Get Mystery Box with random crypto!

JUSTIN APOLOGETICS]

የቴሌግራም ቻናል አርማ justin_apologetics — JUSTIN APOLOGETICS] J
የቴሌግራም ቻናል አርማ justin_apologetics — JUSTIN APOLOGETICS]
የሰርጥ አድራሻ: @justin_apologetics
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 659
የሰርጥ መግለጫ

ከእስልምናና ከሌሎች ቤተ እምነቶች ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ መስጫ
“ #አንድ ጌታ #አንድ ሃይማኖት #አንዲት ጥምቀት፤”
— ኤፌሶን 4፥5
አስተያየት ካሎት @Againest_hereticss_bot ላይ ያድርሱን

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-04 21:04:41
"የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ



የሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ እንዲሁም የምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ምሽት የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሻሸመኔ አብያተክርስቲያናትን በመሥበር ምእመናንን በግፍ በማሠርና በመደብደብ ከየአካባቢው ባመጧቸው ቡድኖች አብያተክርስቲያናት ተቆጣጥረዋል ሲሉ ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በስልክ ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ "የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?" ያሉ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሰጡትን መግለጫ ምእመናን እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
በ13 ወረዳዎች ሊቃነ ካህናት በግፍ መታሠራቸውን ገልጸዋል።
የብፁዕነታቸውን መልእክት በዩቲዩብ ገጻችን ይከታተሉ።

ምንጭ: EOTC TV
91 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 21:04:41
ዜና ሻሸመኔ
‘’ዛፍ ላይ ወጥቼ ነው ምደውልላችሁ’’ - የሻሸመኔ ምእመን
ሕገ ወጥ ቡድኑ የሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ታግዞ ከሰበረ በኋላ በርካታ ምእመናን ወደ አልታወቀ ቦታ እየታፈሱ እየተወሰዱ መሆኑን የከተማው ዓይን እማኞች ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አድርሰውናል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን አሳልፈን አንሰጥም ባለው ምእመን ላይ የከተማው ሚሊሻ፣ፖሊስና ልዩ ኃይል በቅንጅት ተኩስ በመክፈትም በርካታ ምእመናን እንዳቆሰሉና የቆሰሉትን ሳይቀር ወደ ፖሊስ ጣቢያ እያስገቡም ይገኛሉ።

እንደመረጃ ሰጭዎቻችን ከሆነ በአይሱዙ መኪና ካህናትና ምእመናንን ከየቤቱ እያሰሱ በማፈስ ወደ አልታወቀ ቦታ እየወሰዷቸው ነው ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ምእመናን በኃይል ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ በመደረጉ ተበታትነው እየተሳደዱ ይገኛሉ ያሉት መረጃ ሰጫችን ይህንንም መረጃ "ዛፍ ላይ ወጥቼ ነው ምደውልላችሁ" በማለት ያለውን የደኅንነት ስጋት ገልጸውልናል።

