ቆይቶ ከዚህ በኋላ ከሥነ – ጽሑፍ ከመነጋገሪያነትም ፈጽሞ ቀረ የግእዝ ቋንቋ ግን ከ324 ዓ.ም ጀምሮ ብቸኛ ሀገራዊ ቋንቋ በመሆን እስከ 12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማለትም የአማርኛ ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ ሲያገለግል እንደ ነበር የታሪክ ጸሐፊዎች በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡


ዮም ፈጸምነ ዘይእዜ ትምህርት ሠናይ ሶቤ ይኲን ለኲልኲሙ ፡፡
ይቀጥላል...

#መጀመሪያ #ግእዝ_ታሪክ
678 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 11:02:04 ከተማ ውስጥ ያለንን ጨርሰን በቆላውም በደጋውም ጥሬ ልመና ወደ ገጠሩ ተሠማርተን ነው መከላከያ የደረሰው :: የእኔን መኪና ወስደዋታል :: እንኳን ወሰዱ አይቆጨኝም :: ይህ ሕዝብ ለዚህ መብቃቱ ይበቃኛል ። - ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ
[ዳግማዊ ሙሴ]
ቀድመው እንዲህ ብለው ነበር|ከታንክ ፊት የቆሙት ታላቅ አባት|


593 viewsedited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 10:12:57 [በፍጥነት ተመልከቱት]
ተስፋው መስከረም
|2014 ዓ.ም


961 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-20 09:44:57
Sponsor
1.1K views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-11 13:12:33 ገዳማት ተደፈሩ
አባቶች ተዋረዱ
ክርስትያኖች ረገፉ


1.3K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