Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis

የቴሌግራም ቻናል አርማ kumis4274 — ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis
የቴሌግራም ቻናል አርማ kumis4274 — ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis
የሰርጥ አድራሻ: @kumis4274
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.10K
የሰርጥ መግለጫ

Hello guy's Welcome to Sweet channel join and shere
Funs❤❤
Memes❤❤❤
Friends❤❤❤
self roast ❤❤❤
To just offcial&cross @Nizreti ❤❤❤

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-10 20:30:39 አስተማሪ፦ አንተ ምን ሆነህ ነው ያረፈድከው
:
:
Bro፦ አንድ ሰውዬ 100 ብር ጠፍቶት ነው::
:
አስተማሪ፦ ታዲያ አንተ ብሩን
ስታፈላልገው ነበር?
ሲለው ያለውን የምር አልቻልኩም
:
:
:
bro ፦ አይ! ቲቸር እስካሁን በእግሬ ብሩ ላይ ቆሜበት ነበር እስከሚሄድ እየጠበኩ ለዛ ነው ።


@kumis4274
1.2K viewsYOU, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:30:38 እውቀት ነክ
አዬ - አባዬ መሬት ለምንድን ነው ክብ የሆነችው
°
አባት - እኔንጃ ልጄ
°
አዬ - ለምንድን ነው ቀን እና ለሊት የኖረው
°
አባት - እኔንጃ ልጄ
°
አዬ - አየር ላይ ለምንድን ነው መብረር ማንችለው
°
አባት - እኔንጃ ልጄ
°
አዬ - ለምን......
ብሎ ሳይጨርስ እናት በመሀል ትገባና
"ምን አለ አባትክን ባታስጨንቀው" ስትል

አባት - ተይው እንጂ ይጠይቅ
ካልጠየቀ ምን ያውቃል



JOIN & SHERR
@kumis4274
@kumis4274
1.2K viewsYOU, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:49:49 አታውቅም

'"""""""""""""


በሰፈሯ በኩል ስንት ጊዜ እንዳለፍኩ ፣
እሷን ለማናገር እንደተሸማቀቅኩ ፣
በሀሳቤ መሀል እንዳመላለስኳት ፣
በማየው ሁሉ ላይ ሺ ጊዜ እንደሳልኳት ።

አታውቅም

እሷን በማስታወስ ቀኔ እንደሚጀምር ፣
ባገኛት እያልኩኝ ሌቱን እንደማድር ፣
ቀኑ እንደሚረዝም ሳላያት ከዋልኩኝ ፣
ልነግራት አስቤ ስንቴ እንደፈራሁኝ ።

አታውቅም
አታውቅም
አታውቅም ፣

ምናልባት አንድ ቀን
እነግራት ይሆናል በሚል ተስፋ እንደቆምኩ ፣
ናፍቆቷን ስመገብ እህል ሁሉ እንዳቆምኩ ፣
መንገድ ስንገናኝ
ብርድ እንዳለበት ሰው አካሌ እንደሚርድ ፣
ይሄን ሁሉ ተዐምር አታውቅም የኔ ውድ ።

አታውቅም አታውቅም

እንደተሸከምኩኝ የሷን ፍቅር ስቃይ ፣
ሁሌ ተደብቄ ስትስቅ እንደማይ ፣
በፍቅሯ ታምሜ ከህመሜ አልድንም ፣
ምን ብላ ታክመኝ ህመሜን አታውቅም ።

@kumis4274
@kumis4274
1.5K viewsH.P.B, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:19:43
እናትን
........


አይጉደል ጎዳዋ፤
አይሸርከት እግሯ፤
እንዳታለቅስ ከፍቷት፤
ማጣት ቢያገኛት፤
ሃዘን እንዳይገባት፤
ዳቦ አይ ራባት፤


ረጋጭሽ መንደር፡
መጥቼ ብዋቀስ፡ ጩኸቴን ባገነው፤
እናትን አይክፋት፡
እያልኩኝ ብማፀን፡ የሚሰማኝ ማነው??



ይሄ የሚታየኝ፡
ከፊት ለፊቴ ላይ ፡ስጋሽ የደቀቀው፤
እዚ ያደረሰሽን፡
የልብሽን ብርታት፡ መንገድሽን ባውቀው፤
እናትነትሽን ፡ ገብቶኝ እንዳፈቅረው።


ባይታደል ጎጆ፡
እንዲገባት ባትኖር፡ ቢያስድሃትም ልፋት፤
ተደስታ ትኑር፡
በምንም በማንም፡ እናትን አይክፋት።




Semir ami

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን



➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us  @kumis4274
2.3K viewsH.P.B, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:56:31

H.P.B ዛሬ ልደቴ ነው


@kumis4274
@kumis4274
5.2K viewsONE DEY, 03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:54:58 Happy Birthday

