Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡ ክፍል 24 ደራ | የብዕር ጠብታ✍📒📖

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡

ክፍል 24

ደራሲ - አብላካት



እኔ ከማናቸውም ጋር ንግግር ባልፈልግም ግን ደግሞ የአንዳቸውንም ክፉ ማየት አልፈልግም.....ሰዎች ህይወታችን ውስጥ ብዙ መጥፎ ነገሮችን ያደርጋሉ ያሳዝኑናል ያስከፉናል ልባችንን ይሰብሩናል ግን ለእነዛ ሰዎች በተናገሩን መጠን እየ መለስን ከሄድን ከእነሱ ያልተሻልን ሆነን እንገኛለን። እዚህ ምድር ላይ ማንም ትክክል የለም ሁላችንም ስህተት ሰርተናል ሌሎችን በሰሩት ነገር መሸሽን ምርጫ አድርጌ አላውቅም ምክንያቱም ሰውን በስራው መመዘን ተገቢ ነው ብዬ ስለማላስብ። አንዳንድ ሰዎች ማሳየት እሚፈልጉትን ብቻ ነው እሚያሳዩት እንጂ እውነተኛ ማንነታቸውን አደለም.... ውጫቸው ጭቅይት ብሎ ውስጣቸው ግን ልክ እንደ ነጭ ወረቀት የሆነ ብዙዎች አሉ.....እኔም እነ ሊድያ ምንም ያህል ቢያስከፉኝም ቢሰብሩኝም ውስጣቸው ግን ለማንም ማሳየት እማይፈልጉት መልካምነት ያለ ይመስለኛል....ምናልባት እንዲህ መጥፎ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ምክንያት ይኖር ይሆናል። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ወደ ውስጥ ገብቼ እናቴን
ሰላም ካልኩኝ በኋላ ስልኬን አጠፋፍቼ ተኛሁኝ። ለሊት ላይ እንደመባነን አድርጎኝ ነቃሁኝ....ለምን እንደሆነ ባላውቅም ውስጤን ሰላም እየተሰማኝ አደለም..... ስልኬን ከፍቼ ሰዓቱን ስመለከት ከሌሊቱ 9:20 ይላል ምክንያቱን ሳላውቀው እንዲሁ እንዳፈጠጥኩኝ ነጋ። በዚህ ስሜት ወደ ስራም ሆነ ወደ ግቢ መሄድ ስላል ፈለኩ ወደ ቤተክርስቲያን ሄጄ እዛ አረፍ አልኩኝ.....ከጎኔ ሶስት በእድሜ ገፋ ያሉ ሴቶች ተቀምጠዋል አባ እያስተማሩ ንግግራቸው ሀሳቤን ሰርቆት አስተምሮቱን ትቼ እነሱን ማዳመጥ ጀመርኩኝ....ከንግግራቸው እንደተረዳሁት በቅርቡ ስላበደው የሰፈራችን ወጣት ነው እሚያወሩት ልጁን ስለማውቀው ነው የአባን አስተምሮት ትቼ እነሱን እምሰማው...... ስንታየሁ ይባላል እናት እና አባቱ እሱን ከመውለዳቸው በፊት ልጅ እምቢ ብሏቸው ያልገቡበት ጉድጓድ አልነበረም.....መፍትሔ ይገኛል ወደ ተባሉበት ሁሉ ነበር እሚሄዱት.....የሰፈሩ ሰው እርግማን ቢኖርባቸው ነው.. የቤተሰብ ጣጣ ነው.. ከሷ ነው.. ከእሱ ነው ችግሩ.. እያሉ የየራሳቸውን መላምት ያስቀምጡ ነበር....መቼስ ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም አይደል ከእነ አባባሉስ የለመኑት ፈጣሪያቸው አላሳፈራቸውም ስንቴን ሰጣቸው...ብዙ ያዩበት የተገፉበት የተንከራተቱበት ልጃቸው ስለሆነ ስንታየሁ አሉት። ግን እግዜር አልፈቀደምና እንዳለመታደል ሆነ ስንቴ በተወለደ በ አንድ አመቱ እናቱ ሞተች.....የሰፈሩ ሰውም ገፊ የሚል ለማሰብ እንኳን እሚሰቀጥጥ ስም ሰጡት እናቱን ገፍቶ የገደለ እያሉ በልጅ ዓዕምሮህ መጥፎ ጠባሳን ጣሉበት ....አባቱም ልጁ ይህ ንግግራቸው እንዳይጎዳው እና ቦታ እንዳይሰጥ የተቻለውን ያህል ቢጥርም አልተሳካለትም።


