Get Mystery Box with random crypto!

በቅጡ መግደል ኤልያስ ሽታኹን * * * * | ግጥም እና የ Jo ደብዳቤዎች

በቅጡ መግደል
ኤልያስ ሽታኹን
* * * * *
የተዘለለ ዕድሜ
የሰው ሰው ካድሜ
ያሰብኩት ላይቀናኝ
ገዳም ያጣ መናኝ...
ዓለም ሰው ቢቀማው
ልብ አረፈ አሉ እቅፍ እንደጠማው፡፡
የሰው ቃል አይገድለው
የሰው ልብ አይችለው
የለም ሆኖ እንጂ
መሞቻም ባጣሁኝ እኔማ እንዳንቺ፡፡
ከፈረሰው ከገላዬ
ከመቃብር ከኋላዬ
የቆምሽው ከገደል
ይነሳል ብለሽ ነው? ልብ "ኢየሱስ" አይደል?
እመኚና ኑሪ ያውም ተደላድለሽ
ምን እንቅልፍ አሳጣሽ? በቅጡ ከገደልሽ፡፡


።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel