Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ ከሌለን፤ ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለን ነገር ይበል | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ

ከሌለን፤ ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለን ነገር ይበልጣል። ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ መልካም ነገሮች አሉ።

ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል። ይሁን እንጂ አዲስ ቀን ሲሰጥህ ከብዙዎች በላይ እድለኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን። በሰላም ውሎ በሰላም ማደር እጅግ ትልቅ ነገር ነው። አዲስ ቀን አዲስ ህይወት ነው።

አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፤ የራስህንም አታቃል።

ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን በመኖርህ ብቻ ደስታን ምርጫህ አድርግ። አዲስ ቀን እንድታይ ስለተፈቀደልህ ብቻ ለፈጣሪ ምስጋና ልታቀርብ ይገባል።

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን

@Kezimkezia