Get Mystery Box with random crypto!

ምስክርነት +share share ------ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ገዳም ሚዲያ ፨ ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ የገዳሙ ሶሻል ሚዲያ Johnny aleme

ምስክርነት +share share
------ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም!
=ሰላም እንዴት ነህ ጆን ወንድሜ
ስለ አባትችን አቡነ እጨጌ ዩሀንስ ዘፀግሮ ልመሰክር ነበር ትላንትና ጥዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ሁለቱንም እግሬ ከ ጉልበቴ ጀምሮ ቁርጥማት ያዘኝ እና ሰውነቴን ደግሞ የህመም ስሜት ተሰማኝ እና የ አባታችን መልካቸውን መፅሐፍ አንስቸ አሻሸውት ከተሻለኝ እመሰክራለው ብየ ነበረ ተሻለኝ ወዲያውኑ ሳይታወቀኝ ተሻለኝ እግዚአብሔር አምላክ ይመስገን እሳቸውን የሰጠን ድጋሜ ለመመስከር ያብቃኝ አሜን

=Selam joni tinantna lijen amobign neber ena lelit layi demo tikusati betam chemro amobgn neber keza enate digl maryamn medaniyalemn silasewochn ena abune echegen besiele adinachew dabishe tikusatun kensewu besela kasaderulgn emesekralewu biye tikusatu kensolet tegnitolgn adiral sile hulum neger egzaber yimesgen ahunm cherisew yimarulegn

=ሠላም ጆ አንዴት ነህ አቡነ አጨጌ ያደረጉልኝል ልመሠክረ ነው እኔና እህቴ አሜሪካ ሆና የአቡነ እጨጌን ፀበል ጓደኛዋ ይዛ ሰጨኝ ሰትላት ድዊ የያዘው ሠው ሰላለ ላንቺ አልሠጥም ጠለቻት እህቴም አዝና አባቴ ለደጆትአድከሱኝ በላ ጠለች አኔም በሱዋ ሰበብ ደጃቸው ደረሰን በአጋጣሚ መሥቀሉ የሚወጣ ቀን ነበረ ፀበል ተጠምቀን መሥቀል ተዳሰሰን ቸመለሥን ከዚያ ሰንመለሥ አክሰታችን ካንሰር ታማ ነበርና የአቡነጨጌን ፀበል ሠጠናት በትንሸ ጨንቀትና ጣር ከዚህ አለም ተለይታለች ይሄን ምሰክረሰነት ለመሥጠት ነው ሰላም ሁንልኝ

=ሠላም ጆ እንዴት ነህ ሠላም ነህ ወይ ወንድሜ አሜሪካ ነው ያለው እና ሸንቱ ደም መቀላቀል ጀመረበት ከዚያ ኦፕራሲዬን ሆ 1ወር ሆነው እና አጢው ወጥቶ ሲመረመረ ማወቅ አልቻልንም ብለው ሌላ በታ ተላከ ምርመራው ሲመጣ ካንሰር ሆነ እና አኔም ወጤቱ ከመምጣቱ በፊት አባቴ አረድኝ ሠላም አረጉልኝ ወንድሜን ብዬ ፀሎት አድረጌ ተሳልኩ ውጤቱ መጣ ግን ወንድሜን ምነም ነገር አልደረሰበትም ገና አራሡን እጢውን ብቻ ነው የተበላሸው ከጭንቅ ሥላወጡ አኔም በራሴ ችግሬ ተቀርፎልኝ ለመመሥከር ያብቃኝ መሥክርልኝ አደራ ሰላም ሁን

=ሰላም ዮሐንስ የአባታችን የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ምስክርነት ለመስጠት ነው።ባለቤቴ አሞኛል ሲለኝ ለክፉ እንዳይሰጠው እኔም እጄን አሞኝ ነበር በፀሎት መፅሀፍ በአባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መልክዐ ፀሎት መፅሀፍ እና በእምነት እየተደባበስኩኝ ጨርሶ እንዲሻለኝ የስራ ወረቀት የት እንዳደረኩት ጠፍቶብኝ እንዳገኘው መድሃኔዓለምን እመብርሃንን መላዕክትን ሰማዕታትን ፃድቃንን አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስን ለምኛቸው ነበር።ባለቤቴም ሰላም ሆኗል እኔም እጄን ሙሉ ለሙሉ ተሽሎኛል የጠፋብኝን ወረቀትም እቤት አስቀምጨው አግቼዋለው። መድሃኔዓለም ይክበር ይመስገን።እመብርሃን ክብር ምስጋና ይድረሳት።ቅዱሳን መላዕክት ክብር ምስጋና ይድረሳቸው።ቅዱሳን ሰማዕታት ክብር ምስጋና ይድረሳቸው።ቅዱሳን ፃድቃን ክብር ምስጋና ይድረሳቸው።ፃድቁ አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ክብር ምስጋና ይድረሳቸው።አሜን