የከተማው ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያናቸውን አሳልፈው እንደማይሰጡ ሲታወቅ ሕገ ወጥ ቡድኑ ደጋፊዎች የሌላ ቤተ እምነት ተከታዮችን በማስተባበር መስቀል ሲያስሩና ነጠላ ሲያለብሱ እንደነበር የዓይን እማኛችን ተናግረዋል።
84 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 11:55:51 --
መንበር (Apostolic See. Or Holy See)
--
ብርሃኑ አድማስ የመንበር ጉዳይ ገነን ብሎ የወጣው ከጉባኤ ኒቅያ ወዲህ ነው፤ ከዚያ በፊት ሐዋርያትም ሆነ ተከታዮቻቸው በመካከላቸው የሀገረ ስብከት ወሰን /jurisdiction/ አልነበራቸውም ነበረ ይላል፡፡ የመንበሮች ስያሜ ክርስትናው ወደ ሀገር ከገባበት ወይም በሀገሪቱ ላይ ካለው ገናና ቅዱስ ጋራ ይያያዛል፡፡ ሮማውያንና አንጾኪያዎች መንበራቸውን ‹‹መንበረ ጴጥሮስ›› ይሉታል፣ ሕንዳውያን ‹‹መንበረ ቶማስ››፣ ግብጻውያን ‹‹ምነበረ ማርቆስ››፣ አርመናውያን ‹‹መንበረ በርተሎሜዎስ››፣ በኢየሩሳሌም ያሉ ክርስቲያኖች ‹‹መንበረ ያዕቆብ፣ ብዙኃን የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያን ‹‹መንበረ እንድርያስ››፣ … ሁሉም የራሱን ከታሪኩና ከመንፈሳዊ ሕይወቱ የተገናኘ ስያሜ ይሰጣል፡፡ የኢኦተቤክ ቀደም ሲል ‹‹ማርቆስ አባታችን፣ እስክንድርያ እናታችን›› ማለቷ ለብዙ ጊዜ በእልህና በስሜት እንደምናስተሐቅረው ሳይሆን የአባቶቻችንን የሐዋርያዊ ክትትልንና የመንበር አንድነትን ትርጕም ማወቅ ያሳያል፡፡ በጊዜው ጊዜ ራሳቸውን ሲችሉ መንበሩ ‹‹መንበረ ተክለ ሃይማኖት›› እንዲባል ከግብጻውያን አበው ጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ የመንበር ስያሜን ከሐዋርያዊ ክትትል አለመማምታታት ይገባል፤ ቢዛመዱም ልዩነት አላቸው፡፡ የአቡነ ባስልዮስ የፕትርክና ሹመት ከግብጻዊው ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ 6ኛ የተገኘ ነው፡፡ አቡነ ቄርሎስ 6ኛ ደግሞ ከጌታ በንፍሐት ያገኘውን በአንብሮተ ዕድ ቅዱስ ጰየጥሮስ ካስተላለፈለት ወንጌላዊው የጌታ ረድዕ ቅዱስ ማርቆስ ጀምሮ ሲቈጠር 116ኛው በአንብሮተ ዕድ የተሾሙ አባት ናቸው፡፡ ስለዚህ የአቡነ ባስልዮስ ሥልጣን ወደኋላ ሲቈጠር የአንብሮተ ዕድ ንብርብሩ ጌታ ዘንድ ያደርስናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሐዋርያዊት›› መባሏ ለዚህ ነው፡፡ ያለዚህ ክትትል ሐዋርያዊት መሰኘት እንደማይገባ በክብረ ክህነትና በምሥጢራት የሚያምኑ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ይስማሙበታል፡፡ ወደ ነገረ መንበር ስንመለስ፡- ክርስቲያኖች በቁጥር አናሳና የተጨቆኑ ካልሆኑ በቀር መንበር ብዙ ጊዜ ማዕከሉ በዋና ከተማ በሀገሪቱ መናገሻ ነው የሚሆን፡፡ መንበረ ፕትርክና/ ሊቀ ጵጵስና ይባላል፡፡ የግብፅ በታሪክ በእስክንድርያ (በእርግጥ እስክንድርያም ታላቅና ታሪካዊት ከተማ) ናት ቢባልም ፓትርያርኩ የሚቀመጡ በዋና ከተማዋ በካይሮ ነው፣ የምሥራቃውያኑ ታሪክ በዋና ከተማነት ባገነናት በቁስጥንጥንያ ናቸው፣ የካቶሊካውያን በሮም ነው፣ የእስራኤል በኢየሩሳሌም ነው፣ የራሽያ ኦርቶዶክሱ በሞስኮ ነው፣ … መንበሩ ከሚያገለግለው ሕዝብ መካከል ይሰየማል፡፡ ዐላማው ከተሜነትን ፍለጋ ሳይሆን በድካም ያሉትን ሰብአ ዓለምን መፈለግን ታሳቢ ያደርጋል፤ የአገልግሎት ተደራሽነትንና የተልእኮ መፋጠንንም ከግምት ያስገባል፡፡ በታሪክ የምናውቃቸው ታላላቅ አበው፡- ቀሌምንጦስ ዘሮም፣ አትናቴዎስ አዘስክንድርያ፣ ዮሐንስ ዘአንጾኪያ፣ ቅዱስ ዮሐንስ (አፈወርቅ) ዘቁስጥንጥንያ፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ፣ … ከስማቸው ቀጥሎ የሚቀጸሉላቸው የቦታ ስሞች ሁሉ ታላላቅ ከተሞችና መናገሻዎች መሆናቸው ነገራችንን ያፀናልናል፡፡ ወደ ጵጵስና ከመጡ በኋላ ባለቅኔው እንዳለው ‹‹መንኖ ዓለም ዘምስለ ዓለም - በዓለም እየኖሩ ዓለምን መናቅ›› እንጂ የአገልግሎት ቆብ ከደፉ በኋላ በጸሎቴ ብቻ ነው የማገለግላችሁ ብሎ ከዋሻ መግባት አንድም ራስ ወዳድነት፤ አንድም መመጻደቅ ነው፡፡ የጴጥሮስ ሥልጣንን ከያዙ በኋላ በአደባባይ መስክሮ ማለፍ እንጂ መሹለክለክማ በሥልጣን ከቅዱስ ጴጥሮስ ያልተወለደ መጻተኛ መገለጫ ነው፡፡
--

