Get Mystery Box with random crypto!

6) ቀልድህ አያስቃትም። አንተ እሷን አስቃለሁ ብለህ መከራህን ስትበላ፣ የምትናገረው ነገር አይደለ | ቅዱስ ብልግና

6) ቀልድህ አያስቃትም። አንተ እሷን አስቃለሁ ብለህ መከራህን ስትበላ፣ የምትናገረው ነገር አይደለም ጥርሷን ማስገልፈጥ ፊቷን እንኳ አያስፈግግም። መሳሳቅና መቀላለድ የድሪያ አንዱ መንገድ ነው። ካንተ ጋር መዳራት የሚያስደስታት ሴት፤ በሚያስቀውም፣ በማያስቀውም ትደሰታለች። ካልፈለገችህ ግን አይደለም በማያስቀው ልትስቅ፣ ቀልድህ ራሱ አይገባትም። ጓደኞች ከሆናችሁ ግን ይሉኝታ ይዟት ወይም ቀልዱ ከምር የሚያስቅ ሆኖ ሲገኝ ትስቅልህ ይሆናል።

7) ሁሌም እቅድ ማውጣት ላይ ታቅማማለች። አንተ ለምታቅደው ነገር መሰናክል ትሆናለች። ቀጠሮ አታከብርም። እንደማይመቻት ነግራህ አትመጣም። በየጊዜው ለሁለታችሁ ብለህ ያቀድከውን እንድትሰርዝ ታደርግሃለች። መስሎህ ነው እንጂ እቺ ልጅ ላንተ አይደለችም። ጊዜህን አታባክን። ከወደደችህ ለምን ታቅማማለች? ለምን እቅድህን ታሰርዝሃለች?

8)በሐሳቧ የምትስለው ወንድ አንተን አይመስልም። ሰውየው መልኩ፣ ቁመናው፣ አስተሳሰቡ፣ አነጋገሩ፣ አበላሉ፣ አጠጣጡ፣ አደናነሱ፣ አለባበሱ፣ ሁለመናው ሆሊውድ ለገበያ የሚያቀርባቸውን የፊልም ተዋንያንን እንጂ አንተን በጭራሽ አይመስልም። በሌላ አነጋገር፣ አንተ የእሷ ፍቅረኛ ልትሆን አትችልም። እንደማትችል በግልጽ ቋንቋ እየነገረችህ ነው። የሆሊውዶቹን ወንዶች ለመምሰል ጊዜህንም ሆነ ጉልበትህን አታባክን። ባጠቃላይ፣ የምትወዳት ልጅ ካንተ ጋር ስትሆን ስለሌሎች ወንዶች ማውራት ካዘወተረች፣ አትኩሮቷ ካንተ ይልቅ ሌሎች ወንዶች ላይ ከሆነ፣ አንተን ለፍቅር ጓደኝነት አላሰበችህም ማለት ነው። አንተን ወይ እንደ ጥሩ፣ አማካሪ ጓደኛዋ ነው የምታይህ፤ ያ ካልሆነ ደግሞ የሚመቻትን፣ በፍቅር የሚያከንፋትን ወንድ እስክታገኝ ድረስ የጊዜ ማሳለፊያዋ ነህ። በርግጥ አንዳንድ ሰዎች ፍቅር ሳይዛቸው ፍቅር ውስጥ ይገቡና፣ ፍቅሩ ከተጀመረ በኋላ አፍቃሪያቸውን በጊዜ ሂደት ሊወዱት ይችላሉ። ይሄ ግን የሚከሰተው አልፎ፣ አልፎ ነው። አንዳንድ ወንዶች ደግሞ “በድቼ ልጅ ካስወለድኳት፣ አማራጭ ስለማይኖራት፣ እየወደደችኝ ትመጣለች” ብለው ያስባሉ። እንደዚህ ዓይነቱ ከንቱ አስተሳሰብ አደገኛ ብቻም ሳይሆን ከራስ ወዳድነት የመነጨ ክፋት ነው። በዚህ አድራጎትህ የተነሳ፣ እድሜ ልክህን እየረገመችህ ልትኖር ትችላለች።

9) ያለጓደኞቿ ካንተ ጋር አትገናኝም። ቀጠሮ ስትይዙም ሆነ ለመዝናናት ስትወጡ ብቻዋን አትመጣም። ብቻዋን ብትመጣ እንኳ፣ ብዙ ላትቆይ ወይም “ወደ ቤት እንመለስ” ልትል ትችላለች። ብቻዋን ሆና ከአንተ ጋር መገናኘት ካልፈለገች፣ አብራችሁ ስትሆኑም እንደድሮው ነጻ ሆና ካላወራችና የመጨናነቅ ስሜት ከታየባት፣ የሆነ ችግር አለ ማለት ነው። ቅርርባችሁ ከጓደኝነት ያለፈ ትርጉም እንዲኖረው እንደማትሻ እየነገረችህ ነው። ለፍቅር ጓደኛነት አትፈልግህም። ጓደኞቿን አስከትላ የምትመጣበትም ምክንያት ፍቅር-ነክ ወሬ ወይም ጥያቄ ካንተ ላለመስማት ነው።

ለፍቅር ያሰብካት ልጅ፣ ከተጠቀሱት ምልክቶች ቢያንስ ሶስቱን ካሳየችህ፣ ለፍቅር እንደማታስብህ ተገንዘብ። ከሶስት በላይ ምልክቶችን ካሳየችህ ደግሞ ግንኙነቱን ብትጀምሩ እንኳ ዘላቂነት ላይኖረው ይችላል። እያወቅክ ራስህን ረመጥ ውስጥ መክተት ነው። በርግጥ የወደደ እውር ነው ይባላል። ነገር ግን እያወቁ መታወር ጅልነት ነው። ወደህ የማትወደድ መሆንህን እያወቅክ፣ ለልጅቷ ያለህን ስሜት በጅምሩ መቅጨት ስትችል፣ ለምን ራስን ስቃይ ውስጥ ትከታለህ? እሷ ላይ ጊዜህን ከምታቃጥል፣ ሌሎች ቆነጃጅትን ተዋወቅ። ላንተ የምትሆን አትጠፋም። our channel Link: @kidusblgna ለአስተያየት ወይም ጥያቄ :@kidusblgnabot