Get Mystery Box with random crypto!

ታሪክ በሚጠራን በድሉ ዋዜማ በነፃነታችን ወር ዓለምን በሚመራው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን በልባችን | ቅንድል ዲጂታል መጽሔት Kendel Digital Magazine

ታሪክ በሚጠራን በድሉ ዋዜማ በነፃነታችን ወር ዓለምን በሚመራው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን በልባችን ቅንነት ፣ በአንደበታችን ምክንያታዊነትን ፣ በተግባራችን ሀገር ፍቅርን ወርሰን በብዕር ትሩፋት በቅንነት ድል ልንነሳ ጉዞ የጀመርነው በየካቲት ወር ከ3 አመት በፊት ነበር። በቁጥር በዝተን ፣ በሀሳብ ገዝፈን ከተሰነደችው መፅሔታችን ላይ በልዩ ይዘትና መልክ በድህረገፅ ወደ እናንተ ለመቅረብ በቅተናል።
በጉዟችን አብራችሁን ለነበራችሁ የመፅሔታችን አንባቢያን ብርታታችን ስለሆናችሁ ከልብ እያመሰገንን ተደራሽነታችንን ለመጨመርና ይበልጥ ወደናንተ ለመቅረብ በድህረ ገፅ ስራ መጀመራችንን በደስታ አንገልፃለን።

ድህረ ገፃችንን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
www.kendelmagazine.com

ቅንነት ድል ያደርጋል!
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት