Get Mystery Box with random crypto!

#አስቸኳይ_ማሳሰቢያ ለ2014 የትም/ት ዘመን 12ኛ ክፍል ማጠቃለያ (ሀገር አቀፍ ) ፈተና ተፈታ | ቀ.ኃ.ሥ meme

#አስቸኳይ_ማሳሰቢያ

ለ2014 የትም/ት ዘመን 12ኛ ክፍል ማጠቃለያ (ሀገር አቀፍ ) ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ

በ2014 ዓ.ም የመደበኛም ይሁን የግል ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ምዝገባ ሂደት በሁለት(በዳርማሎግ/online/ እና በ"DRS"/በወረቀት) አማራጮች እየመዘገብን መቆየታችን ይታወሳል።

ሆኖም ግን ጥቂት ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የአንደኛውን አማራጭ ምዝገባ ብቻ በመመዝገብ ቀሪውን እንደዘለሉት ከመዋቅሮች የሚመጡ መረጃዎች ያሳያሉ ፤ ስለሆነም ማንኛውም ተማሪ የ2014 12ኛ ክፍል ፈተና መፈተን የሚችለው ሁለቱንም የምዝገባ አማራጮችን አሟልቶ ሲጠቀም ብቻ እነደሆነ በአፅንኦት እየገለፅን ፤ የDRS ምዝገባ ያልተመዘገባችሁ በሙሉ ቀሪ ሁለት ቀናትን (ከሀምሌ 04 እስከ 05/11/2014) በመጠቀም ቀደም ስል በተመዘገባችሁበት ትምህርት ቤት በአካል በመቅረብ አሰፈላጊውን እንድታሟሉ እናሳስባለን።

ትምህርት ሚኒስቴር


@kokebe_tsibah_meme