የተፋልሶው አደጋ
--
የሐዋርያዊ ክትትል ዐላማ የሃይማኖት፣ የቀኖና፣ የሥርዓተ አምልኮና ሱታፌ ምሥጢር እንዲሁም መዋቅራዊ አንድነትን ማጽናት ነው፡፡ ይህ ዐላማ ሲፋለስ ዝርውነት ይከተላል፡፡ ምሥጢረ ክሀነትና በክህነቱ የሚከናወኑ ምሠጢራት ክብርና ተቀባይነት ያጣሉ፡፡ በክብረ ክህነት ከማያምኑ ተደምሮ መቈጠርን ያስከትላል፡፡ በራስ ጊዜ ተወግዞ መለየትን ይጋብዛል፡፡ ‹‹ዘወሐቦሙ ሥልጣነ ለሐዋርያት …›› እያሉ መናዘዝን፣ ‹‹በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ …›› እያሉ የማሰርና መፍታት ሥልጣንን ያሳጣል፡፡ ሥልጣናቸውን ከቀዳሚዎቻቸው መስመር ጠብቀው የተቀበሉ እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ቴዎፍሎስ፣ ቄርሎስ፣ ዲዮስቆሮስ፣ … ያሉ አበውን ‹‹አባት›› ብሎ በሥልጣን የመጥራት መብትን ሐሳዊ ያደርጋል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዳለው የሐሳዊ መሲህን መምጣት መጠቆም ይሆናል፡፡ በጥቅሉ ኢሥርዓታዊነትን ያነግሣል፤ ምሥጢራትን ያራክሳል፤ ሕገ መጽሐፍን (መጽሐፍ ቅዱስን) ይጻረራል፡፡ አንድ አባት እንዳሉት ‹ይህን ሐዋርያዊ ክትትል ሰበሮ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ማለት የጌታን እስትንፋስ እንደ ማቋረጥ፣ ለአንብሮተ ዕድ የተዘረጋ እጁን እንደ መቁረጥ ይቆጠራል፡፡› እንዲህ እናምናለን!
--
ወነአምን በ #አሐቲ #ቅድስት ቤተ ክርስቲን #እንተ_ላዕለ_ኵሉ ጉባኤ #ዘሐዋርያት፡፡
ደብተራ በአማን ነጸረ
175 viewsedited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 11:55:51 - የእግዚአብሔር ስጦታ ከጳውሎስ ወደ ደቀመዝሙሩ ጢሞቴዎስ መተላለፉ በግልጥ የሚታይ ነው፡፡ ጢሞቴዎስም ይኸንን ስጦታ በአንብሮተ ዕድ አስተላልፏል›› (H.H.Pope Shenouda III, On Priesthood, 1997, p.48)
#ተሞክሮው፡- በአርመንና በሕንድ የማላንካራ አብያተ ክርስቲያናትም ተመሳሳይ ቀኖና አለ፡፡ ሐዋርያዊ ክትትል አጥብቀው ይሰብካሉ፡፡ ከሕን ተገንጥለው በተሐድሶነት ከወጡት ፕሮቴስታንታውያን በቀር ወደ ካቶሊክ የሄዱትና ራሳቸውን ‹‹ጃኮባይት›› የሚሉትም ሐዋርያዊ ክትትልን አያስተሐቅሩም፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጥል አካሄዱ ላይ የኢኦተቤክ ቅሬታ ቢኖራትም ሐዋርያዊ ክትትልን በመጠበቅ ረገድ ግን የኤርትራ አበው ንቁዎች ነበሩ፤ ሐዋርያዊ ክትትል ካላት የኮፕቲክ (የገብፅ) ቤተ ክርስቲያን ሂደው ተሹመዋል፡፡
#ያረጋልና ብርሃኑ፡- ያረጋል አበጋዝ በመድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2፣ ብርሃኑ አድማስ በብላታ መርስዔ ኀዘን ለተዘጋጀውና በልጃቸው በተሰናኘው ‹‹የመጀመሪያው /ኢትዮጵያዊ/ ፓትርያርክ›› በጻፈው ቀዳሚ ቃል የሐዋርያዊ ክትትል ጽንሰ ሐሳብ ተዳስሷል፡፡ በቃል አጠቃቀም ረገድ ያረጋል ‹‹ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ›› ሲል ብርሃኑ በበኩሉ ‹‹ሐዋርያዊ ክትትል›› ይላል፡፡ ይዘቱ አንድ ነው፡፡ የያረጋል ቅጽ 2 መድሎተ ጽድቅ ‹‹ክርስቶስ ብቻ›› የሚለው ርእስ በጥሞና ሊነበብ የሚገባው ውብ የነገረ ክህነት ምንባብ አለበት፡፡
ፕሮፌሰር #ጌታቸው፡- ኦርቶዶክሳዊነትን ከሐዋርያዊ ክትትል ጋራ በጥብቅ አቈራኝተው ያዩታል፡፡ በዚህ ሐዋርያዊ ክትትል ያልተጓዘ ሁሉ ኢኦርቶዶክሳዊ ነው ይላሉ (አዲሱ የደቂቀ እስጢፋኖስ መግቢያ፣ በአንዳፍታ ላውጋችሁ 2ኛ ዕትም ተካትቶ የሚቀርብ)፡፡
--
ሲመተ ፕትርክና ወጵጵስና በጨረፍታ
--
(1) #ቅድመ_ሲመት፡- ይኸኛው ደረጃ የመምረጥና የመለየት/የመቀደስ/ ነው፡፡ ከምሰክሮችም መካከል በየሐዋ.ሥራ 13፡2-3 ‹‹የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙም መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን እኔ ለፈለግኋቸው ሥራ ለዩልኝ አላቸው›› የሚለው ቃልና በሐዋ.6፡6 ‹‹… ከእናንተ ወገን በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ምረጡ፤ ለዚህም ሥራ እንሾማቸዋለን፡፡›› በሚል የሰፈሩት ምንባባት ይጠቀሳሉ፡፡ አካላዊና አእምሮአዊ ጤንነት በተለይም ከሚጥል ሕመምና ከተላላፊ በሽታ የፀዳ መሆን፣ ቀድሶ ለማቁረብ የሚያስል አካላዊ ደኅንነት፣ የሃይማኖት ርትዐት፣ የአስተዳደር ችሎታ፣ ቤተ ክርስቲያንን ከመናፍቃን መጠበቅ የሚያስችል የትምህርት ዝግጅትና ምስጉን ጠባይን ከጥበብ አቀናጅቶ መገኘት በአጠቃላይ 8 የሚደርሱ መመዘኛዎችን ማሟላት ይጠይቃል፡፡ የግእዙና ከዐረብኛው ቅጅ በእንግሊዝኛ የደረሰን ፍትሐ ነገሥት እነዚህንና የመሳሰሉትን ቅድመ ሲመት መማሏት አላቸው የሚላቸውን፣ ከጵጵስና የሚያስቀሩና የማያስቀሩ መመዘኛዎች በአንቀጽ 4 እና 5 በዝርዝር ያኖራል፡፡ ምርጫው ከምዕመን እስከ ሊቀ ጳጳስ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን አካላት ድምፅ ያካትታል፡፡ በምርጫው ተቀራራቢነት ያላቸው ተወዳዳሪዎች የቀረቡ እንደሆነ እንደ ዘመኑ ይወሰናል፡፡ ውሳኔው በድምፅ ብልጫም ሊወሰን እንደሚችል ፍትሐ ነገሥቱ ደንግጓል (አንቀጽ 4፡57)፡፡ ድምፁ እኩል ከሆነ በታቦት ላይ ዕጣ መጣልም ሌላኛው አማራጭ ነው (አንቀጽ 4፡69)፡፡ በመመዘኛ ረገድ ግን ዘመኑ መናፍቃን የበዙበት ከሆነ በስብከቱ የተሻለውን፣ አስተዳደሩ የተጓደለ እንደሆነ በአስተዳደር የተመሰገነውን ማድረግ ይገባል፡፡ “ ይረስይዎ ኖላዌ ለዘይፈቅዶ ፍትሐ ዝኩ ዘመን …ጊዜ የሚፈቅደውን ይሹሙት … the needs of the time should be considered.” ዘመንን የዋጀ ምርጫን ሁሉም ቋንቋዎች ይተባበሩበታል፡፡ ለጵጵስና የሆነ እንደሆነ የሊቀ ጳጳሱንና የሕዝቡን ይሁንታ እንዲሁም ፈቃደ መንፈስ ቅዱስን ማግኘት ግድ ነው (ፍት.ነ.አንቀጽ 5፡90)፡፡ ይኸንን ድንጋጌ መተላለፍ ውጤቴ ግዝት መሆኑን የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 91 ድንጋጌ ይናገራል፡፡
