Get Mystery Box with random crypto!

[ Photo ] በተያየን… ብልጭ ድርግም - ጅምላው ላይት ብርዝ ድብዝዝ - ፍኩን ስሜት ከቀን | ቅኔ እና ጦቢያ

[ Photo ]
በተያየን…

ብልጭ ድርግም - ጅምላው ላይት
ብርዝ ድብዝዝ - ፍኩን ስሜት
ከቀን እኩል - ደግሞ ምሽት
አንፀባርቆ - ለማሳየት
ብልጭ ድርግም - ጅምላው ላይት…(2×)

በበርኖሱ - ውስጠ ብርሃን
በቁር ብርዱ - ነዲድ ምራን
በሬት ልኩ - ብሶ ጣዝማን
በጣር ስሙ - ሃሴት ብርማን
ቀርቶ ጀምበር - ደግማ ሳጠልቅ
ከቋፍ አፋፍ - ፍቅር ሳትወድቅ
በተ*ጠለግ - ስንኳ ፀዳል
ምንም ቢመሽ - ሰርኳ መሃል
እኔ ያንቺ - አንቺ የኔን
ውስጠ ወርቋ - ስውር ቃሏን
ውል ቋጠሮ - ማቋን ፈተን
በጅም ብርት - ውስጥም ቢሆን
በፀዳሏ - በተጣፋን…
በፅልመቷም - በተያየን… ።


@mesele11
please share, and join us
https://t.me/kene_tobeya