ሀይስኩል ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ፊደል                        | ከፍቅር ማህደር

    ሀይስኩል

ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ

ፊደል


                        ክፍል

........ክው ብየ ደርቄ ቀረሁ ። በሰአቱ ራሴን የትም ሆነ እንዴትም ልደብቅም ሆነ ከአቶ ሰለሞን ልደብቀውም ሆነ እንዳያየኝ ላደርግ አልችልም!!!
በሰአቱ ያለኝ አማራጭ ቆሞ መጠበቅ ነበር !!
ልክ አባቷን በጉጉት እንደምጠብቅ ህፃን ልጅ በር በሩን እያየሁ ቆሞ መጠበቅ ነበር !!!
የልጁን ጤንነት ለማየት ተቻኩሎ የመጣው አባት ከዶክተሩ ጋር እያወራ በሩን ክፍት አድርጎ ገባ ።
ያቤፅ ደግሞ ከዃላ በድንጋጤ ቆሞ ምን ላርግ??? በሚል ፊት ይመለከተኛል !!!!
እኔ ከደነገጥኩት ባልተናነሰ ሁኔታ እሱም ደንግጧል ።
ለምን እንደዛ ሊለየን እንደፈለገ ባላውቅም የአመታት ጠላቱን እንዳየ ደመኛ ቀጥ ብሎ ቆሞ ፊቱን አጨማዶ ያየኛል !!????
ምን እንደማረግ ምን እንደምል የማላቀው እኔ አሁንም ግራ በመጋባት ስሜት ተሞልቼ ቆሜ እያየዃቸው ነው !!!!!


መፍትሄው እንደሆነ ሳናወቅ በመፋጠጥ ብቻ ደቂቃዎችን አባከንን !!!
ከዛም በቀስታና ግርማ ሞገስ በተላበሰ አረማመድ ወደኛ መምጣት ጀመረ።
ለዛ ቀን ሲባል የቤት ግድግዳ በአንድ በኩል ክፍት ቤሆን ኖሮ ብዬ ተመኘው !!!!!
እሱም አልበቃ ብሎ ምን አለ መሬት መደበቂያ ቦታ ቢኖራትም ብዬ ተመኝቻለሁ !!!!
ፊቱ ቀለል ያለ እና መልከ መልካም ቢሆንም ከዚ በፊት የተለያየንበት ሁኔታ ጥሩ ስላልነበረ እፈራዋለሁ !!!
አጠገቤ እንደደረሰ በጥፊ የሚያጋጨኝ መስሎ ተሰማኝ !!!!


ያቺ ትንሽ ቤት ራቀችብኝ ። !!!!!!
ከበሩ እኔ ጋር እስከሚደርስ ያለው ርምጃ ረዘመብኝ !!!!!!
ከስንት የልብ ምትና ፍራቻ ቡሀላ አጠገቤ ደረሰ ።
በቤኪ በግራ በኩል ቆመ ። እኔ በቤኪ በቀኝ በኩል ቆሜ እያጎረስኩት ነበረ !!!!
በስተመጨረሻም ፊት ለፊት ተፋጠጥን !!
" እዚህ ምን ታደርጊያለሽ ??""  ብሎ ዝምታውን ሰበረው ።
እ አይ እ ... እያልኩ የ አ ቤት ፊደላትን ጥሪ የተባልኩ ይመስል እ አይ እ እያልኩ እቀባጥራለሁ !!!!
" ባለፈው ቀን አላደመጥሽኝም መሠለኝ !!" አለኝ ።   አሁንም የኔ መልስ ዝምታ ነው
በኩራት ከጁ ላይ ሰአት እየተመለከት
" ብዙ ሰአት የለኝም ግን እባክሽ ብቻሽን ላናግርሽ " አለኝ ?????

አሁን የበለጠ ፈራሁኝ ። !!!!!ግን አሁንም ቃል አላወጣሁም ዝም ብዬ አየዋለሁ ።
" እባክሽ " አለ እጁን ወደ በሩ እየዘረጋ ።
ምን ያርገኝ ምን ይበለኝም ሳላውቅ ቀጥጥጥ ብዬ ወጣሁ ።
ከዛ እጆቼን አጣምሬ አይኔን መሬቱ ላይ ተክዬ ቀረሁኝ ።
ከዃላይ ቀስ ብሎ መጣና ፊት ለፊቴ ግትር አለ ።
"  የምትፈልጊውን ያሆል ገንዘብ እሰጥሻለሁ ስንትም ይሁን የአንቺንም የእናትሽንም ህይወት የምትቀይሪበት ገንዘብ ልስጥሽ ብቻ ከልጄ ራቂ "" አለኝ ???!!!!
ጭራሽ ያልጠበኩት ንግግር ነው ።
ሰው ሲያከብረኝ ነው የማከብረው ።
የነበረውን ሞገስ በአንዴ አጣ !!!!
ለሱ የነበረኝ ክብር ዝቅ ሲል ቀና ብዬ ተመለከትኩት !!!!!
ምን ማለት ነው ፍቅር በገንዘብ አይገዛም እሺ ?!!!!!!!
አለምዬን በገንዘብ ነው የገዛሀት እንዴ እ !!!!!
ሌላ ሰው እንዳይሰማ !!!
እኔ ማንነቱን እንጂ ያለበት ደረጃን ወይ ሌላ ነገሮች አደለም የወደድኩት !!!
ብዬ ተመልሼ ስገባ ...........


.
.

ይቀጥላል


ክፍል ከ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።

ይ ላ ሉን!

 
https://t.me/kefikirmahider
ከፍቅር ማህደር

ከፍቅር ማህደር

@kefikirmahider
134.24K ተመዝጋቢዎች
መዝናኛዎች ምድብ
𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 t̑̈ȏ̈ ከፍቅር ማህደር❤ 💙በዚ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ላይ 💜ድርሰቶች 💚የፍቅር ግጥሞች 💛ጣፋጭ ታሪኮች ❤️...