Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ ምስጋና በክራር

የቴሌግራም ቻናል አርማ kirarlimmd — ኦርቶዶክሳዊ ምስጋና በክራር
የቴሌግራም ቻናል አርማ kirarlimmd — ኦርቶዶክሳዊ ምስጋና በክራር
የሰርጥ አድራሻ: @kirarlimmd
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 987
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል በክራር መዝሙሮች እና ልምምዶች ሚለቀቅበት ነው

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-16 21:02:25 መሰንቆ ሃይማኖት ምሳሌ ነው
በመሰንቆ ጫፍ ላይ የንፃነታችን ዓርማ የደኅንነታን ምልክት የሆነውን መስቀል እናገናለንስለዚህም በመሰንቆ መዝሙር በዘመርን ቁጥር በቀራን ተፈጸመልንን ውለታ ተከፈለልንን ካሳ በማሰብ ፈጣሪያችንን በፍጹም ልባችን እናመሰግነዋለን፡፡ ፍቅሩንም እያሰብን ዘወትር በኃጢአታችን እንፀፀጻለን፡፡ የመሰንቆ መምቻው የኪዳነ ኖኅ ምሳሌ ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ለኖኅ ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ ላያጠፋት ቃል የገባለት ምሳሌ ነው፡፡ዘፍ 9፡11-20 ይህም የመሰንቆ መምቻ ቀስተ ደመና ይመስላል፡፡ አባታችን ኖኅ ከጥፋት ውኃ የዳነበት መርከብ ደግሞ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነው፡፡ “ኖኅ ከጥፋት ውኃ የዳነብሽ መርከብ አንቺ ነሽ” በማለት አባ ሕርያቆስ በቀረዳሴ ማርያም ቁ 31 እንደተናገረው፡፡ ስለዚህ በመሰንቆ ስንዘምር ለአባታችን ለኖኅ በገባህለት ቃል ኪዳን መሠረት ኃጢአታችንን ተመልክተህ አታትፋን ማረን ብለን መለመናችን ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አባታችን ኖኅን ከጥፋት ውኃ ያዳንሽ አማናዊቷ ሐመር /መርከብ/ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የኃ ጢአት ማዕበል ጎልብቶ የፈተናውም ማዕበል በርትቶ በክህደት በጥርጥር ማዕበል እንዳንሰጥም ዛሬም ለእኛ ፈጥነሽ ድረሽልን በማለት እመቤታችንን መለመናችን ነው፡፡
ዋሽንት፡- ከቀርከሃ፣ ከሸንበቆ ፣ከብረት የሚሠራ የመዝሙር መሣሪያ ሲሆን በመጽሀፍ ቅዱስ ትን.ዳን 3፡5፤10 1ኛ ቆሮ 14፡7 ላይ ተጠቅሶ እናገናለን፡፡ ዋሽንት የወንጌል ምሳሌ ነው ፡፡ ከዋሽንት የሚወጣው ድምጽ መልካም እንደሆነ ልቡናን እንደሚመስጥ ደስ እንደሚያሰኝ ሁሉ ወንጌልም እግዚአብሔር ንጉሥ ነው ዲያቢሎሽ ተሻረ የሚለውን ደስ ሚያሰኝ የምሥራች ድምፅ ታሰማለች፡፡
መለከት፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ ለመዝሙር አገልግሎት ይጠቀምባቸው ከነበሩት የመዝሙር መሣሪያዎች አንዱ እንደነበር ከሊቀ ነቢያት ሙሴ የአገልግሎት ዘመን በፊት አገልግሎት ላይ መዋሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጻል ዘፍ 4፡21 በተጨማሪም በብዙ ሥፍራዎች በብዛት ተተቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ኢያሰ 6፡20፤ 2ኛ ዜና 15፡28፤መዝ80፡3
መለከት በትንሣኤ ዘጉባኤ ጌታን መምጣት ያበስራል፡፡ ማቴ 24፡31 1ኛ ተሰ 4፡16 መለከት ሰዎችን ለግዳጅ ያዘጋጃል፡፡ በጥንት ጊዜ ሰዎችን ለጦርነት ሲጠሩ ነጋሪት ይጎሰማል መለከት ይነፋል፡፡ በአጠቃላ መለከት ሰዎችን ለግዳጅ ዝግጁ እንድንሆን ያስጠነቅቃል፡፡ ሕዝ 33፡1-6 መዝሙር ስንዘምር በመለከት መዘመራችን በጌታ ዳግም ምፅአት በትንሣኤ ዘጉባኤ የምናገኘውን አዲስ ህወት በማሰብ ራሳችንን ከወዲሁ በንሥሐ እንድናዘጋጅ ሲረዳን በዕለተ ምጽአት ዕጣ ተርታችን ጽዋ ፈንጻችን ከቶ ከየትናው ወገን ይሆን ? በማለት ራሳችንን ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድንዘጋጅ ያሳስበናል፡፡
እንዚራ፡- በመጽሐፍ ቅዱስ በት ኢሣ 5፡12 ላይ የተጠቀሰ የመዝሙር መሣሪያ ሲሆን አሁን ግን ስለጠፋ በአገልግሎት ላይ ሲውል ባይታይም ቅዱስ ሲኖዶስ ግን ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበላቸው የዜማ መሣሪያዎች ውስጥ አንዱ እንዲገልግል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
1.4K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-16 21:02:24 የጸናጽሉን ጫፍ ስንመለከት የቀስተ ደመና ቅርጽ ያለው ሆኖ ከሁለቱ ብረቶች/የግራና የቀኝ/ ጋር የተያያዘ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህ የቀስተ ደመና ቅርጽ ያለው ብረት ልዑል እግዚአብሔር ለኖኅ ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ እንደማያጠፋት ቃል ሲገባለት የሰጠው የቀስተ ደመና የቃል ኪዳን ምልክት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ድምፅ የሚያሰሙት የብረት ቅጠሎች ደግሞ የፍጥረተ ዓለም ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በጸናጽል መዘመራችን አምላካችን ለኖኅ የገባህለትን ቃል ኪዳን አስበህ ማረን ዘወትር ይቅርታህና ቸርነትህ ፈጥኖ ይደረግልን ብለን መለመናችን ነው፡፡ አንድም ጸናጽል አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየው የወርቅ መሰላል ምሳሌ ነው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት ሰማይና ምድርን፣ ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች አማናዊት ሰዋሰወ ወርቅ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ “ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየሽ የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ” እንዲሁም “በካህን አሮን ልብስ ላይ ያለሽ ጸናጽል አንቺ ነሽ” እንዳለ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ቁ. 33፡፡
ስለዚህ ጸናጽል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ሆኖ ይተረጎማል፡፡ በጸናጽሉ ግራና ቀኝ የሚገኙት ጋድሞች የጸናጽሉ መውጫና መውረጃ ምልክቶች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናቸው፡፡ በጋድሞቹ ላይ ተንጠልጥለው የሚታዩት ቅጠሎች በመሰላሉ ላይ ሲወጡ ሲወርዱ የነበሩት የቅዱሳን መላእክት ምሳሌ ናቸው፡፡ የግራና የቀኝ ዘንጎች /ቋሚዎች/ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ እንዲሁም የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ /ባልንጀራን እንደራስ የመውደድ/ የሚሉት ሕግጋት ምሳሌ ሲሆኑ የተንጠለጠሉት ቅጠሎች ደግሞ የአዋልድ መጻሕፍት ምሳሌዎች ናቸው፡፡
የቅጠሎቹ ብዛት ዐምስት መሆናቸው የዐምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ቅጠሎቹ ከታች ሁለት መሆናቸው የጌታ ሁለቱ ልደታት ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ያለ አባት መወለዱን የሚገልጹ ሲሆን ከላይ ያሉት ሦስት መሆናቸው የእግዚአብሔርን ልዩ ሦስትነት ያስረዳሉ:: መያዣው አንድ መሆኑን በመለኮት፣ በአገዛዝ፣ በሥልጣን አንድ አምላክ መሆኑን ያስረዳናል፡፡ በጸናጽል መዘመራችን አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በምሳሌ ያየሽ አማናዊቷ የወርቅ መሰላል እመቤታቸን ድንግል ማርያም ሆይ ልመናችንን ወደ ልጅሽ አሳርጊልን ብለን መለመናችን ነው፡፡
ሐ. የመቋሚያ ትዕምርትነት/ምሳሌነት/
መቋሚያ፡- ቆመ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጒሙ ተነሣ፣ ቀጥ አለ ማለት ነው፡፡ ከጫፉ የመስቀል ቅርጽ ያለው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በረጅም የሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ለምሳሌ እንደ ቅዳሴ ባለ ሥርዓት ላይ ቀሳውስትም ሆኑ ምእመናን ለድጋፍ ይገለገሉበታል፡፡
መቋሚያ እግዚአብሔር ለአዳም ተስፋ አድርጎ የሰጠው የመስቀል ምሳሌ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲናችንም መቋሚያ የሚያዘው የክርስቶስን መከራ ለማሰብ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በጐጃም ክፍለ ሀገር መሬትዋፋ በምትባል ሥፍራ ይኖሩ የነበሩ መምህር ዐፅቀ ድንግል የሚባሉ የዐፄ ልብነ ድንግል ወንድም መቋሚያ መያዝ የክርስቶስን መከራ ማሰብ መሆኑን አምነው በተደገፉት ቁጥር እንዲወጋቸውና የክርስቶስን መከራውን እንዲያስታውሱ15 እሾህ የፈሰሰበት መቋሚያ አሠርተው ነበር ይባላል፡፡ ይህንንም አርአያ አድርገው በሸዋ ክፍለ ሀገር በመንዝ የነበሩ መነኮሳት እንደዚያው እያደረጉ ይሠሩበት ነበር እየተባለ ይተረካል፡፡ የክርስቶን መከራ በማሰብ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ እንደሚዳንበት አምነው ስሙን ተአምኖ ብለውታል፡፡
መቋሚያ አስቀድሞ በብሉይ ዘመን የነበረ ቢሆንም (ዘፀ 4፡2) አባ እንጦንስና ቅዱስ ያሬድ በማኅሌትና በጸሎት ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲውል አድርገዋል፡፡ ይህንም ያደረጉበት ምክንያት ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ትእምርተ መስቀል ያለበትን በትሩን በፊቱ አቁሞ ይሰግድና ይጸልይ እንደነበር አስበው ነው፡፡ ዕብ 11:20-21 ሙሴ ባሕረ ኤርትራን የከፈለበት በትርም የመስቀል ምሳሌ ነው፡፡ ሙሴ የጌታ፣ ግብፅ የሲዖል፣ ባሕረ ኤርትራ የገሐነመ እሳት፣ የሙሴ በትር የመስቀል ምሳሌ ሆነው ይተረጐማሉ፡፡
መቋሚያ ርዝመቱ አንድ ሜትር ተኩል ወይም ከዚያ በላይ ወይም በታች እንደተገልጋዩ ቁመት ሊሆን ይችላል፡፡ የመቋሚያ ራስ ወይም መጨበጫ (ዘንጉ) ራሱ ከዕንጨት፣ ከብረት፣ ከነሐስ፣ ከብር፣ ከወርቅ ሌላው ከዕንጨት ሆኖ ሊሠራ ይችላል፡፡ አሠራሩ የበግ ቀንድ ቅርጽ መሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ኀጢአት የሚያስተሠርይ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን ይገልጻል፡፡መቋሚያ በማኅሌት ጊዜ በካህናት እጅ በሚውልበት ጊዜ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ ይኸውም ብቸኛ መሣሪያ ሆኖ ያለ ከበሮ እና ያለ ጸናጽል በዝማሜ ብቻ ያገለግላል፡፡ እንዲሁም ከጸናጽልና ከከበሮ ጋር በመዋሐድ በአጽሕሶ /በሽብሸባ/ ጊዜ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ መዘምራን በአገልግሎት ላይ መቋሚያቸውን በትከሻቸው መሸከማቸው ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ሲል መስቀል መሸከሙን ለማጠየቅ ነው፡፡