#ዛሬ ልደቴ ነው
@Emarsen12


@kumis4274
@kumis4274
4.4K viewsONE DEY, 03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 23:09:01 . ይነበብ

አንድ ሰው በጣም የሚወዳትን ቆንጆ ልጃገረድ አገባ። ግን ልጅቷ የቆዳ በሽታ ያዛትና ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች። ይህን የተመለከተው ባሏ ለጉብኝት ራቅ ወደላ ስፍራ ሄደና በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጥሞት ዓይኑን አጣ። ሆኖም የጋብቻ ህይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ እናም ቀናት እያለፉ ውበቷን ደረጃ በደረጃ አጣች። ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳራቸው ሕይወት ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡ እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡ ይቺ በጣም የሚወዳት ሚስቱ አንድ ቀን በድንገት ሞተች። ድንገት በመሞቷ ታላቅ ሀዘን ተሰማው። ሀዘን ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ። በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች “አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? በእነዚህ ሁሉ ቀናት ሚስቱ ነበር የምትረዳው፡፡” ብለው ይወያዩ ነበር፡፡ሰውየውም

“አይነስውር አይደለሁም ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነበር፡፡ ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እነዳልሆነ እንዲሰማት ፈለግሁ ስለዚህ እንደማላይ ነገርኳት።እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች።እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው።" አላቸው

ለካ ባለማየት ውስጥ ድንቅ ማየት አለ፤ ፍቅር የደስታ እና የሰላም ምንጭ ነው።

#ፍቅርን_በፍቅር_እንመልስ
#JOIN_US
@kumis4274
2.0K viewsONE DEY, 20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:20:07 ድንግል ውበት
@kumis4274
ጫማ ካልተጫማው ከባዶ እግሮቿ
ኩልን ካልቀመሰው ከነጩ አይኖቿ
ልብስን ካለመደው ከእርቃን ገላዋ
በኢቫንጋዲ ምሽት ያምራል ጭፈራዋ

ከቡስካው አለም ውስጥ ድብቅ ሚስጥር አለ
በተፈጥሮ ውብት እንደተከለለ
በህግና ባህል እራሱን ያኖረ
የሐመር ምድር ላይ ድንቅ ህዝብ ተፈጠረ
በአለም የሌለ ቀድሞም ያልተዳሰሰ
አለም ተበሰረ
ያልተበረዘ አለም ክፋት ያልጎበኘው
በግልጽ አስተሳሰብ ፍቅር የሚዳኘው
ህግ ስልጣን የለው ባህል ያቆራኘው
የእውነት ፍትህ ካለው
ግን ግን ከቆመው ምሶሶ ካንጋጠጡ ህንጻዎች
ጨለማን ወሽተውት ከቆሙት መብራቶች
ከአለሙ አለም ከከተማው ድምቀት
ይሻላል የቡስካው ያ የጨረቃ ውበት

ውበት ግን ምንድ ነው ?
ውበት ማንነት ነው ጣፋጭ ህልውና
ባጭበርባሪ አለም ድንቅ ስብእና
አስቀምጦ ማለፍ ነው
ለተራማጆች ግን ውበት ያልገባቸው
እርቃንን ሸፍኖ እርቃን ማሳየት ነው
ባዶ ማንነትን ገልጦ ከማሳየት
ይሻለን ነበረ እነደ ሐመሯ ወጣት
በአንገት ክታብ ድምቀት በእርቃን መታየት

@kumis4274
1.4K viewsONE DEY, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 09:22:55 አይደለም ምኞቴ


አይደለም ምኞቴ
ለምለም አንገትሽ ላይ ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ ጭንሽ መሀል መስጠም
አይደለም ምኞቴ
ከንፈርሽን ማለብ
ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ ገላዬን መቀለብ
ደረትሽን ማለም
ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም
ምኞቴን ልንገርሽ?
ካለሺበት ቦታ ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ ትዝታ መጋራት
የጨለመ ፊቴን ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ ዝምታሽን መስማት
ይህ ነው ምኞቴ!!!

@kumis4274
@kumis4274
1.7K viewsYOU, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:46:18 አንዳንድ ጊዜ መናገር የማይገባህን ቃል ትናገራለህ፡፡ ማድርግ የማይጠበቅብህን ነገር ታደርጋለህ፡፡ ምንም ማድረግ አትችልም ሰው ነህ፡፡ ስትኖር ትሳሳታለህ፡፡ ከስህተትህ ትማራለህ፡፡ ስትማር ታድጋለህ፡፡ የተሻልክ ሰውም ትሆናለህ፡፡ይህ ሰው የመሆን ሂደት ነው፡፡ መሳሳት፣ መማርና ማደግ!

@kumis4274
1.9K viewsYOU, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