Get Mystery Box with random crypto!

ጠፊዋ ዱንያ ቀን ቀን የደከምንለት ሌት ሌቱን የቃዠንለት ሃብትና ንብረት አመድ መሆኑ አይቀ | ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️

ጠፊዋ ዱንያ



ቀን ቀን የደከምንለት ሌት ሌቱን የቃዠንለት ሃብትና ንብረት አመድ መሆኑ አይቀሬ ነው! ! እንኳን ተሰብሳቢው ሰብሳቢውም አይቀርለት!!
كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍۢ
በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡

ያለ የሌለንን ሁሉ ጥለን ወደ ዘላለማዊው የአኺራ ኑሮ የምንጓዝበት አንድ ቀን ከተፍ ማለቱ አይቀሬ ነው! የዛኔ አሳደን ያጠራቀምንው ሸቀጥና ገንዘብ ከአስከፊው የቀብርና የጀሃነም ቅጣት አያድነንም ። ከአላህ እዘነት ጋር መልካም ከለላ የሚሆነን ተውሒዳችንና በትእግስት ያካበትንው መልካም ስራ ነውና ያለፈውን ሁሉ ሊምር ቻይ ወደሆነው الله እንመለስ እና መልካም ስራዎችን እናካብት!!
አላህ በተከበረው ቁርአኑ በዱንያ ላይ የለገሰልንን ሁሉ ጥለን ቤሳቢስቲን ሳይኖረን እሱን የምንገናኝበት ቀን እንደሚመጣ እንዲህ በማለት ያስታውሰናል ፣
وَلَقَدْ جِئْتُمُونَا فُرَٰدَىٰ كَمَا خَلَقْنَٰكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍۢ وَتَرَكْتُم مَّا خَوَّلْنَٰكُمْ وَرَآءَ ظُهُورِكُمْ ۖ ...
መጀመሪያም ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ኾናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ ለየብቻችሁ ኾናችሁ በእርግጥ መጣችሁን ....
ያለፈው ሁሉ አልፏል በዱንያ ሸቀጦች መታለላችን ይብቃና ወደ አላህ እንመለስ — ፈጣሪያችን አዛኝና መሃሪ ነው!!
አላህ ይምራን!!