በገና ፡- በገነ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን ነዘረ፣መታ፣ደረደረ ማለት ነው፡፡ በገና የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጣሪውን ያመሰግንበት ከነበሩት የመዝሙር መሣሪያዎች አንዱ ነው፡፡ ዘፍ 4፡21 በገና የእግዚአብሄር በመሆኑ ሰጪውም እርሱ ከመሆኑ በተጨማሪ በሰማይም አለ፡፡ ከሞትንም በኋላ እንኳን በትነሣኤ ዘጉባኤ እናገነዋለን፡፡ “በእሳት ተቀቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን ኤሁ በአውሬውና በምስሉም ቁጥር ድል ነስተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጨ ቆ ላይ ሲቆሙ አየሁ” በማለት ቅዱስ ዮሐንስ ገልጾታል ፡፡ ዮሐ ራዕይ 15፡2
በገና 10 አውታር (የጅማት ክሮች) አሉት፡፡ አሥር መሆናቸው የአሠርቱ ትዕዛዛት ምሳሌ ነው፡፡ ሁለቱ ቋሚዎች የብሉይና የሐዲስ ኪዳን እንዲሁም የፍቅረ ቢጽ (ወንድምን መውደድ) እና ፍቅረ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን የመውደድ) ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ከላይ በአንድ መታሠራቸው ሁለቱ ኪዳናት በአንድ መጽናታቸውን ያስረዳሉ፡፡ ሳጥኑ የታቦት እንዲሁም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነው፡፡ ብርኩማው የደብረ ሲና ምሳሌ ነው፡፡ ድምፁ የወልደ አምላክ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡
መሰንቆ ፡- ሥርወ ቃሉ ሰንቀው ሰነቀ አስጮኸ ፣ከረከረ ካለው ግሥ ወጣ ነው፡፡ በመጽሀፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች ተተቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ኢዮ 21፡12 መሰንቆ
መሰንቆ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነው
“የዳዊት መሰንቆ አንጪ ነሽ” እንዳለ አባ ህርያቆስ በቅዳሴ ማርያም መሰንቆ ክር በእጣን ካልታሸ ድምፅ አይሰትም፡፡ እጣን የጌታ ምሳሌ ፣ክር የእመቤታችን ድምፁ የምስጋናዋ ፣ ክሩ በእጣን ታሽቶ ድምጽ ለመስጠት እንደበቃ እመቤታችንም ጌታን በመውለዷ ወላዲተ አምላክ ለመባል በቅታለች፡፡ ክሩ በእጣን ታሽቶ የተለያየ ድምጽ እንደሚሰጥ ሁሉ እመቤታችንም የጌታ እናት በመሆኗ “ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል” ሉቃ 1፡48 ብላ እንደተናገረችው የተለያዩ ሊቃውንት በተለያየ ምስጋና አመስግነዋታል፡፡
1.2K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-16 21:02:24 የዜማ መሣሪያዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ
በታደሰ ዓለማየሁ
በቤተ ክርስቲያናችን የሚገኙ የዜማ መሣሪያዎች ልክ እንደ ዜማው ትምህርትም ይሰጣሉ ፡፡ ከመንፈሳዊ ዐላማ የሚያወጡ ፍጹም ዓለማዊ የሆኑ ሥጋን አስደስተው ነፍስን የሚያደክሙ መሣሪያችም አሉ፡፡ ከቤተ ክርስቲያናችን ውጪ የሆኑ የዘፈን መሣሪያዎች አሠራራቸውም ለዘፈን አገልግሎት በመሆኑ መንፈሳዊ ትርጒምና በረከት የላቸውም ፡፡ የዘፈኑ ዜማ ደራስያኑም የዓለም ሰዎች በመሆናቸው የድርሰቱ ዓላማም የሰውን ሥጋዊ ስሜት ማርካት ብቻ በመሆኑ ለመንፈሳዊ ሕይወት ጥማት ማርኪያ ሊውሉ አይችሉም ፡፡
በስመ ቴክኖሎጂ ጠቀሜታ አንጻር የመጣ ሁሉ በቤተ ክርስቲያናችን ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ስለሆነም ቤተ ክርስቲያናችን ከመሠረተ እምነት /ዶግማ/፣ ቀኖናና ትውፊት አንጻር ትገመግማለች፣ ትመረምራለች፣ እምነቷን፣ ሥርዐቷን፣ ትውፊቷን፣ የሚያጠናክረውን እየመረጠች ትጠቀምበታለች፡፡ ለምሳሌ ጥላ፣ ምንጣፍ፣ መጋረጃ ወ.ዘ.ተ ከየዐይነታቸው እየመረጠች ትጠቀምበታለች፡፡ የዓለማዊ ነገር ማስታወቂያ ያለበትን ጥላ፣ ከረንቡላ እየተጫወቱ የሚመስሉ ውሾች ሥዕል ያለበትን ምንጣፍ መጋረጃ አትቀበልም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የዜማ መሣሪዎችን ትመርጣለች ፡፡ሥጋን የሚያስደስተውንና ነፍስን የሚያሳዝነውን፣ አምላክን የሚያስረሳውን ጭፈራና ሁካታን የሚያባብሰውን መሣሪያ ፈጽሞ አትቀበልም፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ የአባቶቻችንን ቃል በመያዝ እነ ጠቢቡ ሰሎሞን በጥበባቸው ያልቀየሩትን በቅድስና ያጸኑትን መያዝ እንዳለብን ስታስረዳን “አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍርስ” ምሳሌ 22፡28 እያለች በዚህ በዚህ አመስግኑ ተጠቀሙ ብላ ሥርዓት ሠርታ፣ ሕግ አውጥታ ሰጥታናለች፡፡ ለቤተ ክርስቲያን አለመታዘዝ ራስዋ ለሆነው ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ከርስቶቶስ አለመታዘዝ ነውና ልናከብራት ይገባል፡፡ ›?ô 5፡24 'qL 1፡24
