Get Mystery Box with random crypto!

† † እንኳን ለጻድቁ አባታችን አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ | ✞ገድለ ቅዱሳን✞

† † እንኳን ለጻድቁ አባታችን አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ †††

††† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ በበርሃ ሰው ሳያዩ ለ70 ዓመታት በቅድስና ኑረዋል:: በጊዜውም እግዚአብሔር አባ አብዱልማዎስን ወደ አባ ዕብሎይ ልኳቸው ነበር:: ሁለቱ ተገናኝተው አብረው ለ3 ቀናት ሲቆዩ ቅዱስ መልአክ እየተገለጸ አጽናንቷቸዋል:: ከሥውራን ማኅበርም ተቀላቅለው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለዋል::

††† አባ ዕብሎይ ሲያርፍ አንበሶች እያገዟቸው ቀብረዋቸዋል:: እርሳቸውም "እኔን የሚቀብረኝ ስጠኝ" ብለው ጸልየው ነበርና 3 ገዳማውያን መጥተውላቸዋል:: የካቲት 5 ቀን አባ ዕብሎይን ገንዘው ቀብረው በ3ኛው ቀን አርፈዋል::

††† የጻድቁ ክብር ይደርብን።

††† የካቲት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ
2.አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
3.አባ እለ እስክንድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
4.ቅዱስ አባዲር

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ

††† የአብ በረከት: የወልድ ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስ አንድነት: የድንግል ማርያም ምልጃ: የቅዱሳኑ ፀጋ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

††† "ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ::"†††
(ማቴ. ፭፥፲)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††