Get Mystery Box with random crypto!

#የቅኔ #ጉባኤ #ቤት ባህር ዳር የሚገኘው ታላቁ የቅኔ ጉባኤ ቤት ሊሠራ የሚከተለውን ዓይነት ዲዛይ | መሠረተ ግእዝ

#የቅኔ #ጉባኤ #ቤት
ባህር ዳር የሚገኘው ታላቁ የቅኔ ጉባኤ ቤት ሊሠራ የሚከተለውን ዓይነት ዲዛይን ወጥቶለታል፡፡ የጉባኤ ቤት ቤት አሠራር ትውፊትን የያዘ ድንቅ ዲዛይን ነው፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ለትርጓሜም ለሌሎች ትምህርቶችም ዋናው ቁልፍ ቅኔ ነው፡፡ የግእዝ ትምህርት በጥልቀት የሚሰጠው ቅኔ ቤት ነው፡፡ ግእዝ ደግሞ ብዙ ጥንታውያን መጻሕፍት የተጻፉበት ቋንቋ ነው፡፡ ሊቃውንቱ በቅኔያቸው የእግዚአብሔርን ቸርነቱን፣ መግቦቱን፣ ሁሉን ቻይነቱን፣ ፈታሒነቱን፣ ይቅር ባይነቱን፣ አንድነቱን፣ ሦስትነቱን፣ ጌትነቱን፣ ዘለዓለማዊነቱን በአማረ የቋንቋ አሰካክ በሰምና ወርቅ ይገልጡበታል፡፡ የቅዱሳንን አማላጅነት የሰማዕታትን መንፈሳዊ ቆራጥነት የመላእክትን ተራዳኢነት በቅኔያቸው ይገልጹታል፡፡ በቅኔያቸው ክፉዎችን ይገሥጹበታል፡፡ ምእመናንን ይመክሩበታል፡፡
፡፡
በአጭሩ ለመግለጽ ቅኔ መንፈሳዊ ፍልስፍና ነው፡፡ ቀድሞማ መሳፍንቱ መኳንንቱ ወይዛዝርቱ ሁሉ ባለቅኔ ነበሩ፡፡ የዚችን ዓለም ከንቱነት በቅኔያቸው ይገልጡት ነበር፡፡ የእነ ተዋነይ መንፈሳዊ ፍልስፍናኮ ቅኔ ነው፡፡ የቅኔ ትምህርት በአሁኑ ሰዓት በስፋት የሚሰጥበት ጉባኤ ደግሞ የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ልጅ የሆኑት የየኔታ ቅዱስ ያሬድ ጉባኤ ቤት ነው፡፡ ይህን ጉባኤ ቤት ለመሠራት ወደ 200 ሚልየን ብር ይፈጃል ተብሏል፡፡ ስለዚህ ሁሉም በችሎታው ማገዝ አለበት፡፡ ለማገዝ የምትፈልጉ ከስር በተገለጡት የአካውንት ቁጥሮች መርዳት ትችላላችሁ፡፡
፡፡
አምላከ ሊቃውንት እግዚአብሔር ቤተጉባኤን ይጠብቅልን፡፡