ዛሬ በግልጽ እንደምናየው መናፍቃን አምርረው ይጠሉት እንዳልነበረ ሁሉ ከበሮውን፣ መቋሚያውን ጸናጽሉን፣ ሽብሸባውን በየአዳራሹ ለማስገባት በሚታገሉበት ወቅት የእነርሱን የዘፈን መሣሪያ ተቀብለን የእኛን እንድናጣ አያስፈልግም፡፡ “ክብርህን ለባዕድ አትስጥ የሚሻልህንም ለሌላ ወገን አትስጥ” ተብሏል፡፡ መጽ.ባሮክ 4፡3
የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ መሣሪያዎች እጅግ መንፈሳዊና ራስን በንስሐ በማንጻት ነፍስን በማርካትና ሥጋዊ ስሜትን በመቆጣጠር በተመስጦ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ እግዚአብሔር ለእኛ ለሰው ልጆች የሰጠን ጸጋዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም የዜማ መሣሪያዎች ፍጹም ሰማያዊውን ሥርዓት የሚያመለክቱንና የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ በዐይነ ሕሊናችን እያየን ወደ ንስሐና እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ የሚያደርሱን ከመሆናቸውም ሌላ ጥልቅ በሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጒም የተሞሉና ምሳሌነት ያላቸው ስለሆኑ ለሚያያቸውም ሆነ ለሚጠቀምባቸው መንፈሳዊ ትምህርት በመስጠት አዕምሮን በመመገባቸው አንደበት የሌላቸው ሰባክያን ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ቤተ ክርስያናችን ራስ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 2 ቀን 1986 ዓ.ም እንድንጠቀምባቸው የደነገገልን የዜማ መሣሪያዎች ከበሮ፣ ጸናጽል.፣መቋሚያ፣ በገና፣ መሰንቆ፣ ዋሽንት፣ መለከት እና እንዚራ ሲሆኑ እነዚህንም በዝርዝር እንመለከታለን፡፡
ሀ. የከበሮ ትዕምርትነት /ምሳሌነት/
ከበሮ ፡- የሚሠራው ከዕንጨት ወይም ከብርና ከከብት ቆዳ ሆኖ ዙሪያውን ሱቲ (ጨርቅ) ይለብስና ላዩ ላይ ጥልፍልፍ ጠፍር ይታሠራል፡፡ የከበሮው አፍ ከአንዱ በኩል ሰፋ ያለ ሆኖ ከተቃራኒው በኩል በጣም ጠበብ ብሎ ሞላላ ቅርጽ አለው፡፡ በውስጡ ጠጠሮች አሉበት፡፡ ከበሮ ስፋትና ክብደት ካላቸው የዜማ መሣሪዎች አንዱ ነው፡፡ ከበሮ አመታቱ ቁጭ ብሎ (በቁምና በዐቢይ መረግድ ጊዜ) ወይም ቆመው (በሽብሸባ ጊዜ) ወይም ወዲህና ወዲያ እየተመላለሱ ትከሻቸው ላይ በማንገት ነው፡፡ ጊዜን እየጠበቁ በሁለት እጅ ማለትም በቀኝ እጅ ሰፊውን፣ በግራ እጅ ጠባቡን ተመትቶ ወዲያው በማከታተል ቀኙ ይመታል ፡፡ እንደየዜማ አገባብ ጠባቡ ክፍል ሁለት ጊዜ ወይም አንድ ጊዜ ከተመታ በኋላ ሰፊው አፍ ይመታል፡፡ ሰፊው ክፍል በሙሉ መዳፍ የሚመታ ሲሆን ጠባቡ ክፍል በግራ እጅ በአራቱ ጣቶች ነካ እየተደረገ በስሱ ይመታል፡፡ ሰፊው ክፍል ጠበቅ ተደርጎ በኀይል ሲመታ ጠባቡ ግን በስስ መልኩ በዝግታና በቀስታ ይመታል፡፡ ለማኅሌት የሚመታ ከበሮ ከሀገረሰብ ጭፈራና ሌሎች አጋጣሚዎች ጥቅም ላይ ከሚውሉት ከበሮዎች የተለየ ነው፡፡ አመታቱ፣ አሠራሩና ምሥጢር አዘልነቱ ይለዩታል፡፡
እያንዳንዱ የከበሮ ክፍልና አጠቃቀም (አገልግሎቱ) አንዳች ነገር የሚያስታውስ በመሆኑ ከበሮን ተምሳሌታዊ ያሰኙታል፡፡ ከበሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ የከበሮው ሠፊው ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ስፉሕ ምሉዕ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ጠባቡ ክፍል በሰውነቱ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን የትስብእትን (የሥጋን) ውሱንነት ያስረዳል፡፡ ሁለቱን የከበሮ አፎች ያያዛቸው ጠፍር (ቆዳ) የተዋሕዶ ምሳሌ ነው፡፡ መለኮትና ትስብእት አንድ የሆኑት በተዋሕዶ ነውና፡፡ ሌሎቹ ተጠላልፈው የሚታዩት ጠፍሮች አይሁድ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘው ከጲላጦስ ትእዛዝ ውጪ አብዝተው በገረፉት ጊዜ የግርፋቱን ሰንበር የሚያስታውስ ነው፡፡ ከበሮ በሚመታበት ጊዜ በትከሻ ላይ የሚነገተው ማንገቻ ጌታችን በዕለተ ዐርብ የተገረፈበትን ጅራፍና የታሠረበትን ገመድ ያስታውሳል፡፡ ከጠፍሩ በታች ከበሮው የተሸፈነበት ሱቲ ወይም ጨርቅ አይሁድ ያለበሱት ከለሜዳና የመግነዙ ምሳሌ ነው፡፡
በሱቲ የተሸፈነውና በቆዳ የተወጠረው ከበሮ በዝግታና በፍጥነት መመታቱ ነቢዩ ኢሳይያስ “ጀርባዬን ለግርፋት ፊቴን ለጽፍአት /ለጥፊ/ ሰጠሁ” ሲል ስለ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነበየው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ፊቱን በሻሽ ሸፍነው አምላክ ከሆንክ በጥፊ የመታህ ማነው? እያሉ በመዘባበት በጥፊ መትተውት ስለነበር ያንን ያሳስበናል፡፡ የከበሮው አመታትም መጀመሪያ ሲጀመር በጣም ዝግ ብሎ እየተቆጠረ ይጀምርና በኋላ እየፈጠነ በመሄድ በመጨረሻም ለመቁጠር በማይቻል ሁኔታ አመታቱ እየፈጠነ ይሄዳል፡፡ ይኽም የአመታቱ ሥርዓት የጌታን መመታት ይገልጻል፡፡ ሮማውያን በሕጋቸው የሚሰቅሉትን አይገርፉትም፤ የሚገርፉትንም አይሰቅሉትም፡፡ ጌታን ግን ገርፈው ለመስቀል ስላሰቡ መጀመሪያ ግርፋቱን ሲጀምሩ እየቆጠሩ መግረፍ ጀምረዋል፣ በኋላ ግን ቁጥሩን እያሳሳቱ፣ እየተፈራረቁ ብዙ ገርፈውት ስለነበር የከበሮው ምትም እየፈጠነ በመሄድ ለቆጠራ አስቸጋሪ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱ የጌታን ግርፋት ለማስታወስ ነው፡፡
ለ. የጸናጽል ትዕምርትነት /ምሳሌነት/

