Get Mystery Box with random crypto!

ምክር ቢጤ ለ ፍሬሾች ቀለሜ(@keleme_2013) ስርቆት ጋር በተያያዘ ሚላችሁ ነገር አለ አንብ | ቀለሜ

ምክር ቢጤ ለ ፍሬሾች

ቀለሜ(@keleme_2013) ስርቆት ጋር በተያያዘ ሚላችሁ ነገር አለ አንብቡልኝ እማ....

ግቢ ውስጥ

አሁን ባላችሁበት Condition dorm ውስጥ እስከ ምትላመዱ ድረስ ማንንም ማመን አትችሉም ማንንም። ስለዚህ እንዝላል አትሁኑ... ልብሳችሁን ፣ጓዛችሁን ሎከራችሁ ውስጥ ቆልፉ፤ በፍጹም ስልክ Charger አድርጋችሁ እንዳትወጡ ትበላላችሁ even ጓደኛየ Fresh እያለን ቻርጅ አድርጓ ተኝቶ ጥዋት ሲነሳ ስልኩ የለም ...ዶርም ውስጥ ያሉ ጓደኞቹን በሙሉ ቢጠይቃቸው አላየንም ነው ያሉት ቢከሳቸውም ምንም መፍትሄ አላገኘም ። ብቻ አንዴ አትበሉ እንጅ ከተሰረቃችሁ ምንም መፍትሄ የለም።
ሌላው ከዚህ ላይ ማንሳት የምፈልገው የDorm ቁልፍ ቀድሞ ከ dormu አባል ለመጣው ልጅ አንድ ብቻ ስለሚሰጣችሁ እንደፈለጋችሁ Dorm ውስጥ መግባት መውጣት ላትችሉ ትችላላችሁ ፤ ልጁ ሳይኖር ሲቀር ሁሌ እየደወላችሁ ና ክፈትልኝ ማለት ያሰጠላችኅል ። ይሄን ለማስቀረት ስትሉም ቁልፏን በሩ ታች ስር እያስቀመጣችሁ ትሄዳላችሁ ይህ ትልቅ ስህተት ነው almost all በሚባል መልኩ ይችን ሙድ ሁሉ ያውቃታል እናንተን መስረቅ የሚፈልግ አካል መጀመሪያ በደንብ ነው የሚያጠናችሁ ከዛ መውጣታችሁን ጠብቆ ታች ቁልፏን አግኝቶ ቢገባስ?......እሽ ማድረግ ስላለባችሁ ወደ መፍትሄው እንሂድ

1 ህጋዊው መፍትሄ

ቁልፍ የያዘውን ልጅ ቁልፍ በመቀበል እየተቀባበላችሁ መጠቀም። ግን ይሄ በጣም አዝግ ነው አስባችሁታል ሁሌ እሱን እየጠበቃችሁ ....

2 ህጋዊ ያልሆነው መፍትሄ

ቁልፍ ማስቀረጽ ...ይሄን ሁሉ ተማሪ የሚያደርገው ነገር ነው። ከ University አቅራቢያ ስራየ ብለው የሚጠብቋችሁ ቁልፍ ቀራጮች አሉ ከነሱ Original ቁልፍን በማስቀረጽ የራሳችሁን መያዝ ትችላላችሁ ሁነኛ መፍትሄ ነው። ግን ፕሮክተር ከያዛችሁ .... ልትፈርሙ ትችላላችሁ ከባድ Risk አለው።

ከግቢ ውጭ

fresh አደላችሁ ከተማውን ለማየት ከ ግቢ መውጣታችሁ አይቀርም ...ግን አደራ ብቻችሁን ላለመውጣት ሞክሩ በስርቆት PHD ያላቸው localሎች እናንተን እየጠበቁ ነው ፣ ድንቅ ቴክኒኮችን ተጠቅመው እንዴት እንደሚሸውዷችሁ አታውቁትም .... ስልካችሁን ፣ብራችሁን በ ፍቃደኝነት አስረክባችሁ ነው ምትመጡት። የምሬን ነው ምላችሁ ጓደኛየን እንዴት እንደበሉት ብነግራችሁ አንድ ሙሉ ድርሰት ይወጣዋል በ group ሁነው Drama ሰርተው እንዴት እንዳሳመኑት እነሱ እና ፈጣሪ ብቻ ነው ሚያውቀው ስልኩ የለ ብሩ የ እጅ ስሀቱ ሳይቀር አስረክቧቸው የመጣ። እና ለግዜው ከ localoch ብትርቁ መልካም ነው።ዘው ብለው እራሳቸው መጠው ካወሯችሁ ጠርጥሩ.....

የቤተሰብነቴን እንዲህ አልኀችሁ መልካም ቀን!!

 ━━━━━━━━━━━━━━━━━
••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Keleme_2013
@Keleme_2013