(2) #ጊዜ_ሲመት፡- በሲመቱ ጊዜ የሚኖርን ሥርዓት የሚመሩት ጳጳሳት ናቸው፡፡ ቢያንስ 2 ወይም 3 ጳጳሳት መገኘት አለባቸው “ … his becoming a bishop is in the presence of two or three bishops.” ቀኖና ሐዋርያት /Apostolic Constitution/ ነው ፡፡ ሕዝቡም ተገኝቶ ሥርዓቱን በይፋ በገሐድ ይከታተላል፡፡ ጳጳሳቱ እጃቸውን ታጥበው ‹‹እኛ በዚህ በተመረጠ የእግዚአብሔር ባሪያ ላይ እጃችንን እንጭናለን - We lay our hands on this servant selected for God›› ብለው በአንብሮተ ዕድ እየባረኩት የሲመት ቅድምና ያለው እጁን በተለጫው እጩ ጳጳስ ላይ ጭኖ ለሲመቱ የተገባውን ጸሎት ሲያደርስ ሕዝቡ በልዑል ዜማና በንባብ ‹‹ይገባዋል-ይደልዎ/አኪዎስ/›› ይላሉ (ፍት፣ነ.አንቀጽ 5፡101)፡፡ አብነቱ ከቅዱስ መጽሐፍም በ2ኛ ጢሞ.1፡6፡- ‹‹… #እጄን_በአንተ_ላይ_በመጫኔ ያገኘኸው የእግዚአብሔር ጸጋ›› በሚል እንዲሁም በ1ኛ ጢሞ.4፡14 ‹‹… #በጳጳሳት_እጅ_መጫን_የተሰጠህን በአንተ ላይ ያለውን ጸጋ አታቃልል›› የሚል ምስክር አለው፡፡ ሐዋርያት የተመረጡትን በአንብሮተ ዕድ መሾማቸው ‹‹በሐዋርያትም ፊት አቆሟቸው ጸልየውም እጃቸውን በራሳቸው ላይ ጫኑ›› ከሚለው የሐዋ.ሥራ.6፡6 በግልጥ የሚነበብ ነው፡፡ አንብሮተ ዕድ ግድ ነው! ቅዱስ ጳውሎስ እንኳ በጌታ ቢጠራም ክህነቱ ግን ከሐዋርት በአንብሮተ ዕድ ነበረ የተገኘ (የሐዋ.ሥራ 13፡2)! ወደ ንዑስ ርእሳችን ስንመለስ፡- ጸሎቱ ሲጠናቀቅ ተሰያሚውን ጳጳስ እጅ ይነሡታል፡፡ ልብሰ ተክህኖና መስቀል ይሰጠዋል፡፡ ቀድሶ ቆርቦ ያቆርባል፡፡
(3) #ድኅረ ሲመት፡- ጳጳስ አምስት ተልእኮዎች እንዳሉት ፍትሐ ነገሥታችን ይጠቅሳል፡፡ ከዐረብኛው ቅጂ ወደ እንግሊዝኛ ከተተረጐመው ባጭሩ ብንወስድ፡- ሃይማኖተ አበውን ባገናዘበ መልኩ መንጋውን ከመናፍቃን በትምህርት በምዕዳን መጠበቅና ማጽናት /duty to protect or sustain/፣ በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ በሚነሣ ክርክር በሥልጣኑ ልክ ፍርድ መስጠት /judgment/፣ ነዳያንን መፍቀድ /determine the needs of the needy/፣ ለሚገባቸው ሥልጣንን መስጠት/ to give positions of leadership/፣ ለሁሉም ጊዜ አለውና ከጸሎትና አስተዳደር ባሻገር ምዕመናን በግልም በማኅበርም ማነጋገርና ማጽናናት እንዲሁም ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት /Mnage public affairs/ ይጠቀሳሉ (Magmou al-Safawy Ibn al- Assal, p.8 ). የተልእኮው መዝጊያ ቃል፡- ‹‹አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› የሚለው የሐዋ.ሥራ 20፡28 መሆን ይችላል፡፡ ከሲመት በኋላ ከመንጋው ርቆ ‹‹ጸሎት ላይ ነኝ›› እያሉ መንጋው እንዲናውዝ መተው የሚገባ አይደለም! ሲመቱ፡- ቅድመ ሲመትም፣ ጊዜ ሲመትም፣ ድኅረ ሲመትም የሚገባውን መስመር ሊጠበቅ ግድ ይሆናል፡፡
119 views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 11:55:51 ከእልህና ስሜት ባሻገር፡ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ /ክትትል/ (Apostolic Succession)
--
ክህነት ምሥጢራት ሁሉ የሚፈጸሙበት የማይደገም የማይከለስ የማይታደስ ምሥጢር ነው፡፡ ከነገረ ድኅነት ጋራ ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተራ ዲያቆናት እስከ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያሉ ውሉደ ክህነትን፣ በተለይም መነኮሳትን መንቀፍን እንደ ልማድ ስለወሰድነው ኀዳሪው በማኅደሩ እየተፈተነ ይመስላል፡፡ ከልጅነት ሥርዓት መውጣትና ተቈርቋሪነትም ሳይምታቱ አልቀረም፡፡ ካህኑ ለካህናት የተጻፈውን ግብር አጉድሎ ቢገኝ እርሱ ይወቀስበታል እንጂ ክህነቱ ሊራከስ አይችልም፤ አይገባምም፤ በአገልጋዩ ድክመት አገልግሎቱ አይነቀፍም፡፡ ምሥጢረ ክህነት በካቶሊካውያንም፣ በምሥራቃውያንም፣ በአሲርያ ንስጥሮሳውያንም፣ በኦሪየንታልና በተወሰነ ደረጃ በአንግሊካኖችም ዘንድ አለ፡፡ እነዚህ ሁሉ ቅዳሴ፣ ሜሮን፣ ቁርባን፣ ንስሐ … የመሳሰሉ ምሥጢራትን ለመፈጸም ካህን ይጠቀማሉ፡፡ የካህኑ ክህነት ሐዋርያዊ ክትትልን ከጠበቀ አባት እንዲሆንም ግድ ነው ይላሉ፡፡ የገዳማውያንና የመናንያን መናኽሪያ በሆነችው በቤተ ክርስቲያናችንም ይህ ቤተ ክርስቲያንን ‹‹ሐዋርያዊት›› የሚያሰኝ ምሥጢር እንዳይፋለስ ሲባል አንድ ሚሊኒየም ተኩል የወሰደ የትዕግሥት ጊዜ ተከፍሏል፡፡ ስለዚህ፡- የሐዋርያዊ ቅብብሎሽን መጽሐፋዊ መነሻ፣ ቀኖናዊ መሠረት፣ የሲመተ ጵጵስናውን አፈጻጸምና የጳጳሱን ግብር፣ የመንበሩን ነገር፣ ምሥጢረ ክህነትን ማስተሐቀር የሚያመጣውን ፈተና ከመጽሐፍም፣ ከአዋልድም፣ ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተሞክሮም እያዛመድን በሚጢጢ ንባብ ብናይ ጊዜው ይፈቅድልናል፡፡ ወሩ ወርሐ ሰኔ ነው፡፡ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ የተሾሙልን በዚህ ወር ነው - ሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም.፡፡
