Get Mystery Box with random crypto!

የማያልቀውን ታሪክ እንጀምር ዛሬ ደሞ ከወትሮው ተለየብኝ!! ለምን? ጊዜው ብርዳማ መሆ | Kali pictures 🐾

የማያልቀውን ታሪክ እንጀምር

ዛሬ ደሞ ከወትሮው ተለየብኝ!! ለምን?

ጊዜው ብርዳማ መሆኑ አይዘነጋም ሙሉ ቀኔን ተኝቼ ውዬ አመሻሹን ከቤቴ ትሸርት ላይ ሸሚዝ ሸሚዜ ላይም ጠቆር ያለውን ጃኬቴን ደርቤ ጥቁር ሱሪ ጥቁር ጫማዬን ተጫምቼ ግቢያችን ያቆረውን የዝናብ ውሃ ዘለል ዘለል...አያልኩ ከጅ ደረስኩ። ሁሌ አዲስ ነገር የማይጠፋበትን ጎዳና ልንሸራሸርበት። ትንሽ ራመድ እንዳልኩ ከሰፈር ማጠፋዋን ሙዚቃ ወዳድ ጓደኛየን እንደተለመደው ነጭ ማዳመጫ ጆሮ ዋ ላይ ሰክታ አገኘዋት። እሱዋም በመገረም አይታኝ "ከመሸ ወደት ነው ዘንጠክ ቃል" ስትል ጠየቀችኝ እኔም "ኧረ እዚው ነው ውድ" ብላት "ኧረ አይመስልም ከመሸማ የሆነች ችክ(ሴት) ቀጥረክ ነው እዲህ አምሮብክ ላጥላጥ ምትለው" አለችኝ እኔም "ኧረአደለም ብዬ" ያን ውብ ፈገግታዬን ለግሻት ።"በቃስመለስ አገኝሻለው" ብዬ ተሰናብቻት መንገዴን ቀጠልኩ...።ከሰፈር ወጣ እንዳልኩ ፎቶግራፈር መሆኔን ማይዘነጋውን ጓደኛዬን ወደ ሰፈር እየተመለሰ አገኘውት። አሱም "እንዴ ቃሊ ፏ ብለሽ ወዴት ነው ከመሸ" አለኝ እኔም "እዚው ነው " አልኩት እሱም ከአፌ አውርቼ ሳልጨርስ "ስራ ነው እእ የ ሰርግ መልስ ልትቀርፅ ነው" አለኝ አኔም "ኧረ አደለም" ከማለቴ "አሰክሺኛ(አትዋሸኝ) ቃል ከሆነ ልከተልክ እራቴን ዘግቼ(በልቼ) ልመለስ እንጂ"አለ እኔም "ስራ አደለም ዝምብዬ ወጥቼ ነው" አልኩት እሱም አዬ(እሺ) በቃ ደርሰሽ ተመለሺ" አለኝ እሺ ብዬው መንገዴን ቀጠልኩ ጎዳናው ደስ ይላል መንፈስንም ያድሳል። ለብርድ መቆቆሚያ ይሆን ዘንድ በመን ገዱ ዳር የሚጠበሰው በቆሎ እና ድንች(ችብስ) ሽታው ያውዳል። ወዲወድያ የሚሉት ሰዋች ተረጋግቶ ለሚያያቸው ረብሽ ያለ ነው ሚመስለው! ጥድፌያቸው...እኔም በተመስጦ እየተጉዋዝኩ ድንገት ተደናቀፍኩ ገድገድ ስል "አይዞህ አይዞህ ልጄ" ተባልኩ ድምፃቸው ትልቅ እናት መሆናቸውን ያስታውቃል ዞር ስልም ማቃቸው ጎረበታችን ናቸው እኔም " ተርፍያለው እማማ" አልኩዋቸው እሳቸውም "ተረፍክ ተርፈካል ልጄ " አሉኝ "አዋ አዋ አማማ" አልኩኝ እሳቸውም ትንሽ በግርምት አይተውኝ "ኬት ነው ልጄ እንዲ ጥቁር በጥቁር ለብሰክ ሰላም አደለም እዴ" ሲሉኝ እኔም ተደና ገጥኩ የቅድሞቹ ጓደኞቼ እየፎገሩኝ መሰለኝ ከዛም በተወዛገበ ስሜት ሆኜ " ኧረ አው እማማ ሰላም ነው እንዲው ለብሼ ነው"ብያቸው መንገዴን ቀጠልኩ ትንሽ ተራምጄም ወደቤቴ ተመለስኩ....

እናም ከወትሮው ለየት ያለብኝ የሰው ልጅ በራሱ ሚዛን እን ደሚመዝን ተረድቼ መግባቴ ነው።

ቤተሰብ የሰው ልጅ እንደራሱ እና በራሱ መንገድ ነው ሚረዳን ።ስለዚ ሰው ለሚልክ ነገር አትጨነቅ ዝም ብለክ መንገድክን ቀጥል።

በሌላ ታሪክ ይቀጥላል
@Mski2
@kali_1221 comment