Get Mystery Box with random crypto!

መክስተ ምስጢር ወዘኢያገድፍ #ፍፁም የሆነ የመርሳት ችግር መፍትሔ ቢሹ እንደምንም ከይትም ይህን | መርጌታ ቅዱስ የባህል ህክምና መስጫ ቻናል

መክስተ ምስጢር ወዘኢያገድፍ

#ፍፁም የሆነ የመርሳት ችግር መፍትሔ ቢሹ እንደምንም ከይትም ይህንን ገቢር አፈላልጋችሁ ተጠቀሙ።

የፈጠራ ክህለትዎ ይጨምራል።
የመርሳት ችግር ይቀረፋል።
የመያዝ ክህለትዎ እጅግ ይፈጥናል።

በስመ :አብ :ወወልድ: ወመንፈስ :ቅዱስ :፩ዱ ፡አምላክ፡ ጸሎት ፡በእንተ፡ መክስተ፡ ምስጢር፡ ኤራን፡ ኤራን፡ ኤራን፡ ዘከሰትከ፡ ሎቱ፡ ጥበበ፡ ለሰሎሞን ፡ከማሁ፡ ክሥት፡ ሊተ (የክርስትና ስም አስገባ)
ኩሎ፡ ሕቡዓተ-ልሳን፡ ከመ ፡እንብብ፡ ሠናየ፡ ንባበ ፡ዘኢያደክም፡ ለሰሚዕ፡ አዶናይ፡ አዶናይ፡ አዶናይ፡ ኤልሻዳይ፡ ኤልሻዳይ፡ ኤልሻዳይ፡ ኤሎሄ ፡ኤሎሄ፡ ኤሎሄ፡ ዮፍታሔ፡ ፍታሕ፡ ማዕሠረ -ልሳንየ፡ ወአንቅህ፡ ሕሊናየ፡ ወልቡናየ፡ እምንዋመ ፡ሐኬት፡ ወዝንጋዔ፡ እስከ፡ እሬኢ፡ ስውረ ፡ልሳን፡ ወእኬልህ ፡መዝሙረ ፡በዜማ፡ሰናየ፡ ከመ፡ ያሬድ ፡ክሥት፡ ሊተ፡ ጥበበ፡ ለገብርከ (የክርስትና ስም አስገባ)
አቅናኤል፡ አዝናኤል፡ ብርስባሔል፡ ኤሎሄ፡ ወዖ፡ ዘሀሎ፡ መይሄሉ፡ ለዓለመ፡ ዓለም፡ ፈኑ፡ ሠይፈ- እሳት፡ ሜሎስ፡ ኃቤየ፡ ዘእምኀቤከ ፡ዘፈነውከ፡ ሎሙ፡ ለአርዳዕከ ፡በጊዜ፡ ፫ቱ፡ ሰዓት፡ ወበ፶፡ ዕለት፡ በጽርሐ፡ ጽዮን፡ መካን ፡ዘአስተይኮሙ፡ ለአርዳዕከ ፡ሰይፈ ነበልባል፡ በጽርሐ- ጽዮን፡ ቅድስት፡ ወአንበቦሙ፡ በነገረ -ጳርቴ፡ ወኤላሜጥ፡ በ ፸ወ፡ ፪ቱ፡ ልሳናት፡ ከማሆሙ፡ አንብበኒ፡ ንባበ፡ ኃይለ፡ ቃል፡ ወአለብወኒ፡ ፍካሬ- መጻሕፍት፡ ዘብሉይ፡ ወዘሐዲስ፡ ሊተ ፡ለገብርከ፡ (የክርስትና ስም አስገባ)
ኤል ፡ኤል ፡ኤል፡ ባኮን፡ ሐዚክን ፡ዘይፈትሕ፡ ልበ፡ ዕብን፡ ዕብንሰ፡ አነ፡ ገብርከ፡ በዲበ፡ አሐቲ፡ እብን፡ ዘ ፯ቱ፡ አዕይንት፡ ከማሁ፡ ፍታሕ ፡ወአብርህ፡ ፯ተ፡ አዕይንተ ፡ልብየ፡ ለአንብቦ፡ መጻሕፍት፡ ወለአጽንዖ፡ መዝሙረ- ዳዊት፡ ወለድረሰታተ፡ ወለፈክሮ፡ ማህሌቱ፡ ለእግዚአብሔር፡ ወአስተራውጽ፡ ልሳንየ ፡ወይኩን፡ ልሳንየ፡ ከመ፡ መብረቅ፡ ፈጣን፡ ወከመ፡ ነጎድጓድ፡ ግሩም፡ ፎ ፎ ፎ ፎ ፎ ፎ ፎ ፡አስራበ ፡ልሳንየ፡ አስፍሕ ፡ወቁልፍትየ ፡ፍታሕ፡ በኃይለ፡ እሉ ፡አስማቲከ፡ ረስዮ፡ ለልብየ፡ ከመ -ፀሐይ ፡ብሩሃ ፡፩ ጊዜ ፡ዘአጽናዕኩ፡ ከመ ኢይግድፍ ፡ወዘኢያጽናዕኩ ፡ከመ አጽንዕ፡ አነ፡ ገብርከ፡ (የክርስትና ስም አስገባ)

ገቢሩ፦የዕፀ ኮመል ደም
የቀጠጥና ሥር
#ቀጠጥናው አንድ የጣት ዓፅቅ በመለካት አድርቀው ፈጭተው በ ዕፀ ኮመሉ ደም በመለወስ ከዛ በንፁህ የጥቅምት ማር ፫ የሾርባ ማንኪያ በመለወስ። ለሰባት ቀን ጧት ጧት ሰባት ሰባት ጊዜ ከላይ ያለው ጸሎት በተለወሰው ማር ላይ በመጸለይ ከሰባት ቀን በኃላ ለ ፫ ቀን በባዶ ሆድ መዋጥ።

የሚከለከሉ ነገሮች፦
1,አልኮል መጠጥ
2,እንቁላል/ወተት/ሎሚ
3,ተልባ/sex/የወር አበባ

#ፍቱን ነው የዕጸ ኮመሉ ደም እንዳይበዛ ልብ ይጎዳል።

የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

0985166353