Get Mystery Box with random crypto!

ምስክርነት =ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም! /ሠላም ዮሐንስ ምስ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ገዳም ሚዲያ ፨ ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ የገዳሙ ሶሻል ሚዲያ Johnny aleme

ምስክርነት =ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም!
/ሠላም ዮሐንስ ምስክርነት
1. ለሊት ለጸሎት እንዲያነቁኝ እና ካነቁኝ እንደምመሰክር ቃል ገብቼ ጠይቂያቸው ፈቃዳቸው ሆኖ ባልኳቸው ሰዓት አንቅተውኛል
2. በህልሜ ደሞ እየረበሸ የሚያስጨንቀኝ ነገር አለ እና እሱን እንዲያርቁልኝ ጠይቂያቸው በሰላም አሳድረውኛል ጻድቁን አመስግኑልኝ
አምላከ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ይክበር ይመስገን
ጻድቁም ስማቸው የተመሰገነ ይሁን

/Selam jhonny wendeme abatachen kidus abune echege yohannes yaregulegnen lememesiker new... Lelit lay betam kebad wugat dereten yezogne metenifes akitogne abatachenen eyetematseniku melikachewun derete lay asikemiche ena betsebelachewu tedabeshe ahun betam teshelognale kibir misgana tsadikun leseten egziyabeher ,kibir misgana lenatachen lekidist dingel mariyam ... Hulem yetsadiku tibeka ayeleyen

/በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈሰ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ለዚች ቀን ለዚች ሰዓት ያደረስከን አምላካችን መድሀኒዓለም ክብር ምስጋና ይግባህ እመቤቴ ወላዲተ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባሻ የሆስፒታል ቀጠሮ ነበረኝ ስደርስ ረፎዷል አሉኝ በጣም ደነገጥኩ አብነ እጨጌን ጠራሁ ቅድስ ዑራኤል ቀን ነዉ እባካችሁ እርድኝ አልኳቸዉ እመሰክራለሁ አልኩ አስተካከሉልኝ ሌላዉ ደም ለመስጠት በጣም እቸገር ነበር ሁልጊዜ ቅድስ ዑራኤል እያልኩ በአንድ ጊዜ ተገኘልኝ እናቴ እመቤት ሁሉን ነገር አስተካክላ አብነ እጨጌ ሁሉን እደሚያስተካኩልኝ እየጠበኩ ነዉ እግዚአብሔር ይመስገን ለፍሬ በቅቼ የምመሰክር ያድርገኝ ወስበሀት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር ፍቅርተ መድህን እባላለሁ !!

/ጆኒ እንደምን አለህ ምስክርነት ለመስጠት ነው 1 ሰው ጋራ የነበረኝን ገንዘብ በእጄ አስገብተውልኛል 2 በጣም ተናድጄ ነበረ አረጋግተውኛል 3 የለመንኳቸው ነገር ነበረ ፍንጭ ሰጥተውኛል 4 ከሰዎች ጋራ የነበረኝን ግንኙነት አስተካክለውልኛል ጭንቀቴንም አስወግደውልኛል የነለያዩ ነገሮችንም አስተካክለውልኛል እልልል ብላችሁ አመስግኑልኝ

/በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
ወንድሜ የአባታችንን ተአምር ለመመስከር ነው
1.ባለፈው ልጄን መጥፎ ሳል አሞት ነበር ለአባቴ ነግሬያቸው ሳሉን አቆሙለት ደጃቸው ስመጣ ብመሰክር ይሻላል ብዬ ስተወው ልጄን በጣም አመመው:: አባቴ ይቅር ይበሉኝ አሁንም ይማሩልኝ
2. ባለፈው የማይሆን ግብር ጠይቀውኝ ለአባቴ ነግሬያቸው በሰላም ጨረሱልኝ :: አባታችንን እና እሳቸውን የሰጠንን አምላክ ይክበር ይመስገን::

