Get Mystery Box with random crypto!

ከፎቶሽ ፍሬም ስር (በድሉ ዋቅጅራ) መስኮቱ መቃን ላይ . . . ጠብ ! ጠብ ! ጠብ ! ከደጃፍ | ቅኔ እና ጦቢያ

ከፎቶሽ ፍሬም ስር (በድሉ ዋቅጅራ)
መስኮቱ መቃን ላይ . . .
ጠብ !
ጠብ !
ጠብ !
ከደጃፍ
ቅርንጫፍ
ጠፈጠፍ ይወድቃል፡፡
***
ከመስኮቱ ወዲያ፣ . . .
ብልጭ!
ትርትር!
ስንጥቅ!
ኮረብታው አናት ላይ፣
በብርሀን ጣቱ እየኮረኮረ፣
ደመናውን ሊገፍ
ጭጋጉን ሊያስቀው
አድማስ ይታገላል፡፡
***
ከመስኮቱ ወዲህ፣ . . . .
ከፎቶሽ ፍሬም ስር
በክረምት ውቅያኖስ
የበጋ ደሴት ነው
የʽኔ ቤት ይሞቃል፡፡
***
ከመስኮቱ ወዲያ፣ . . .
ዝናቡ ቢቆምም . . .
የዣንጥላ
ዱላ
እየወዘወዙ፤
በልብስ ተጀቡነው፣
ካቦርታ ደርበው፣
በሀሳብና እግር፣ ጥምረት ʽሚጓዙ፤
ሰዎች ይታያሉ፡፡
***
ከመስኮቱ ወዲህ . . .
ከፎቶሽ ፍሬም ስር፣
ሳሎን መሀል ቆሜ፤
ጥቅምት ነው ለʽኔ፡፡
ከፎቶሽ ስር ቆሜ፣
በመስኮት የማየው፤
ድጡ ለምለም ንጣፍ፣
ሙጃው አበባ ነው፡፡
የመስቀል ወፍ ስትበር
የቀዘፈችው አየር
የአደዩን መአዛ
ጎጆዬ እየነዛ
ትፍስህት ʽሚያድለኝ
በሀምሌ ጭለማ፣
ጥቅምት ደሴት ውስጥ
ከፍሬምሽ ስር ነኝ፡፡
ባትኖሪም፡፡
---------
@kene_tobeya
@kene_tobeya