Get Mystery Box with random crypto!

#ሁለቱ_ልጃገረዶች           ክፍል አራት ኸዲጃ እርካታውን ያጣችው ወጣት ወኪሎቿ ብልህ | ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️

#ሁለቱ_ልጃገረዶች


          ክፍል አራት

ኸዲጃ እርካታውን ያጣችው ወጣት ወኪሎቿ ብልህነትና ብቃት ጎድሏቸው ስራውን በአግባቡ መወጣት ስለተሳናቸው ሳይሆን ለታማኝነት ያላቸው አመለካከት ደካማ በመሆኑ ነበር።

በመሆኑም ኸዲጃ የተሻለ ወኪል ሰራተኛ ለማግኘት ዘወትር ትጥር
ነበር አንድ ቀን ለዚሁ ስራ ብቁ የሆነን ሰው ለመቅጠር ባቀረበችው ጥሪ መሰረት ማመልከቻ ካስገቡ ስራ ፈላጊዎች መካከል የአሚና ልጅ ሙሐመድ አንዱ ነበር። ሙሐመድ ከእናቱ ሞት በኋላ በመጀመሪያ ኑሮውን አድርጎ የነበረው ከአያቱ አብዱል ሙጠሊብ ዘንድ ነው አያቱ ታዲያ በከተማ የመማክርት ስብሰባ ላይም ሆነ በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች በሚሄዱበት ስፍራ ሁሉ አብሯቸው እንዲሆን ይፈቅድለት ነበር። በዚህም የተነሳ ሙሐመድ ብዙ የስራ ልምዶችን ለመቅሰም በቅቷል ያም ሆኖ ግን ከእያቱ ጋር መኖር የቻለው ለሁለት ዓመታት ብቻ ነበር። ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ አያቱ በመሞታቸው ኑሮውን ከአጎቱ አቡ ጣሊብ ቤት ለማድረግ ተገደደ፡፡ አቡ ጣሊብ ሙሐመድን በእጅጉ ይወዱት የነበረ ቢሆንም ቤተሰባቸው በርካታ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ የህይወት ፈተናዎችና
ጭንቀቶች ነበሩባቸው፡፡ በዚህም የተነሳ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የበኩሉን እየሰራ ቤተሰቡን ማገዝ ነበረበት፡፡ እናም ገና ታዳጊ ልጅ የነበረው ሙሐመድ የአካባቢው ሰዎችን በጎች በማገድ ቤተሰቡን ያግዝ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን አጎቱ ሙሐመድ ወደፊት ሚተዳደርበትን የንግድ ስራ ክህሎት በአግባቡ ያካብት
ዘንድ ያስተምሩት ጀመር፡፡ አንድ ጊዜ እንዲያውም እስከ ሶሪያ ድረስ ይዘውት ሄደው እንደነበርም ይነገራል፡፡

ከኸዲጃ ዘንድ ለመቀጠር ጥያቄ ባቀረበበት ወቅት ሙሐመድ በመላው መካ ሁሉም እምነት የሚጥልበት ሰው መሆኑ መነገር ጀምሮ ነበር፡፡ በዚህ መልካም ዝናው የተነሳ እንዲያውም በሚያውቁት ዘንድ "አል-አሚን" ወይም ታማኙ የሚል ስምን ለመጎናፀፍ በቅቶ ነበር፡፡ ሰዎች ሩቅ መንገድ ለመጓዝ ሲነሱ ውድ የሆኑ ንብረቶቻቸውን በአደራ መልክ የሚያስቀምጡት ሙሐመድ ዘንድ ነበር፡፡ ኸዲጃም ታዲያ እነዚህን ሙሐመድን የተመለከቱ
እውነታዎች ቀደም ብላ ሰምታ ነበር፡፡ እና ኸዲጃ ዘንድ ለመቀጠር
ማመልከቻ ካስገቡት ተወዳዳሪዎች መካከል ሙሐመድ የበለጠ ተወዳዳሪ ሆኖና በኸዲጃ ተመርጦ ስራውን ያገኝ ይሆን? ኸዲጃ ስለሙሐመድ የሰማቻቸውን እውነታዎች በተጨባጭ ማረጋገጥ
ሳትፈልግ አልቀረችምና ቀጠረችው፡፡ ለገበያ የሚቀርቡትን እቃዎቿን
በማስያዝም የመጀመሪያ የሩቅ አገር ንግዷን ወክሎ እንዲገበያይ
ሙሐመድን ላከችው ያም ሆኖ ግን ሙሐመድ በዚህ ወቅት ብቻውን አልነበረም የኸዲጃን ንብረት ይዞ የተጓዘው፡፡ መይሰራ የተባለው ባሪያዋ ከሙሐመድ ጋር አብሮ በመጓዝ ሙሐመድን እንዲያግዝና በመጨረሻ ላይም አጠቃላይ የንግድ ተግባሩን በተመለከተ ሪፖርት እንዲያቀርብ አዘዘቸው፡፡

