Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ ታሪክ.. ስታነቡ በትክክል አንብቡ!! ጨርሶ ማንበብ ግድ ነው!!! አስገራሚ ክስ | ከፖስቱ ኮሜንቱ በኛ 😂😜

አሳዛኝ ታሪክ.. ስታነቡ በትክክል አንብቡ!!
ጨርሶ ማንበብ ግድ ነው!!!

አስገራሚ ክስተት ከሳዑዲዋ ሪያድ ከተማ! የዱባይ ከተማ ፖሊሶች አዲስ መኪናውን እያፀዳ ያለን አንድ ሰው በቁጥጥር ስር አዋሉ!! ነገሩ እንዲህ ነው.. ይህ ሰውዬ መኪናውን እያፀዳ በነበረበት ወቅት የሁለት አመት ህፃን ልጁ አጠገቡ ያለውን መዶሻ አንስቶ መኪናውን በመዶሻ እና በሚስማር እየመታ መኪናው ላይ ቅርፅ እያወጣ ነበር ይህ ክስተት በሰዓቱ አባትየውን በጣም አስገርሞት ነበር! ይህ አባት መኪናውን ሲያየው በጣም ተበላሽቷል።

እሱ እንደዛ ደክሞ ያፀዳውን መኪና ልጁ በመዶሻ ቀጥቅጦ መሰባበሩ አባትን ክፉኛ አበሳጨና | በንዴት ልጁን መምታት ጀመረ !!!በቁጣ የታወረው ይህ አባት የልጁን ጣት በመዶሻ እየቀጠቀጠ መሆኑን ከብዙ ቆይታ በኋላ ነበር ያስተዋለው። ወዲያውኑ ተደናግጦ ልጁን ወደ ሆስፒታል ይዞ ከነፈ። ሆኖም የልጁ ጣት ከመቆረጥ አልተረፈችም ነበር የሆነው ሆኖ አባት ልጁ ወዳለበት ክፍል ሊያየው ሄደ። ይህ ህፃን ልጅ ገና አባቱን እንዳየ "አባዬ ጣቴ መቼ ነው የሚበቅለው? " ብሎ ጠየቀው።

የዚህ ልጅ ንግግር አባትየው ላይ እንደመብረቅ ነበር የወረደው!! ወዲያውኑ ከሆስፒታሉ ወጣና መኪናዋ ወዳለችበት ቦታ ሄዶ ቀጥቅጦ ሰባበራትና ፊት ለፊቷ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። በሰራው ነገር ቁጭት ይዞት እያነባ እያለ ልጁ መኪናዋን ሲቀጠቅጥ ወደ ነበረበት ቦታ አስተዋለ። " አባቴ እወድሃለሁ" ይላል ፅሁፉ!! ይህን ሁሉ ከባድ የሀዘን ስሜት መሸከም ያልቻለው አባት በቀጣዩ ቀን ራሱን አጠፋ። እስቲ ታሪኩን ከመጀመሪያው ጀምረን እንገምግመው!

- እንዴት አንድ ሰው መኪናውን በመዶሻ ያፀዳል??
- ሲጀመር መዶሻ እና መኪናን ምን አገናኛቸው??
- እንዴት ብሎ ነው የሁለት አመት ህፃን ልጅ አባቴ እወድሃለሁ" ብሎ የሚፅፈው??
- የዱባይ ከተማ ፖሊሶች ሪያድ ላይ ስለተፈጠረው ነገር ምናባታቸው አገባቸው?
- ሲቀጥል ሰውዬው ራሱን አጥፍቶ ከሆነ የዱባይ ፖሊሶች እንዴት በቁጥጥር ስር አዋሉት??.. ኧረ ወገን እያስተዋልን እናንብብ ቡዙዎቻችን ሰዓታችንን የምናባክነው እንደዚህ በማይረቡ ነገሮች በመጠመድ ነው። ዝም ብለን የምንነዳ ከሆነ ማንም ሰው በቀላሉ ትኩረታችንን መስረቅ ይችላል። ኧረ እባካችሁን ሰዎች የማንም መጫወቻ አትሁኑ! የዛሬ ትምህርታችን ይሄው ነው!! #ሼር ይደረግ

@ke_postu_commentu_begna
@ke_postu_commentu_begna