--
ትርጓሜው
--
ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታ ተቀብለውት ያለማቋረጥ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የክህነት ሲመታዊ ክትትልን ያሳያል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተፈጥሮ ነፍስን ከሐዋርያዊ ክትትል ያመሳስላል፡፡ በመጽሐፈ ምሥጢርና በመዝገበ ሃይማኖት እንደተመለከተው ከአባት ዘር፣ ከእናት ደም ተከፍሎ ሲዋሐድ ነፍስ ከወላጅ ወደ ልጅ ታልፋለች፡፡ በፀናው ሲነገር (እንበለ ዘርዐ ብእሲ /ያለወንድ ዘር/ ከተፀሰነው ጌታ በቀር) የአዳም ዘር ሁሉ በዚህ ያለፈ ነው፡፡ የነፍሳችንን ጥንተ ፍጥረት ወደኋላ ብንቆጥር የመጨረሻው መገናኛችን አዳም ይሆናል፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ክህነትም እንዲሁ ነው፡፡ የእያንዳንዳችን ውሉደ ክህነት የሥልጣን ምንጭ ወደኋላ ቢቈጠር የመጨረሻ መገናኛችን የጌታ እስትንፋስ /ንፍሐት/ና ቡራኬ ነው፡፡ የክህነት ክትትሉ ሲቈጠር በዚህ ሐዋርያዊ ሰንሰለት ያልተገኘ ሥልጣን ‹‹ውጹእ/ውዱቅ›› /invalid/ ነው፡፡ በትክክለኛው መስመር አልመጣምና የሥልጣን ውርሱ አይጸድቅም፤ አያጸድቅም!
--
መነሻው፡ በቃለ መጽሐፍና በቀኖና አበው
--
በብሉይ ኪዳን በሌዊ ቤት ሐረገ ትውልድን ጠብቆ በዘር ይተላለፍ እንደነበረ ነጋሪ አያሻም፡፡ በሐዲስ ኪዳን በዘር መሆኑ ቀረና ከ12ቱ ነገድ የተውጣጡ ቅዱሳን ሐዋርያትን መረጠ፤ ጠራ፡፡ ‹‹በዚያም ወራት ጌታችን ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር #ይጸልይ ነበር፤ ሲነጋም ደቀ መዛሙርቱን እርሱ #ጠራቸው፤ ከውስጣቸውም ዐሥራ ሁለቱን #መረጠ፤ ሐዋርያትም ብሎ ሰየማቸው፡፡›› እንዲል ሉቃ.6፡12-13፡፡ ለተመረጡትና በሐዋርያነት ለተሰየሙት ደቀ መዛሙርት ሥልጣን እንዴት እንደ ተሰጠ ደግሞ ‹‹ጌታችን ኢየሱስም ዳግመኛ እንዲህ አላቸው ሰላም ለእናንተ ይሁን አብ እንደላከኝ እንዲሁ #እልካችኋለሁ፡፡ ይህንም ብሎ #እፍ_አለባቸው፤ እንዲህም አላቸው ‹መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፡፡ ኃጢኣታቸውን ይቅር ያላችሁላቸው ይሰረይላቸዋል፤ ይቅር ያላላችኋላቸው ግን አይሰረይላቸውም፡፡›› በሚል ሰፍሯል (ዮሐ.20፡210-23)፡፡ ሲመት፡- መመረጥን፣ ንፍሐትን፣ ተልእኮን እንደሚያካትት ከጥቅሶቹ እንረዳለን፡፡ ንፍሐቱ የጌታ ነው፤ እስትንፋሱ የእርሱ ነው፡፡ በሕየወታዊ ሕላዌያችን ከአዳም እንደ ተገኘን በክህነትም ከጌታ ተገኝተናል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ይናገራል፡- ‹‹ለአዳም የተሰጠ የሕይወት እስትንፋስ የሰው ልጅ ለመሆን በዘሩና በዘር ዘሩ ለልጅ ልጅ እንደ ፈሰሰ ሌላ የእውነት ምስክር አለኝ፡፡ ሌላ የሕይወት እትንፋስ (ከአዳም በቀር) የተቀበለ ምንም ማንም የለም፡፡ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ይቅር ላላችኋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል፤ ይቅር ላላችኋቸው አይቀርላቸውም ብሎ #እፍ_ባለባቸው_ጊዜ_ከጌታ_ከኢየሱስ_አፍ_የመንፈስ_ቅዱስ_መቀበል_ሆነ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ በኤጲስ ቆጶሳቱ ላይ በቀሳውስትም ላይ በክርስቲያን ታላላቆችም ላይ ቢሆን እፍ ያለበት ጊዜ የለም፡፡ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በደረሱበት ኤጲስቆጶሳትና ቀሳውስትን ዲያቆናትንም ይሾማሉ … ዲያቆን አድርገው #የሚሾሙትን_እፍ_ቢሉበት የዲቁና መንፈስ ይቀበላል፤ ለማጥመቅም እፍ ቢሉበት የክርስቲያን ታላቅ ለመሆን መንፈስን ይቀበላል፤ የኢየሱስ ክርስቶስም መንፈስ ወደ ወደዱት ሹመት #መዓርግ_ይተላለፍላቸዋል፡፡›› (መጽሐፈ ምሥጢር፣ ምዕ፣23፡28-29፣ ገጽ 242)፡፡ ‹‹ይተላለፍላቸዋል›› የሚለው ይሠመርበት! መተላለፉ የሚቋረጥ አይደለም፤ እስከ ሐሳዊ መሲሕ መምጣ ይቀጥላል እንጂ! አባ ጊዮርጊስ ይቀጥላል፡- ‹‹ከጌታ ኢየሱስ አፍ ለሐዋርያት የሆነ የመንፈስ ቅዱስ መቀበል እርሱ በፊት ላይ እፍ በማለት #ከአንዱ_ወደ_ሁለተኛው፣ #ከሁለተኛው_ወደ-ሦስተኛው፣ #ከዚያን_ጊዜ_ጀምሮ_እስካሁን_እስከ_ሐሳዊ_መሲሕም_መምጣት_ድረስ_የሚተላፍ_ሆነ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም ከደቀ መዛሙርቱ ሌላ ሁለተኛ እፍ እንዳላለ ዳሩ ግን (ቀድሞ) ከተሾሙት አፍ (አዲስ) ወደሚሾሙት #ያለመቋረጥና_ያለመከልከል_ይተላለፋል፡፡›› ይለናል ብሔራዊው ሊቅ (መጽ.ምሥጢር፣ ምዕ.23፡31፣ ገጽ 243)፡፡ ፍትሐ ነገሥቱም ‹‹ሊቃነ ጳጳሳት ግን የክርስቶስና እናንተን የተቀበለ እኔን መቀበሉ ነው ያላቸው #የሐዋርያት_ተከታዮች ናቸው፡፡›› (ፍትሐ ነገሥት፣ አንቀጽ 4፡39)፡፡ የሐዋርያዊ ክትትል ድንጋጌው ሥልጣነ ክህነቱን ከቅዱስ ጴጥሮስ የተቀበለው ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮምም ባኖርልን ትእዛዙ ምዕራፍ 8፡4 ከመምህሩ ተቀብሎ አስቀድሞ የነገረን ነውና የታመነ ነው፡፡
--

