ማለፍ እውነተኛ ታሪክ ማኔ ክፍል | ከፍቅር ማህደር
ማለፍ
እውነተኛ ታሪክ
ማኔ
ክፍል
በቃ እንደመጣች ከኋላ ነው ፀጉሯን ያየሁት እሷ ቆማ ለride ብር እየከፈለች እኛ ከኋላዋ ቆመን ነበር።
ቀይ ትሁን ጥቁር ቆንጆ ትሁን አስቀያሚ ሳላያት እኔ ያንተ ወንድም ፍዝዝ ብዬ ቀረሁልህ።
ገና ፊቷን ሳታዞር አጠገቤ ያለችው ልጅ ደበረችኝ ነው ምልህ።
ፊልም የምሰራ ይመስል አፌን ከፍቼ እያየኋት ዞራ ሁላችንንም ሰላም አለችን አቤት የሰው ልጅ እቅፍ እንዲህ ይሆናል ስታቅፈኝ ባትለቀኝ ብዬ ተመኘሁ።
ወደክለቡ ለመግባት መንገድ ስንጀምር ከሷ ኋላ ኋላ ስከተል አደናቅፎኝ ልደፋ ስል እኔን ብላ መጥታ ስደግፈኝ ሰውነቴን ወረረኝ ነው ምልህ።
አባቴ ያቺን ክፍተት አገኘሁልህና እኔ ያንተ ወንድም ልጅቷን እያሽኮረመምኩ ሙዳችን ገጥሞ ፏ እያልን አመሸን አንዴ ወንበር ስቤ ሳስቀምጣት አንዴ ሳስደንሳት ቆየሁና ወደሽንት ቤት ሄድኩልህ ስመለስ ከጓደኞቼ መሀል የለችም የት ሄደች ብዬ እሷን ፍለጋ ወደውጭ ስወጣ ጀርባዋን ለኔ ሰጥታኝ ስልክ እያወራች ተመለከትኳት።
ጠጋ ብዬ ከጀርባዋ አቀፍ አድርጌ አንገቷ ስር ሳም ሳደርጋት ወደኔ ዞረችና አንተ ባለጌ ከፍቅረኛ ውጭ አንገት ስር ይሳማል እንዴ ብላ ተቨሽኮረመመች ።
ምናልባት ፍቅረኛዬ ብቶኝስ ማን ያውቃል ብዬ መጠጡም ገፋፍቶኝ ከንፈሯን ግጥም አድርጌ ሳም አደረኳት።
ምንም ሳትለኝ አልፋኝ ወደውስጥ ገባች ተከተልኳት::
ውስጥ ከገባች ቡሀላ አብረን መጨፈር ጀመርን ስትስቅልኝ ደስ አለኝ መሰለኝ ድጋሜ ግጥም አድርጌ ሳምኳት እሷም አልተቃወመችኝም ተመቻት መሰለኝ እቅፌ ውስጥ ገብታ ነገር አለሙን እረሳችሁ።
የሚገርምህ በመሀል ቤቱ በፖሊስ ተጥለቀለቀ ድንገተኛ ፍተሻ ይደረግ ተብሎ ህዝቡ ሲርበተበት ጓደኞቻችን ሳይቀሩ ሚገቡበት ሲጠፋቸው እኔና እሷ ተቃቅፈን አይን አይኗን እያየኋት ፖሊስ መኖሩን እራሱ ዘንግቼው ነበረ።
ከሌሊቱ አምስት ምናምን ላይ ቤት እንቀይር ተብሎ ወደሌላ ቤት አመራን እዛኛው ቤትም ሰው ሁላ ትኩረቱ እኛ ላይ እስኪሆን ድረስ መሀል ገብተን ሁላታችን እብድ ስንል አመሸን ታቃለህ አብሮ አደጌ የሆነች ያክል ነው የተሰማኝ አለ አደል እረጅም አመት አብሮ የኖረ ሰው ባንዴ ሰው ፍቅር ይይዘዋል እንዴ አፈቀርኳት ነው ምልህ ከዛ ግን ስድስት አካባቢ ተደጋጋሚ ስልክ ለማውራት ወደውጭ እየወጣች ነበር በመሀል ስትቆይብኝ ላያት ስወጣ የሆነ መኪና ውስጥ ገብታ ስትሄድ አየኋት።
.
.
ይቀጥላል
ክፍል ከ️ Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ሼር ማድረግ አይርሱ።
ይ ላ ሉን!
https://t.me/+8_qLreasnHUxN2U0
https://t.me/+8_qLreasnHUxN2U0