ስንቴ ከሰፈር ልጆች ጋር ለመጫወት ሲወጣ የልጆቹ ወላጆች እሱ ገፊ ነው ይገላችኋል... ጠንቋይ ነው እያሉ ከሱ ያርቋቸው ነበር። አስራ ሰባት አመት ሲሞላው
አባቱ በልብ ድካም ህይወታቸው አለፈ....በዛ ሰዓት ለስንቴ ህይወት ቀላል አልሆንለት አለው የሰፈሩ ሰው ጥላች እናት አባቱን ሳይጠግባቸው መሞታቸው ችግሩን እሚያካፍለው ጓደኛ ማጣቱ ውስጡን ሰበረው.... ጠንካራ ሆኖ ለመኖር ቢጥርም ዳገት ሆነበት። እራሱን በሱስ ውስጥ ደበቀ ማጨስ ፣ መጠጣት የዘወትር ስራው ሆነ.... ከዛም አንዲት ሴት ህይወቱ ውስጥ ገባች ከሱስ እንዲላቀቅ እና የተሻለ ህይወት እንዲኖር እረዳቸው እየተለወጠ መጣ.... ዛሬም ግን የሰፈሩ ሰው እሷንም ደሞ እንደ እናት አባትህ ልትገድላት ነው እያሉ ያሽሟጥጡት ጀመር.... ፍቅረኛው ለእንደዚህ አይነቱ ንግግር ቦታ ሳትሰጥ ከስንቴ ጎን ቆመች ሊጋቡ ሽር ጉዱ እያሉ ባሉበት ሰዓት እሷም በመኪና አደጋ ህይወቷን አጣች። ይሄኔ ከእናንተም መሃል እውነትም ገፊ ነው እሚል አይጠፋም ግን የሱ ጥፋት ምኑ ላይ ነው በእግዜር ስራ እኛ ምን ቤት ነን ማነው ፈራጅ ያደረገን.... ያለ ጥፋቱ እንዴት ይወቀሳል እንዴት ይገፋል ? ከእሷ ሞት በኋላ ይሰፈሩ ሰው ዳይኖሰር እንዳየ እሱን ሲያዩ ይሮጡ ጀመር ከእሱ በእድሜ እሚያንሱ ህፃናት ሰፈር ውስጥ ሲያዩ ስንታየሁ ገፊ ስንታየሁ ሰይጣን እያሉ ያሾፉበት ነበር። ሱሰኝነቱ ከበፊቱ ተባባሰ እራሱን መጣል ከቤቱ ውጮ መንገድ ዳር ማደር ጀመረ። ከእዚህ ሁኔታ እንዲወጣ ከጓደኞቼ ጋር የተቻለንን አድርገናል ሳይሆን ቀረና የሰዉ ንግግር የእናት አባቱ ሞት ህይወቱን የቀየረችለት ያፈቀራት ሴትን ማጣቱ ዓዕምሮውን ያስጨንቀው ጀመር እየቆየ ጨረቁን አስጥሎ አሳበደው። ታዲያ የዚህ ልጅ ጥፋት ምንድነው መርጦ አልተወለደ ይሄ የእግዜር ውሳኔ እንጂ የሱ አልነበረም እኮ ለምን ይሄን ያህል ይጠላል ለምን ይሄን ያህል ይገፋል ደስተኛ ሆኖ መኖር እሚችልን ሰው በዚህ መንገድ እቅልን ማሳት ነው ትክክለኛው ፍርድ ንገሩኝ እስቲ የሰውን ተስፋ ነገውን እያጨለሙ ነው አብሮነትን ማሳየት ? በእሱ እንደዚህ መሆን ማን ተጠቀመ ? የማን ህይወት ተቀየረ ? አንዳንዴ ሰዎችን መጥቀም መርዳት ባንችል ምናለ የራሳቸውን ህይወት እንደራሳቸው ፍቃድ እንዲኖሩ ብንተዋቸው ? ጥቅም ለሌለው ነገር ለምን ሌላን ሰው እንጎዳለን ? ጥሩ ባንሆንላቸው መጥፎ መሆን ለምን ያስፈልጋል ? በተደጋጋሚ ከእነ ሳቢ ጋር ሆስፒታል ልንወስደው ብንሞክርም አልተሳካልንም ልብስ እና ምግብ እየያዝን አብረነው ውለን እመጣለን። ዛሬም ገፊ እንደሆነ እና የቤተሰብ ጣጣ ቤተሰቡን እንደነጠቀው ፣ እንዳሳበደው ሲያወሩ ስሰማ ነው ፀሎቴን ትቼ እነሱን ማዳመጥ የጀመርኩት። በሰው ለመፍረድ ያለንን ችክሉነት ለማወቅ ብንጠቀመው የት በደረስን....እራሴን ለማረጋጋት ብዬ ብመጣ ጭራሽ ከበፊቱ የባሰ ተበሳጨሁኝ...እዚህ ቆይቼ በአላስፈላጊ ንግግር ሀጥያት ከምገባ ምንም ሳልናገር ተሳልሜ ወጣሁኝ። እምሄድበት ሲጠፋኝ ማይለፍ ጋር ደወልኩለት......



ይቀጥላል.........



ለአስተያየት - @Yetomah_Bot


✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