ቃለ ጸሐፍት
--
#ዐሥራት ገብረ ማርያም፡- ‹‹ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ነች የተባለው የሐዋርያትን ትውፊትና ትምህርት ስለምታስተምርና ይህንንም ለመጠበቅ እንዲቻል ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ተከታታይነቱ ያልተቋረጠ የካህናት አሹዋሹዋምን ሥርዓት ስለምትከተል ነው፡፡ … ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት የተባለችው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ከሐዋርያት ተቀብለው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የእርስዋን መመሪያ እንዲከተሉ ነው እንጂ መመሪያዎችን ችላ ብለው መረን እንዲለቀቁ አይደለም፡፡›› (ዐሥራት ገብረ ማርያም፣ ትምህርተ መለኮት፣ 1991 ዓ.ም.፣ ገጽ 203)፡፡
አቡነ #ሺኖዳ፡- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ‹‹Apostolic Succession and Laying of Hands - ሐዋርያዊ ክትትልና አንብሮተ ዕድ›› በሚል ርእስ በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለውናል፡- ‹‹It is clear that that God’s gift was passed on from Saint Paul to his disciple Timothy [2Tim.1:6]. Also Timothy passed on this to gift to others, by laying on of the Hands.
105 views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 17:14:41 ዛሬ ማታ 3:00.. ኢየሱስ አምላክ ነው.. ለሙስሊም ወንድም እህቶቻችሁ ሼር አድርጉላቸው

