Get Mystery Box with random crypto!

​​​​† ጠላትን ለምን ከፋዉ † እኔዉ ጎንበስ ብዬ እኔዉ ቀና ላልኩት እኔዉ አመስግኜ እኔ ለሰ | VAMOS FIXED MATCH 🇪🇹

​​​​† ጠላትን ለምን ከፋዉ †


እኔዉ ጎንበስ ብዬ እኔዉ ቀና ላልኩት
እኔዉ አመስግኜ እኔ ለሰገድኩት
ጠላት ምን ተነካ የሚያረዉ በቅናት
እመቤቴ ብዬ እኔዉ ለወደድኳት
ያንድዬ እናት ብዬ እኔዉ ከወደድኳት
ብወድቅ ብነሳ እኔዉ ካልደከመኝ
ሳወድሳት ብዉል እኔን ካልሰለቸኝ
ስማፀናት ባድር እኔዉ ካልታከተኝ
ጠላት ምን አገባዉ አትስገድ የሚለኝ
ፃድቃንን አይቼ እኔ ብማፀናት
ገብረኤልን አይቼ እኔ  ባወድሳት
ሰማህታትን አይቼ እኔ ብሞትላት
አምላክን አይቼ እኔ እሷን ብመርጣት
ልጄ ስላለችኝ እናቴ ስላልኳት
ጠላት ለምን ከፋዉ እኔ እሷን ብወዳት
አፅናንተሽኝ አይቻለዉ ሲከፋኝ እናቴ
ሚስጥረኛዬ ነሽ ገፀ በረከቴ
አልተዉሽም እስከ ለተ ሞቴ



♚ @kidus_God ♚