Get Mystery Box with random crypto!

* አፍቅሪኝ እባክሽ ምንም ነገር የለኝ ላንች የምሰጥሽ ህይወት ከ | Kali pictures 🐾

* አፍቅሪኝ እባክሽ


ምንም ነገር የለኝ ላንች የምሰጥሽ
ህይወት ከኔ ጋር ምንም ባይመችሽ
ኑሮዬ ቢያሽጠላም ባያምር ውሎዬ
ፀሎቴን ባረዝም ወደ ፈጣሪዬ

እባክህ ጌታዬ ግራ ጎኔን ስጠኝ
እኔም የምወዳት እሱዋም የምትወደኝ

ከእነ ድህነቴ ከእኔ ጋር የምትኖር
የምታስተምረኝ እውነተኛ ፍቅር
ምሶሶ የሆነች ለምትወደው ቤቷ
እኔን የምትወደኝ ከውስጥ ካንጀቷ

የማትጨቃጨቅ በቀንም በማታ
ሰነፍም ያሎነች በውጪም በቤቷ

ለእኔ ለውዷ ብቻ የምታስብ
የማትጠይቀኝ መኪና እና ገንዘብ

እንደዚህ አይነት ሴት በምድር ላይ ካለሽ
ብዙ ሳታደክሚኝ አፍቅሪኝ እባክሽ



🅚🅐🅛🅘
🅟🅘🅒🅣🅤🅡🅢
@kali_1221