ጸናጽል ፡- ጸንጸለ መታ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸንጸለ ማለት አቃጨለ ፣ደወለ ማለት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 150፡5 “እግዚአብሔርን ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጸል አመስግኑት” በማለት ጸናጽል ለመዝሙር አገልግሎት ያለውን ታላቅ ድርሻ ገልጾልናል፡፡ ጸናጽል የኪዳነ ኖኅ ምሳሌ ነው:: (ዘፍ 9፡8-17)
1.1K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 15:06:32 ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችን ምድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማዕቷ ለትውልድ የሚተላለፍ የዘላለም ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ መታሰብያዋን ያደረገ ስሟን የጠራ፣በስሟ ቤተ ክርስትያን የሰራ፣የተራበውን በስሟ ያበላ፣የተጠማውን በስሟ ያጠጣ፣የገድሏን መጽሐፍ የጻፈውን፣ያጻፈውን፣ያነበበውን፣የተረጎመውን፣ሰምቶም በልቡ ያኖረውን፣የልቡን መሻት እንደሚፈጽምለት እና በመንግስተ ሰማያት እንደ እርሷ የክብር አክሊል እንደሚያቀዳጀው፤ሥዕሏን አሥሎ በክብር በቤቱ አስቀምጦ ሽቶ እየረጨ ቢጸልይበት ጸሎቱ እንደሚሰማና ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ እንደሚያሸተው፣ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በስሟ የሰየመ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና ከበረ ስም እንደሚሰጣቸው፣ዕጣን፣ስንዴና መብራትን፣ልብሰ ተክህኖ፣መጋረጃ ቢሰጥ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስ እንደሚለብስ፣ያለ ወቀሳ ያለከሳ ባህረ ሲኦልን ተሻግሮ መንግስቱን እንደሚወርስ ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡

፨ ሰማዕቷን ከሌሎች ቅዱሳን ልዩ የሚያደርጋት ታሪክ ፨

በግብጽ አገር አርባ ዓመታት የነገሠ ባለ 12 ክንፉ ብጹአዊ አቡነ ሙሴ የሚባሉ ታላቅ ጻድቅ አሉ፡፡ እኝህ ጻድቅ ከንግስና ወደ ምንኩስና የተሸጋገሩ መንፈሳዊ አርበኛ ናቸው፡፡

ታድያ እኝህ ጻድቅ የቅዱሳን፣የሰማዕታትን ዓጽም እሰበሰቡ ደግላቸውን እያጻፉ፣ቤተ ክርስትያን በመስራት፣ታቦታቸውን በማክበር፣በበዓላቸውም ቀን ይቀድሱ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ታቦት ለማሰናዳት፣ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ በወርቅ የተለበጠ እና በላዩ በሮማይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት ያገኛሉ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰቡ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመሩ፡፡ ግን የቅድስት አርሴማን ግድልና የሞቷን ዜና አላገኙም፡፡ ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች እና የሰማዕትነቷን ሥራ ያስረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አመለከቱ፡፡

ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለአቡነ ሙሴ ተገልጦ ‹‹ብጽአዊ ሙሴ ሆይ የብጽእት አርሴማን ሥራ እነግርህ ዘንድ ስማ፡፡ ይህቺ ሰማዕት ገና አልተጸነሰችም፣አልተወለደችም፤በወርቅ ዓምድ በህይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ፡፡ ነብዩ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይፋል እንዳለ እርሷም በኃለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች፤በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል፡፡

ተአምሯ የሚነገረው በኢትዮጲያ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰብያ መጥራት አትተው፡፡ ጽላትዋም ከአንተ ጋር ይኑር፡፡ የመቅደስዋም ህንጻ በህንጻህ ቦታ ጎን ይኑር፡፡ ስምህ በተጠራበትም የስሟ መታሰብያ ይጠራል›› ብሎ መልአኩ ወደ ላከው እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡

አቡነ ሙሴም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ ሰማዕቷም ገና ሳትወለድ በፊት እንደ እመቤታችን በእግዚአብሔር ህሌና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ እኛም እንደ እንደ ጻድቁ አቡነ ሙሴ በሰማዕቷ ጸሎት እና ቃል ኪዳን ልንጠቀምባት ይገባል፡፡

የበረከት ቀን ይሁንላችሁ!

መስከረም 28/1/2012 ዓ.ም

አዲስ አበባ
1.1K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 15:06:32 አርሴማ ቅድስት ሰማዕት

አጠር በጠር ያለ ታረኳ

ሰማዕትነትን የተቀበለችበትን እለት በማሰብ በድጋሚ የተለጠፈ

በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለሰማዕቷ ልጆች አዳርሱ

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከሚያከብሩ ብሩካን ከሆኑ፤በጾም በጸሎት በስግደት በትጋት ከሚኖሩ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስ ከእናቷ ከቅድስት አትናስያና በጥር 6 ቀን የተወለደች ደገኛ የገድል አርበኛ ናት፡፡

በተለይ ስትወለድ ይህ ቀረሽ የማትባል እጅግ መልከኛ እና ግርማዋ የሚያስፈራ ነበር፡፡ እናት እና አባቷም በጾም በጸሎት በስዕለት ስላገኟት እስከ 3 ዓመት ካሳደግዋት በኃላ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም በተሰራች ቤተ ክርስትያን ታገለግል ዘንድ ሰጧት፡፡ እመቤታችንን 12 ዓመት አገልግላ ያለፈቃድዋ በቤተሰቦችዋ ግፊት በ15 ዓመቷ ዳሯት፡፡ ሰማዕቷ ግን ዓለማዊ ህይወት ባለመፈለግዋ ወደ ገዳማዊ ምናኔ ህይወት ገብታለች፡፡

በዚያን ዘመን ብዙ ሰማዕታት ያስፈጀ ጨካኙ የሰው አውሬ ካሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ መላኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሴት ሊያገባ ሽቶ በየአገሩ ሁሉ ፈልገው መርጠው ያመጡለት አንድ አሽከሮቹን አዘዘ፡፡