https://vm.tiktok.com/ZMFWnCHL8/
188 views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 07:31:44 በገና አባት የተሸፈነ ቅዱስ አባት

+++ቅዱስ ኒቆላዎስ ገባሬ መንክራት (St.Nicholas the wonder worker)+++

ቅዱስ ኒቆላዎስ (St.Nicholas-Santa Claus) በሮማ መንግስት ዘመን በኤዥያ ውስጥ በምትገኝ ሜራ በምትባል አገር (የአሁኗ ቱርክ) ግሪካዊ ከሆኑ ክርስቲያን ቤተሰቦቹ ተወለደ፡፡ የዚህም ቅዱስ እናቱ ጦና (Tona) አባቱ ኤጲፋንዮስ ይባላሉ፡፡ እኒህም እግዚአብሔርን የሚፈሩና ባለጠጎችም ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከሞቱ በኋላ ንብረታቸውን የሚያወርሱት፣ ለልባቸውም ደስታን የሚመግብ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ዕድሜያቸው እየገፋ በመምጣቱም ምክንያት በተስፋ መቁረጥ ተከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ያለ አምላክ በእርጅና ዘመናቸው ልክ ጻድቁ ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥን እንደጎበኘ እነርሱንም በቸርነቱ ጎበኛው፡፡ ቅዱስ የሆነም ልጅን ሰጣቸው፡፡ ይህም ልጅ ገና ታናሽ ሳለ መንፈሰ እግዚአብሔር የሞላበት ነበር፡፡ ዕድሜውም ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ዕውቀትና ጥበብን ይቀስም ዘንድ ወደ መምህራን የተላከ ቢሆንም፣ ከመምህሩ ከተማረው ይልቅ ከመንፈስ ቅዱስ የተረዳው ይበልጥ ነበር፡፡

መሠረታዊ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርቶች በልጅነቱ ተምሮ በማጠናቀቁ በዲቁና መዓርግ ተሾመ፡፡ በኋላም የአጎቱ ልጅ አበምኔት በሆነበት በአንዱ ገዳም አርዑተ ምንኩስናን (የምንኩስናን ቆብ) ጭኖ የቅድስና እና የትሕርምት ሕይወትን ኖሯል፡፡ በአሥራ ዘጠኝ ዓመቱም የቆሞስነትን መዓርግ አግኝቷል፡፡

ለዚህም ቅዱስ አባት እግዚአብሔር ተአምር እና ድንቅን የማድረግ ፤ሕሙማንንም የመፈወስ ታላቅ ጸጋ ሰጥቶታል፡፡

#ለጋስ (የስጦታ) አባት

በሜራ ከተማ የሚኖር ቀድሞ ባለጠጋ የነበረ በኋላ ግን ሃብት ንብረቱን ያጣ አንድ ሰው ነበረ፡፡ በድህነቱ ምክንያት ሊድራቸው ያልቻለ ሦስት ዕድሜያቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሰይጣንም እነዚህን ልጆቹን በዝሙት ሥራ ገንዘብ እየሰበሰቡ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ያደርጋቸው ዘንድ ክፉ ሐሳብን በሕሊናው አመጣበት፡፡ እግዚአብሔርም በዚህ ሰው ልቡና ውስጥ ሰይጣን የተከለበትን ክፉ ሐሳብ እና ምን ሊያደርግ እንደተነሣሣ ለቅዱስ ኒቆላዎስ ገለጠለት፡፡

ቅዱስ ኒቆላዎስም የእናት የአባቱ ገንዘብ ከሆነው ላይ መቶ ዲናር ወስዶ በስልቻ (sack) ጠቅልሎ ማንም ሳያየው በምሽት ወደዚያ ደሃ ሰው ቤት በመሄድ በመስኮት በኩል ወረወረለት፡፡ ያም ደሃ ከየት እንደመጣ ያላወቀውን 100 ዲናር በቤቱ ባገኘ ጊዜ ተደነቀ አምላኩንም አመሰገነ፡፡ ያሰበውንም ክፉ ሐሳብ ተወ። በገንዘብ እጦት ምክንያትም ከትዳር የዘገየችውን የመጀመሪያ ልጁን ዳረ፡፡ በሌላም ቀን ቅዱስ ኒቆላዎስ ሁለተኛ ልጁን መዳር ይችል ዘንድ፣ አሁንም ተጨማሪ መቶ ዲናር ገንዘብ በጥቅል ስልቻ አድርጎ በመስኮቱ በኩል ወረወረለት፡፡ ይህንንም ገንዘብ ዳግመኛ በቤቱ ያገኘው ደሃ ሰው እንዲህ ያለውን ቸርነት በስውር የሚያደርገው ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ አይቶ ያውቅ ዘንድ ጉጉት አደረበት፡፡ ቤቱንም በንቃት መከታተል ጀመረ፡፡

ቅዱስ ኒቆላዎስም እንደ ለመደው ለሦስተኛ ጊዜ መቶውን ዲናር የያዘውን ስልቻ በመስኮት ሲወረውር ወዲያው ተዘጋጅቶ ይጠብቀው የነበረው ሰው ፈጥኖ በሩጫ ከቤቱ ወጣ። ሊያየው ይመኘው የነበረ ያንንም ቸር ሰው ሊቀ ጳጳሱ ኒቆላዎስ ሆኖ አገኘው፡፡ ከእግሩ ስርም ተደፍቶ ልጆቹን ከድህነት እና ከኃጢአት ሕይወት ስለታደገለት ሊያመሰግነው ቢሞክርም ቅዱስ ኒቆላዎስ ግን ምስጋናውን እምቢ አለ፡፡ ይህን ሐሳብ በልቡ ያኖረ እግዚአብሔርንም ያመሰግን ዘንድ ለመነው፡፡

