Get Mystery Box with random crypto!

​​Satellite Dish Information by Kal ዛሬ ይዘንላቹው የቀረብነው ስለ RS-2 | ሳትላይት ዲሽ መረጃ

​​Satellite Dish Information by Kal

ዛሬ ይዘንላቹው የቀረብነው ስለ RS-232 Cable እና ስለ Loader ምንነት እና አንድ አንድ ጠቃሚ መረጃ ይዤ ቀርቤያለው!

ረሲቨር HEVC 265 ሆነ 4K,HD,SD በSoftware ምክንያት ቀይ አብርቶ ወይም BOOT,LOAD,ON ብሎ ሊቀሩ ይችላሉ አልያም የተለያዩ ችግሮች ሊያመጣ ይችላል ይህንን ለማስተካከል ደግሞ ስለ RS cable እና ስለ Loader በደንም ማወቅ ይኖርብናል!

የዛሬ Topic ስለ RS-232 Cable እና ስለ Loader ይሆናል እኔም በበኩሌ የማውቃትን ያህል ሹክ ልበላችሁ!

RS-232 ማለት በአብዛኛዎቹ የHEVC 265 እና የ4K የHD,SD ሪሲቨሮች ጀርባ ላይ የምናገኘው DB9(ባለ 8 ቀዳዳ) Cable ነው! የዚህም Cable port ጥቅሙ በተለያዩ አጋጣሚዎች የምንጠቀምበት ሪሲቨር በ"Software" ምክንያት Fail ካደረገ(አልበራም ካለ፣BOOT | LOAD | ON ወይም READY ብሎ ከቀረ ረሲቨሩ ሳይፈታ! በCOMPUTER/PC/LAPTOP አማካኝነት ድጋሚ እንዲሰራ ለማድረግ የሚጠቅመን DEVICE/CABLE ነው!

Loader ማለት ደግሞ Computer ላይ የሚጫን Software ማለት ነው!
እንደ እየ ረሲቨሮቹ የChip፣የIC እና የMemmory size አይነት የተለያዩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው Loaderኦች አሉ!


Receiver Damage እንዲሆን ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል!

ረሲቨሩ ላይ ትክክለኛ ያልሆነ Software መጫን/Upgrading the STB with a wrong software!

ሶፍትዌር እየጫንን እያለ የምበራት ወይም የ Storage device(USB) መቋረጥ! /Power cut and USB DEVICE removal during the Upgrading Process!
ዋነኞቹ ናቸው!

እኔም እንደ ባለሙያነቴ ለተጠቃሚዎችም ሆነ ለዲሽ ገጣሚዎች ከላይ ያሉት ሁለት(2) ጉዳዮች  ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ታረጉ ዘንድ አሳስባለው!

አንድን ረሲቨር Loader Upgrade ለማድረግ የሚያስፈልጉ ነገሮች!

የረሲቨሩ Loader!
በእኛ ሀገር ከሚገኙት ሪሲቨሮች መካከል እኔ ጋር Loader ያለቸው ሪሲቨሮች ዝርዝር!


ሁሉም #Lifestar★ HEVC 265 እና 4K,HD,SD ረሲቨሮች!
ሁሉም #Tiger★ HEVC 265 እና 4K,HD,SD ረሲቨሮች!
ሁሉም #LEG★ HEVC 265 እና 4K,HD,SD ረሲቨሮች!
ሁሉም #Starsat★ HEVC 265 እና 4K,HD,SD ረሲቨሮች!
ሁሉም #KINGSTAR★4K እና HD,SD ረሲቨሮች!
ሁሉም #Goldstar★ HEVC 265 እና 4K,HD,SD ረሲቨሮች!
ሁሉም #GSKY HD ረሲቨሮች!
ሁሉም #FREESAT HD ረሲቨሮች!
ሁሉም #CORONET_MEWE_CLLASICSTAR_EXTREAM ረሲቨሮች!
አብዛኛዎቹ #Supermax ረሲቨሮች!
አብዛኛዎቹ #Eurostar እና #IBOX #Eurobox ረሲቨሮች!

② COMPUTER
ለስራ ቅለት Window 7 Ultimate ቢሆን ይመረጣል እና Window 10,10pro System Run የሚያረጉ! Dekstop ወይም Laptop!

③ RS-232 Cable!
ለDesktop ከሆነ FEMALE to FEMALE DB9 RS-232 Cable!

Laptop ከሆነ ግን ከ"FEMALE to FEMALE DB9 RS-232 Cable" በተጨማሪ USB to DB9 MALE Cable ያስፈልገናል!

ይህም የሚሆነው ሁሉም ላፕቶፖች ማለት ይቻላል የRS-232 Cable መቀበያ Port ስለሌላቸው የግድ ይህ "USB to DB9 MALE" Convertor ያስፈልገናል!

ልብ ይበሉ የዚህ Cable Originalነት በጣም ወሳኝ ነው! በአብዛኛው በየሱቁ የምናገኘው ባለ ሰማያዊ Colour USB to DB9 Rs232 Cable ሪሲቨር ስለሚመርጥ እኔ በበኩሌ ይህንን Cable እንድትገዙ አልመክርም!

እንዚህን ካሟላን በሁዋላ Loaderu ላይ የሪሲቨሩን File በመምረጥ Loaderu እንደሚያዘን (እንደ ባህሪው) Upgrade ማድረግ ነው!


Like እና Share ስላደረጉ ነገም ሌላ ቀን ነው አዳዲስ መረጃዎችን ማግኝት ይችላሉ!

In Box @kal_admin

የቴሌግራም ቻነላችን ሊንክ @kaldishinfo1 ሼር በማድረግ ሌሎችም እንዲዳረስ ያድርጉ!