እንግዲህ የሰማቷ አሳዘኝ የመከራ ህይወት ከዚህ ነው የሚጀምረው፡፡

የዲዮቅልጥያኖስ ሠራዊቶች አርሴማ የምትባል ውብ ሴት እንዳለች በሰሙ ጊዜ ቅድስት አርሴማ በሮሜ በአንድ ገዳም እንዳለች ሰሙ፡፡ አዋቂዎችም የሰማዕቷን ውብ መልኳን ስለው ለንገሡ ለዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ስዕሏን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና በሥጋዊ ጋብቻ አብራት ሊኖር እንዳሰበ ለመኳንንቱ ነግሮ ለሠርግ እንዲመጡ አዘዘ፡፡

ቅድስት አርሴማ ይህንን በሰማች ባወቀች ጊዜ ከደናግሉ ጋር የንጉስ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነው አርመንያ አገር ሸሸች፡፡ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ የከበረች አርሴማን አስፈልጎ ባጣት ጊዜ በአርመንያ እዳለች ሰማ፡፡

ለአርመንያው ንጉሥ ለድርጣድስ ከእሱ ሸሽታ እንደሄደች እና ባስቸኳይ አስጠብቆ እንዲልክላት አዘዘው፡፡ ደናግሉ ይንን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሰወሩ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በክብር ያመጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ሰማዕቷም ወደ እርሱ መምጣትን እንቢ ባለች ጊዜ በመሬት እየጎተቱ ወደ ንጉሡ አቀረቧት፡፡

ድርጣድስ የቅድስት አርሴማን ደም ግባት እና ውበት ባየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ የመንፈስ እናቷን አጋታን አባብላ እሺ ታሰኛት ዘንድ አዘዛት፡፡

አጋታም ወደ ሰማዕቷ ሄዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት ‹‹ ዕወቂ ይህ ርኩስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ምሽራሽን ክርስቶስን እንዳትተይ›› ብላ አጸናቻት፡፡

ንጉሥ ድርጣድስም ሰማዕቷን ይዞ ወደ እልፍኝ ሊያስገባት ከአደባባይ መካከል ተነስቶ ድንግል አርሴማ በእጁ ያዛት፡፡ በዚያን ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው፡፡ ድርጣድስም በጦትነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለነበር በታናሽ ብላቴና ስለተሸነፈ መኳንንቱ ፊት ስለተዋረደ አፈረ፡፡

ከዚህ በኃላ በሰው አንደበት ለመናገር የሚከብድ መከራና ስቃይ አጸናባት፡፡ ሰማዕቷም ከንጉሡና ከጋሻ ጃግሬዎቹ የሚደርስባትን መከራ በመታገስ በረታች፡፡ ንጉሥ ድጣድስ በሰማዕቷ ላይ የሚያደርሰውን ሥጋዊ መከራ የልቡ ስላልደረሰለት ጡቷን በማስቆረጥ ዓይኗን በወረንጦ በማስወጣት ቢያሰቃያትም ሰማዕቷ ይበልጥ በክርስቶስ ፍቅር ጸናች፡፡ በሚደርስባትም ነገር ደስ ተሰኘች፡፡

ወዳጆቼ እኛ በሚደረስብን ሥጋዊ ህመም ስቃይ መከራ ፈተና እንደሰታለን? አንደሰትም ይልቁንም እናማርራለን፡፡ ምንያቱም የክርስቶስ የመከራ ህይወት ውስጣችን ስላልገባ ነው፡፡ ክርስቶስ ጋር ለመድረስ መንገዱ፣በአጋንንት እና በሥጋ እየተጎዱ መሆኑን ስለማንረዳ ነው፡፡ ብንረዳም የደስታ እንጂ የመከራ ትከሻ ስለሌለን ነው፡፡ የመከራ ትከሻ ቢኖረንም ትዕግስት ስለሌለን በመከራችን አንጸናም፡፡

በመጨረሻም ንጉሥ ድርጣድስ የሚያደርገውን ሲያጣ አንገቷን በሰይፍ ሊያስቆርጥ ወሰነ፡፡ ከዚህ በኃላ ንጉሥ ድርጣድስ ቡርክት ቅድስት አርሴማን ወደ መገደያ ወንዝ እንዲወስዷትና በዚያም የከበረ ራሷን ይቆርጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን ወታደሮች አንገቷን ሲቆርጧት ያይ ዘንድ ከእርሷ ጋር ወጣ፡፡ ሰማዕቷ በምትገደልበት ትይዩ ከሠራዊቱ ጋር ተቀመጠ፡፡

የእጃቸው ክንድ የበረታ ልባቸው ግን የጨከነ ሮማውያን ወታደሮች ሰይፍ ይዘው ወደ ሰማዕቷ ቀረቡ፡፡ ሰማዕቷ ሞቷ ሰማያዊ እረፍቷ ስለሆነ በደስታ ትመለከታቸው ነበር፡፡

ቅድስት አርሴማም ወታደሮቹን የጸሎት ጊዜ እንዲሰጧት ጠይቃቸው ፈጣሪዋን ካመሰገነች በኃላ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ ወገቧን ታጥቃ አንገቷን ከፍ አድርጋ ለሚቆወጣት ታመቻችላቸው ነበር፡፡