ሙሐመድ የተሰጠውን ኃላፊነት በመፈፀም ተመለሰ፡፡ ከሙሐመድ
ጋር የተጓዘው መይሰራም ለአሳዳሪው ባቀረበው ሪፖርት ሙሐመድ እጅግ ታማኝ፣ ጎበዝና ቅንነትን የተላበሰ ሰው መሆኑን አረጋገጠ፡፡ ሙሐመድ ባሪያዎችን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ሰው በታላቅ አክብሮትና ትህትና የሚያስተናግድ ምርጥ ሰው መሆኑንም የመይሰራ ሪፖርት አመለከተ። ኸዲጃ በደረሳት መይሰራ እማኝነት መሰረት ሙሐመድ ትርፍ ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው እንደሌሎቹ መንገደኛ ወጣት ነጋዴዎች ወይን በመጠጣትና ሌሎች አልባሌ ተግባራትን በመፈፀም ሳይሆን እረፍት በማድረግና የጥሞና ጊዜ በመውሰድ በተለያዩ የህይወት ጉዳዮች ዙሪያ በማሰብ ነበር፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን የተላከበትን ኃላፊነት በከፍተኛ ክህሎትና ትጋት በመወጣት ጠቀም ያለ ትርፍ ይዞ ነበር የተመለሰው፡፡ ኸዲጃም በሙሐመድ የስራ አፈፃፀም ከሚገባው በላይ ረካች፡፡ በስምምነታቸው መሰረት ከሩቅ አገር የንግድ ስራው ከሚገኘው ትርፍ ግማሹን ሙሐመድ ይወስዳል፡፡

ኸዲጃ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ሙሐመድን መርሳት አልቻለችም፡፡ ወደ ሶሪያ በሚደረገው ተከታዩ ዓመት ትልቅ የሩቅ አገር ንግዷ በድጋሚ ወኪሏ አድርጋ ልታሰማራው ወሰነች፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃችም፡፡ ለስራው ልትቀጥረው ቃለ ምልልስ ባደረገችለት ወቅት ወጣቱ ሙሐመድ በኃይማኖትና በፍትህ ረገድ ያለውን አንዳች ልዩና በእርሷ አእምሮ ውስጥ ካለው አመለካከት ጋር እጅግ ተመሳሳይነት ያለው አስተሳሰብንም ታዝባ ነበር፡፡ በዚሁ ወቅት ሙሐመድ በመካ ውስጥ የሚኖሩ ምስኪን የህብረተሰብ ክፍሎችን መብት ለማስከበር የሚንቀሳቀሰውና ሒልህ አል-ፉዱል የተሰኘ ቡድን አባል መሆኑን በመገንዘቧ ተደንቃ ነበር፡፡ እናም ቀልቧ ስለ ሙሐመድ በጥልቁ ማውጣትና ማውረድ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

ሙሐመድ የኸዲጃ የትዳር ተጓዳኝ እንዲሆን ትሻ ይሆን? ግን ደግሞ ሙሐመድ ገና ወጣት በመሆኑ ከኸዲጃ በእድሜ ያነሰች ሌላ ወጣት ልጃገረድን ሊመርጥ ይችል ይሆናል?

  ያም ሆኖ በሙሐመድ  ልዩ ሰብእና እንዲሁም ከእርሷ ጋር ተመሳሳይነት ባለው የእምነትና የፍትህ አስተሳሰቡ የተማረከችው ኸዲጃ ትዳር ከመያዝ ጋር በተያያዘ ሙሐመድ ያለውን ሐሳብ ትጠይቅላት ዘንድ አንዲት አረጋዊ ሴትን ላከች። ነገር ግን በሙሐመድ ዘንድ ትዳርን አስመልክቶ ምንም ዓይነት ሀሳብ እንደሌለ ከአረጋዊዋ ሴት የተገኘው መረጃ አመለከተ ሙሐመድ ትዳር መስርቶ ቤተሰብ ማስተዳደር ብዙ ወጪ የሚጠይቅ ውሳኔ ነው! በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሰርቶ የሚያገኛትን ሁሉ በቀጥታ የሚያስረክበው ለአጎቱ መሆኑን በመግለፅ ነበር አረጋዊዋን የሸኛት። ይህንን የሙሐመድን አመለካከት የተገነዘበችው ኸዲጃ ገንዘብን አስመልክቶ ምንም ዓይነት ጭንቀት ሊገባው እንደማይገባ ገለፀች ሙሐመድም ትዳር ለመያዝ መስማማቱን አረጋገጠ...





ል...