ከዚህ ታሪክ በተጨማሪም ለሕፃናት እና ለተቸገሩ ሰዎች ያደረገው ልግስና የብዙ ብዙ ነው። ለዚህም ይመስላል በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት መታሰቢያውን በልግስና የሚያከብሩት።

በአጠቃላይ ይህ ቅዱስ አባት በዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ስለ እምነቱ ብዙ ስቃይ እና እስራት ደርሶበታል፡፡ ፋታ በማይሰጥ መከራ እና ግርፋት ውስጥ እያለ የራሱን ሕመም ከማዳመጥ ይልቅ በውጪ ላሉ ለልጆቹ ምዕመናን የሚያበረታታ እና በእምነታቸው እንዲጸኑ የሚያደርግ መልእክትን ይጽፍላቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ኒቆላዎስ በ325 ዓ.ም ለአውግዞተ አርዮስ ከተበሰቡት 318ቱ ሊቃውንት መካከል አንዱ የነበረ የዚህች ኦርቶዶክሳዊት እምነት ባለውለታ ነው፡፡ ከአርባ ዓመታት በላይ በሊቀ ጵጵስና መንበር በጎቹን ከነጣቂ ተኩላ እየጠበቀ ቤተ ክርስቲያንን ካገለገለ በኋላ በሰማንያ ዓመቱ አርፏል፡፡

(ቅዱስ ኒቆላዎስ በእኛ (በኢትዮጽያ) የስንክሳር መጽሐፍ ላይ የእረፍቱ መታሰቢያ የሚያዝያ ወር በገባ በአስራ አምስተኛው ቀን እንደሆነ ተመዝግቧል፡፡ ኒቆላዎስም ማለት ‹መዋኤ ሕዝብ - ሕዝብን የሚያሸንፍ› ማለት ነው።)

የልደት በዓል እግዚአብሔር አብ ልጁን ለዓለም የሰጠበት በመሆኑ ‹የሥጦታ በዓል› በመባል ይጠራል፡፡ ይህንንም በማሰብ ለድሆች በመራራት ለተቸገሩት ቸርነት በማድረግ እናከብረው ዘንድ ምሳሌ እንዲሆነን ቅዱስ ኒቆላዎስን እናስባለን፡፡ ምንም ዓለም አፈ ታሪክ አድርጋ ብታወራውም፣ የዚህንም ቅዱስ ማንነት እንዳይታወቅ በፈጠረቻቸው ተረቶች ብታጠለሸውም እኛ ግን የ‹ገና አባት› ብላ ከሰየመቻቸው የፈጠራ ሰው ጀርባ እውነተኛ የሆነውን ይህን ቅዱስ አባት እናስበዋለን፡፡

+++++ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛ ኃጢአተኞቹንም በዚህ ጻድቅ ሰው ጸሎት ይማረን!!!+++

ምንጭ:– -መጽሐፈ ስንክሳር
-Coptic synaxarium

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
selam@dnabel.com
228 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 06:58:47
#የበረከት_ሥራ

የኤፍራታ(አረቋቴ) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድነት ገዳም (ራያ ቆቦ)
#ገድለ_ቅዱስ_ቂርቆስ_ሕፃን_ወእሙ_ቅድስት_ኢየሉጣ በግእዝ እና አማርኛ አሳትመው በጦርነቱ ምክንያት ሳይሰራጭ ቆይተዋል።ለበረከት 250ኮፒ ልከውልናል።
#ዋጋው_450ብር ነው።በጾም ወቅት ለገዳማት፤ጉባዔ ቤቶች መጽሓፍ ግዙ እያልኩ ሳስቸግራችሁ ነበር።አሁን ግን ለራሳችሁ ግዙ ስትገዙግን የገዳሙ በረከት ታገኛላችሁ።በግል፤በማኅበር መግዛት ይቻላል።የገዳሙ አበምኔት ቆሞስ አባ ለአከማርያም መጽሓፉ ወደ መደብራችን ይዘው ሲመጡ።አባ የግለሰብ እና የነጋዴ ዋጋ ያውጡለት ስላቸው።ለግለሰብ 500ብር ለነጋዴ 450ብር አሉኝ።ልጄ በውድ አሳትመነው በጦርነቱ ምክንያት ይዘነው ቁጭብለን ነው ሲሉኝ።በልቤ የወሰንኩት #ለኅብረቱ_አባላትም_ለነጋዴም_450ብር ብቻ እንውሰድ።በግል ለምትፈልጉ @orthokiha እዘዙኝ።በብዛት ምትፈልጉ ወንድሜ ፍቃዱ ኃይሌ
+251930368109 ደውሉለት።
እስከ ነገ ማታ 250ሰው እፈልጋለሁ።መግዛት አቅሙ የሌላችሁ ሼር በማድረግ አግዙኝ።
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_በ0986025463_0966214181_ይደውሉ!!
224 views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 06:48:32 እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል በአል በሰላም አጀረሳቹ

ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ዳንኤል(10:13)
የሚያጽናናኝ ሚካኤል ነው ዳንኤል(10:21)
ስለኛ የሚቆመው ሚካኤል ዳንኤል(12:1)
የመላዕክት አለቃ ሚካኤል ይሁዳ(1:9)
235 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 06:31:13 “እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።”

— ኢሳይያስ 30፥18
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”

— ኢሳይያስ 40፥31
“በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና።”
— መዝሙር 4፥8

https://t.me/Tmhrte_Tewahdo
238 views03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