Get Mystery Box with random crypto!

bikebdegnim tmhrten endakuart aderegugn enem keza fetena amele | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ገዳም ሚዲያ ፨ ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ የገዳሙ ሶሻል ሚዲያ Johnny aleme

bikebdegnim tmhrten endakuart aderegugn enem keza fetena ameletku beseatu negeroch bikebdugnim yehonew hulu yalesu fkad yehone yelemna sletederegelgn neger fetarin amesgnulgn

=ጆኒዬ ፡ እንደምን ፡ አለህ ፡ የአባቴን ፡ ምስክርነት ፡ መስጠት ፡ ፈልጌ ፡ ነበር ፡ ትላንትና ፡ ልጄን ፡ ሀይለኛ ፡ ሳል ፡ አመመብኝ ፡ እና ፡ ተጨንቄ ፡ ነበር ፡ ማታ ፡ ስትተኛ ፡ እንዲምሩልኝ ፡ በሰላም ፡ እንድታድር ፡ ተማፀንኩኝ ፡ በሰላም ፡ አድራ ፡ ዉሎአም ፡ በሰላም ፡ ዉላልኛለች ፡ አምላከ ፡ አቡነ ፡ እጨጌ ፡ ይመስገን ፡ እኔም ፡ ጨጓራዬ ፡ ያስቸግረኛል ፡ አባታን ፡ ለምኜ ፡ በሰላም ፡ አድሬአለሁ ፡ ተመስገን ፡ ፃድቁን ፡ አመስግኑልአኝ

=+++~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ~+++
ጉዞ ህዳር3/4 እና የጻድቁ ልደታቸው ንግስ ህዳር 29-(28/29)
ገዳሙ ጉዞ አዘጋጅቷል ሰሜንሸዋ መንዝ+++++(መዘዞ)አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+++ህዳር 3/4 እና ልደታቸው ህዳር 29 -(28/29) ጉዞ ተዘጋጅቷል።
መነሻ፦ህዳር3ቅዳሜ
መመለሻ፦ህዳር 4ተባርከን መመለስ።
ለበለጠ መረጃ፦
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969
በጻድቁ አባታችን መስቀላቸውና መቋሚያቸው ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ!አሜን!!!!