/ሰላም ጆን ልጄ 13 አመት ናት እናም እናቴ ምስክርነት ንገሪልኝ ብላኝ ነው የአባቴን ምስል ሰጥችያት በፈተና ሰአት ይዛ ሄዳ ነበር ከጠበቀችው በላይ ውጤት አምጥታልች ክብር ምሰጋና ለአባቴ ትላንት ደግሞ ለሊት ላይ ጆሮዋን አሞት በምስላቸው ደባብሻት ተሽላታል እኔም በአለፈው ሳምንት ትንሽ እሚያስጨንቅ ነገር ገጥሞኝ አባቴ በመጠኑ ቀርፈውልኛል ጨርሰው እንደሚገላግልኝ አምናለሁ መጥቼ እመሰክራለሁክ ክብር ምስጋና አባቴን ለሰጠን እግዚአብሔር አሜን ከዚህ በተረፈ ተደርጉልኝ ያልመሰከርኩት ካለ አባቴ ይቅር ይበሉኝ ምክንያቱም በትንሽ በትልቁ አባቴ ከአፌ አይጠፉም አሜን

/Misker lemestet neber tsadeku endet nh tsadeku buze neger aregolegnal seraye tena balemoya negne meserabet hospital ye nerve tama neber huletu egerwa ena huletu ejewa paralize neber menkesakes atechelem keza kegna wede lela hospital yemetenfesha tebo endegebalat telakeche ene ye abune echege yohanes tsebel emnet setehat tsadeku erdugne abate adenewat beye tseleyku keza tsebelu emnetu atetechat kebachat wedeyaw daneche meramedem chaleche yemetenfesha tebom kere keber le abatachen yedengel leje le dingel maryam esachewen yeseten amelak kibru yesfa chereso yemarewat

/ሰላም ጆን መስክርነቴን አድርስልኝ 1ባለቤቴን በ 21 ከሰአት በኋላ አሞት ማታም አሞት ሌሊቱን ሽንት ቤት ሲመላለስ አደረ ጠዋት ተነስ ስለዉ ደክሞኛል ስራ አልገባም አለኝ ጠዋት በብርጭቆ ፀበል ቀድቼ እንዲጣ ነግሬዉ ስራ ሄድኩ።ከዛ ስደውል ተሽሎኝ ወደ ስራ እየሄድኩ ነዉ አለኝ ።2 tvያችን ከተበላሸ ቆየ እና የአቡነ እጨጌን ፀበል በእጄ ነክቼ አሸት አሸት አደረኩት እና በአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ፀበል ነው ደና የሆነልኝ አመስግኑልኝ ፣አምላከ የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ አምላክ ይመስገን፣ወለዲተ አምላክን አመስግኑልኝ።

/ሰላም ጆኒ እንዴት ነህ?ስለ እቡነ እጨጌ ልመሰክር ነበር ብር አስፈልጎኝ ባለቤቴን እንድሊክልኝ ልቡን አራሩልኝ ብዬ እልክልሻለው ብሎኛል ክብር ምስጋና ለአባቴ አቡነ እጨጌ ሁሌ ስጠራቸው ለማይሰለቹኝ

/ሰላም ጆኒ እንዴት ሰነበትክ ብዙ ግዜ መስህሪያለሁ ዛሬም ልመሰክር ነው የአባታችንን ተራዳኢነት፣ ብዙ ግዜ ቶንሲል ያስቸግረኛል ሲያመኝ ደግሞ ገሎ ነው የሚያነሳኝ ላባታችን ነግሬያቸው ለረጅም ግዜ ትቶኝ ነበር ሳልመሰክር በመቅረቴ ግን ሰሞኑን በጣም አሞኝ አቅም እጥቼ ነበር ትናንት ማታ በገድላቸው ተሻሽቼ አባቴ ይቅር በሉኝ ማሩኝ ብዬ ዛሬ ሰላም ውያለሁ ሌላው ደግሞ በሰላም መለያየት የምፈልጋቸው ሰዎች ነበሩ አርቀውኛል ክብርን ምስጋና ይግባቸው ያስጨነቀኝ ጉዳይ ገድላቸውን አንብቤ ቀለል ብሎኛል ፍፃሜው እንዲያሳምሩልኝ በፀሎታችሁ ወለተሀና ብላችሁ አስቡኝ

/Selam yohannes zarem abate abune echege yohannes ze tsegeron yelemenkuachew neger neber misgana yidresachew asakitewuligal yemiserawun sira barkulig tru adrigulig biye lemenkuachew ye amlaken sim teriche ye emebeten sim teriche ye semaitun giyorgis sim teriche yeserahut melkam tru honoligal kibir ena misgana le leul egziabher kibir ena misgana le emebetachin dingil mariyam kibir ena misgana le hulum kidusan melaikt kibir ena misgana le hulum tsadikan semaitat yihun.Amen