ቆራጮች ወታደሮች ከቅድስት አርሴማ ግርማ የተነሳ ደንግጠው ሰይፋቸውን እንደያዙ በምድር ላይ ወደቁ ሰይፋቸውንም ጣሉ፡፡ ሰማዕቷም እያበረታታች የታዘዛችሁትን ፈጽሙ ትላቸው ነበር፡፡ ወታደሮቹም እኛስ ወዳንቺ መቅረብ እና አንገትሽን መቁረጥ አልቻልንም በግንባርሽ ላይ ያለው ትዕምርተ መስቀል አስፈርቶና፤ግንባርሽን ካልሸፈንሽልን አንገትሽን ፈጽሞ ልንቆርጥ አንችልም አሏት፡፡

ሰማዕቷም ለወታደሮቹ ፊቴን የምሸፍንበት ቁራጭ ልብስ ወይም ቁራጭ ጨርቅ ስጡኝ አለቻቸው፡፡ እነሱም ቁራጭ ጨርቅ ጣሉላት እሷም ፊቷን ሸፈነች፡፡

ቅድስት አርሴማም ንጉሥ ድርጣድስ እና ሠራዊቱ ህዝቡም እየተመለከቱ ምስከረም 29 ቀን አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ፡፡ ወዳጆቼ እኛን ጌታችን እንደ እነ ቅድስት አርሴማ፣ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ወዘተ አንገታችሁን ተቆረጡልኝ ሰማዕት ሁኑልኝ አላለንም፡፡ ኃጢአትን ከእናንተ ሰውነት ቆርጣችሁ ጣሉት ነው ያለን፡፡

የዝሙትን ፍላጎት ከሰውነታችሁ ቁረጡና ደም አላባ ሰማዕት ሁኑ ነው የተባልነው፡፡ የኃጢአቶችን ተቀጽላ ከሥጋችሁ ላይ ቁረጡና በንስሐ ጻድቅ ሁኑ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት በደማቸው ዋጋ ገነት ግቡ ሳይሆን በደሜ ፈሳሽት መንግስቴን ውረሱ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት ጽኑ መከራን በስጋችሁ ተቀበሉ ሳይሆን ቅዱስ ሥጋዬን ብሉና የርስቴ ተካፋይ ሁኑ ነው ያለን፡፡ ሰማዕት ሁኑ ሳይሆን በእኔ መስዋዕትነት ዳኑ ወደ መንግስቴ ጎዳና አቅኑ ነው ያለን፡፡ አወይ አለመጠቀማችን እንደ እኛ ያደለው ማን አለ?

ከአንገቷም ደም፣ውኃ፣ቀተትና ማር እንደ ክረምት ነጠብጣብ እየተንጠባጠበ መነጨ፡፡

ደም ከአንገቷ የመነጨው ስለ ሃይማኖትዋ ቆራጥነት ስለ ሞት አለመፍራት እና የጌታችንን መከራ ተሸክማ ሰማዕት ስለሆነች ነው፡፡

ውኃ የፈሰሰው ስለ ብዙ ጸሎትዋ፤ስለልመናዋና የቤተ ክርስትያን መጻሕፍትንና ምስጢራትን ሁሉ ልብ ስለምታደርግ ነው፡፡

ወተት የመነጨላት ስለ ክብሯ ስለ ከፍታዋ እና ንጽሃ ድግልናዋን ስለጠበቀች ነው፡፡

ማር የወረደው ስለሚያስደንቅ የፊቷ ወዝ፣ደም ግባቷ፣ስለ ጣፋጭ የከንፈሯ ቃልና የሰማዕታት ሁሉ እህት ስለሆነች ነው፡፡

ከዚህ በኃላ ብሩህ የሆነ የደመና አምድ ወረደና በላይዋ ጋረዳት፡፡ ወደ ሰማይም እንደ መብረቅ ሳባት፡፡ የቅዱሳን መላእክትም ማህበር ነፍሷን አሳረጓት፡፡ በክብር በእልልታ በዝማሬና በማህሌት ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አስገቧት፡፡

እርሷ እንደ ሞተች ባወቁ ጊዜ ወታደሮቹ ደናግሉን ሁሉ ጫማቸውን እየበሱ እራሳቸውን ቆረጡ፡፡ ቁጥራቸውም ሰባ ሁለት ነፍሳት ነበሩ፡፡

፨ ቃል ኪዳንዋ ፨
1.1K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 11:18:01
ሁላችሁም ኦርቶዶክሳውያን ይህን ሳታዩና share ሳታደርጉ እንዳታልፋ መስቀል አደባባይ የኛ ነው ለሀይማኖታችን ካስፈለገ እንዘምታለን
2.0K viewsedited  08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-01 22:12:45 ትዝታ ቅኝት በሌላ ስሙ "ዋኔን" ቅኝት ይባላል። አምባሰል ቅኝት በሌላ ስሙ "ሰላምታ" ቅኝት ይባላል። እንዲሁም አንቺሆዬ ቅኝት በሌላ ስሙ "ስለቸርነትህ" ቅኝት ይባላል።
2.7K views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-28 14:13:42
ምስጋናው ይቀጥል
2.7K viewsedited  11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