Get Mystery Box with random crypto!

#ቦረና በ #ቦረና በታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው ድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት የም | ሳትላይት ዲሽ መረጃ

#ቦረና

በ #ቦረና በታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው ድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት የምትፈልጉ በ " #ALCHIISOO_PASTORALIST_UP " በኩል መርዳት ትችላላሁ።

የዚህ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) የባንክ አካውንቶች ፦

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000522499823 (Swift Code: CBETETAA)

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ -  1011800084313 (Swift code: CBO RETAA)

አዋሽ ባንክ - 013081084782900
(Swift code:  AWINETAA)

ኦሮሚያ ባንክ - 1548414100001
(Swift code: ORIRETAA)

ቁጥሮች ስለ ቦረና ምን ይናግሩናል ?

- በቦረና ዞን 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ከነዚህ ውስጥ 167 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች አስቸኳይና ተከታታይ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው።

- በዞኑ ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል።

- በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85 % የቀንድ ከብቶች ናቸው።

- በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው።

- የተከሰተው ድርቅ በዞኑ 13 ወረዳዎች አጥቅቷል ፤ በዞኑ ከሚገኘው 60 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ ድጋፍ ይፈልጋል።