Get Mystery Box with random crypto!

. አውቃለሁ... ግዜውን ጠብቆ፣ እንደ ጠዋት ጤዛ ውበትሽ ይረግፋል መልክሽም እንደ ቀለድ፣ ልክ | ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis

.
አውቃለሁ...

ግዜውን ጠብቆ፣
እንደ ጠዋት ጤዛ ውበትሽ ይረግፋል
መልክሽም እንደ ቀለድ፣
ልክ እንደ ደመና በድንገት ይጠፋል
አውቃለሁ
ታውቂያለሽ~ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡

ሁሉም ነገር ይለፍ
ውበትሽም ይርገፍ~እኔ ምን አገባኝ
ከስጋሽ ጋ ሳይሆን፣
ከነብስሽ ጋራ ነው ፍቅር የተጣባኝ፡፡

ስጋማ አፈሩ፣
ቤቱ መቃብሩ~ ገርጅፎ ቢጃጅም
ወድሻለሁ ውዴ ነብስሽ አታረጅም።

@kumis4274