+++++ምዕራፈ ቅዱሳን /አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ/++++በኢትዮጵያ በስማቸው ያላ ብቸኛ ገዳም መስቀላቸውና መቋሚያቸውና ገድላቸው የሚገኛበት፤ጥንታዊ ጻድቁ የመሰረቱት መንዝናይፋት መዘዞ { /መዘዞ/አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ(ዘጸገሮ)} 9በዓት ጸልየዋል፦
ያነበበብ አሜን ይበል!።
ጠገሮ ፃድቅ የአባ አቡነ እጨጌ ዩሐንስ ዘጸገሮ፦....... አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል የካቲት 28 ተፀንሰው በወራሀ ህዳር 28 ለ29 ሌሊት ተወለዱ (ህዳር29) ተወለዱ ፣የአባታቸው ስም ዲላሶር ሲባል የእናታቸው ስም ደግሞ እምነ ፅዩን ይባላል። ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ፃድቃኖች ናቸው ፃድቁ አባታችን ገና በአምስት አመታቸው ሳሉ
ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው ሲሄዱ ፍቅሩ ወልዳ ስለ ማርያም ተመልክተው መሳቅ ጀመሩ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከምስሉ ወጥታ በምን
አውቀህኝ ነው ብላ አቅፋ ሳመችሁ ከእንግዲ በኃላ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላዕክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ትኖራለህ ብላ ባርካው ተሰወረች። ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኃላ በደመና ተጭኖ በመላዕኩ ቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
መጡ። ፃድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለው ለ50 ዓመት በፆምና ፀሎት በተጋደሉ ቆይተዋል። አባ ዩሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል
አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ። ይህ ገዳማቸው የሚገኘው በሰሜን ሸዋ በመንዝናይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር 1 ሰዓት ከተጓዙ በኃላ የሚገኝ ሲሆን
አስደናቂ የፃድቁ የእጬጌ ዩሐንስ ገዳም ነው።አባታችን ተጋድሏቸው ሳሉ ሰዎች በክፋት ተነሱባቸው ሰይጣን በእነርሱ አድሯልና እንዴት እንደሚያጠፋቸው ይማከሩ ጀመር ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ
የታወቀ ነውና ፈሩ ለምን ከምንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን በሐሰት እንክሰሳቸው ብለው ወርቅና ብር ለሴቷ ሰጥተው በአሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትናገር አደረጎት አባታችንን በሕዝብ ፊት በአሰት ተከሰሱ ፃድቁም አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው አሏት እርሷም አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ አለችሁ አባታችንም አዝነው በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ ሲሉ ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች የአገሩ ሰዎች ፈሩ ፃድቁም ምድሯን እረገሟት የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ የተተከለው አይፅደቅ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ ብለው ረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሄዱ። አባ ዩሐንስ በመላው ኢትዮጰያ ዞረው ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሳ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት በጨረቃ ላይ 50 ዓመት በደመና ላይ 50 እንዲሁም አለም በክንፎ በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ አባትም ናቸው ከሰው ተወልደው ከመላዕክት ተደምረዋልና በይፋት ጠገሮባለወልድ ፣በአፋር አዘሎ፣በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣በደብረ ሊባኖስ፣ በጉንደ ተክለሃይማኖት፤ሳፈጅ ዮሐንስ ብልጋ፤አለም በመዘር እና በሌሎችም ስፍራ በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ በፆምና ፀሎት ቆይተዋል።ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሄደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በፀለዩበት ባሕር በፀበላቸው ይጠመቃል በተጨማሪም ይዞሀት በነበረው መቋሚያ ጀርባችንን እንዳበስበታለን ማየት ማመን ነውና ከምስሉ ተመልከቱ መጥታችሁ ገደሙን ማየት ነው ። ቆመው
ከፀለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል በገዳማቸው አባ ዩሐንስ 500ዓመት ከኖሩ በኃላ እረፍተ ዘመናቸው ደረሰ መዳኒዓለምም ከ15 ነቢያት ከ12 ሐዋሪያት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ከአርባ አራት ሺው ሕፃናትን አብርሃም ይሳዕቅ፤ያዕቆብን ሁሉንም ነገደ መላዕክትን፤ነበያት፤ሃዋርያትን፤ ጻድቃን፤ ሰማዕታትን አስከትሎ መጣ ለአባ ዩሐንስ ቃልኪዳን ሰጣቸው ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣መባ የሰጠ፣ቤተክርስትያንህን የሰራ ያሰራ የረዳ፣ገድልን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ መታሰቢያን ያደረገ፣ እስከ10 ትውልድ እምርልሀለው ንስሀ ሳይገባ አይሞትም ልጅ መውለድ ባይችል ማህን ቢሆን እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ የክርስትያን ማደርያ በሆነች ገነት(ደብረ ፂዮን)በብርሃን ቦታ አስቀምጠዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው ገድላቸው በጥቂቱ ነው እንዲሁም ገድልህን በቤትህ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ አይነካውም፣ክፉ አጋንት አይነካውም፣ቸነፈርና ወባ አይነካውም፣መላኢከ ጽልመት አይነካውም።በገዳምህ መነኩሴ ቢቀበር በሰማይ
ክንፍ አበቅልለታለሁ፣አይሁድም አረማዊም ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልለሃለሁ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ።
የነገርኳችሁ ከዚህ በኃላ ወደ ሰማይ አረገ አባ ዩሐንስ ሐምሌ 29 ቀን አረፉ። በጉንደ ተክለሃይማኖትም ተቀበሩ 157ዓመት በኃላ አንድ የበቁ ባሕታዊ ወደ መንዝ ሄደው የረገሟት መሬት እንድትቀደስ የተዘራው እንዲበቅል ከስውራን አባቶች ጋር በመሆን ግማሽ አፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አውጥተው አርባሐራ መዳኒዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ አፅሙ አረፈ ምድሪቷም ተባረከች የዘሩትንም አበቀለች ውርጩም
ብርዱም ቀነሰ ዝናብ አልዘንብ ሲል ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምዕላ ይያዛል ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል ዝናብም ይዘንባል። ፀበላቸው ሽባ ይተረትራል ድውይ ፈዋሽ ከሰማይ የወረደላቸው መስቀልም ታምር ሰሪ ከባሕራቸው ደረቅ አሸዋ የሚወጣበት የጠገሮ ፃድቁ እጬጌ ዩሐንስ በረከት
ይደርብን አሜን!!!