Get Mystery Box with random crypto!

በሀገራችን፡ፍትህ፡ስደተኛ፡ናት። ከሰው፡ልብ፡ሸሽታ በገዥዎች፡ሸንጎ | ቅኔ እና ጦቢያ

በሀገራችን፡ፍትህ፡ስደተኛ፡ናት።
ከሰው፡ልብ፡ሸሽታ
በገዥዎች፡ሸንጎ
ጥገኝነት፡የምትጠይቅ
ደጅ፡ጠኝ፡ሆናለች።
ራስ፡ወዳድነት፣አስመሳይነት፡እና
ስስት፡ተበራክተው፡ፍትህን፡አደቀቋት፤
ደበደቧት። መውጫ፡መግቢያ፡ነሷት።
ሸሸች። ከሰው፡ልብ፡ጠፋች።
ከሜዳ፡ሜዳ፡ስትዞር
ከመንግስት፡ስር፡መጠጊያ፡አገኘች።
መንግስት፡ደግሞ
እንደማንኛውም፡ስደተኛ
ንብረቱ፡አደረጋት፡፡
ሲያሻው፡ሰጥቶ
ሲያሻው፡የሚነፍጋት፡ሆነች።
ሰው፡ከልቡ፡ያለውን፡ፍትህ፡አባርሮ
መንግስትን፡መልሰህ፡ስጠኝ፡ቢል
ከየት፡ይሰጠዋል?

ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ
@kene_tobeya