Get Mystery Box with random crypto!

እየወደቀ ያለው የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም  (BRI፣ B3W እና Global Gateway) (የዐዲስ | ቅንድል ዲጂታል መጽሔት Kendel Digital Magazine

እየወደቀ ያለው የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም 
(BRI፣ B3W እና Global Gateway) (የዐዲስ ኢኮኖሚ ሥርዐት ውልደት መባቻ (?)


 ( በ ዶ/ር ፀደይ ወንድሙ )

የኮሚውኒስቱ ጎራ አሜሪካንን ኢምፔሪያሊስት ናት ሲላት ቆይቷል (ከነአባባሉም "ኢምፔሪያሊዝም ይውደም" ነበር)። ለአሜሪካዊያን ግን ራሳቸውን እንደ ኢምፔሪያሊስት ማሰብ ሩቅ ነበር (“Americans are not in the habit of speaking of themselves as imperialistic” ሲል ይገልጸዋል ፖል ቫርግ “Imperialism and the American Orientation toward World Affairs” በተሰኘ መጣጥፉ (እ.አ.አ. በ1966 የተጻፈ ነው))። የአሜሪካንን ኢምፔሪያሊስትነት በተመለከተ በአሜሪካን ምሁራን መካከል ጥቂት ክርክሮች የነበሩ ቢኾንም፣ በአሜሪካ የትምህርት ሥርዐት ውስጥ ከመጀመሪያ ዲግሪ የፖለቲካ ሳይንስ ጥናት ጀምሮ አሜሪካንን እና ኢምፔሪያሊዝምን ማገናኘት ከ"ሙሁራዊ" ክበብ ማፈንገጥ ተደርጎ ይታያል። ይኽንን የሚነግረን ሚካኤል ፓረንቲ፣ እ.አ.አ. በ1995 አንድ መጽሓፍ አሳተመ፣ Against Empire የተሰኘ። ይኽ መጽሓፍ ከወጣ በኋላ የብዙዎች ዐይን የተከፈተ ይመስላል። 
እንደፓረንቲ ከኾነ የኢምፔሪያሊዝም አስተሳሰብ እና ድርጊት ለረጅም ጊዜ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የዘለቀ ቢኾንም፣ ከአሜሪካ ጋር እንዳይያያዝ በተለያዩ አገላለጾች ሲሸፋፈን ቆይቷል፦ ለምሳሌ በግዛትነት የተያዙ አገራትን ("empires"ን)፣ "commonwealth"፣ "dominion" ወይም "territory" ብሎ በመጥራት፤ ወይም ደግሞ ግዛት ለማድረግ ጦርነት ሲደረግ ሰበቡን "አገር ለመከላከል"፣ ለ"ብሔራዊ ደኅንነት"፣ እና "መረጋጋትን ለማስጠበቅ" በማድረግ።
የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ከመቶ ዓመታቶች በፊት ከነበሩት ኢምፓየሮች የሚለየው ካፒታሊስት መኾኑ ነው። ከረጅም ጊዜ በፊት የሚደረጉ የግዛት ማስፋፋቶች ሃብት ለመዝረፍ፣ ለማስገበር፣ የወርቅ ማዕድን ለመሰብሰብ ወይም ለክብር የሚደረግ ነበር። ካፒታሊስታዊውን የሚለየው ግን፣ በሚስፋፋባቸው አገሮች ላይ በአነስተኛ ክፍያ ጉልበትን በመበዝበዝ እና በገበያ ሥርዓታቸው ውስጥ ሰርፆ በመግባት ካፒታልን ወደራሱ ስለሚያከማች ነው። ካፒታል የሚያከማቸውም በሚይዛቸው አገሮች ላይ ኢንቨስት በማድረግ፣ በኢኮኖሚያቸው፣ በባህላቸው እና በፖለቲካ ሥርዓታቸው ላይ የበላይ በመኾን የምርት ሥርዓታቸውን ከዓለም ዓቀፍ ገበያ ጋር በማስተሳሰር ነው።  
Continue Reading