=ሰላም ጆኒ አባቴ አቡነ እጨጌ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነው መስከረም ወር ላይ ለልጄ የልደት ሰርተፍኬት ለማውጣት ቀበሌ ሄጄ ከፍርድ ቤት የሚመጣ ወረቀት አለ ይዘሽ ነይ ስባል አባቴ እርሶ እርዱኝ ብዬ ስልኬ ላይ ያለውን ስእለአድኖአቸውን ስስመው ወድያው ተይው አያስፈልግም ብለው ሳልንገላታ አውጥቻለው ።አባቴ ብዙ ነገር አድርገውልኛል አስታውሼ ለመመስከር ያብቁኝ

=በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!! የእግዚያብሄር ቸርነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን!!! እነሆ ቅዱስ አባታችንን ደግሜ ደጋግሜ ያማልዱኝ ብዬ ለምኛቸዉ ያደረጉልኝን ምስክርነት ልሰጥ ነዉ :: ማታ ጨጎራየን አሞኝ ነበረ አባቴን የአቡነ እጨጌ ዩሃንስን ምስል ይዤ ለምኛቻዉ ነበር አባቴም አላሳፈሩኝ ምህረቱን ልከዉልኝ ቢሮ ገብቻለሁ አመስግኑልኝ!!!እኝህን አባት የሰጠን ፈጣሪ ስሙ የተመሰገነ ይሁን!!! የእኔን ልመና እንደሰሙ የእናንተንም ፀሎት እና ልመና ይስሟችሁ። በህይወቴ የምጨነቅበት ትልቅ ጉዳይ አለኝ የልቤን ጻድቁ አባታችን ያዉቃሉ ተሳክቶልኝ ለዳግም ምስክርነት ያብቁኝ አሜን!!!!

=አቡነ እጨጌ ዮሀንስ ያደረጉልኝ ብዙ ነው የኔ ፈጥኖ ደራሥ አባት ክብር ስማቸው ይሁን ለምስክርነታቸው ስላበቁን

1. መኪና ልምምድ ነበረኝ እና አቡነ እጨጌ ዮሀንስ የጸሎት መጽሀፍ ደረቴ ውስጥ አድርጌ ልምምዴን ጨርሼ ታከሲ ውስጥ ስገባ አን ከጎኔ የተቀመጠ ሰው እራሴን አሞኛል በጣም ግን ሳይሽ ል ደነገጠ አለኝ ከዛም እያወራን ከባለቤቴ ጋር በ7 አመታችን ልጅ ውልደን አሁን 7 ቀኑ ነው እና ጭንቅላቱ ውስጥ ደም ፈሶ ተስፋ የለውም ብለውን ሆስፒታል ነው ያለቺው አልቅሳ ልተሞት ነው ብሎ ነገረገኝ፡፡ ከዛም እኔ ስለ አቡነ እጨጌ ነግረኩት .እሱ ደሞ ኦርቶዶክስ ነኝ ግን በሳይንሱ ነው የማምነው አለኝ. ኤኔም በቃ እኔ እነግራቸዋለሁ አንተም ልጁ ያለበትን ትነግረኛለክ ብይ ስልክ ተቀያረን ውረድኩንኝ ከሳምንት ባዋላ ስጠይቀው 15 % ተስፋ አለው ብለዋል ዶክተሮ አለኝ መልሼ ከ15 ቀን በኻላ ጠየኩት 75 % ተስፋ አለው ብለዋል ዶክተሮቹ አለኝ . ከ ሳምንት በሓላ ደውለኩለት ጡት መጥባት ጀምረ አለኝአቡነ እጨጌ ዮሀንስ አባቴ ምንም ሳያሳፍሩጘን የኔ አባት ልጁን አድውነታል ክብር ምስጋና ለስማቸው ይሁን . ልምታውቁትም ለማታውቁትም ታምራቸውን ንገሩ .በዚ ሀጢያታችን በበዛበት ዘመን እሳቸውን የሰጠን እግዚበሄር ይመስገን
2. ባለቤቴን ብዙ ጊዜ ጨገራውን ያመዋል . አሁን ጸበላቸውን እየጠጣ በጠም ተሽሎታል ጨርሰው ይማሩት ደጃቸውንም እንዲረግጥ በጣም እፈልግ ነበር ደጃቸውን አረግጦ መተል
3. ልጆቼ ብዙ ጊዜ አሞብኝ አቡነ እጨጌ ዮሀንስ የጸሎጽ መፅኀፋቸን አሻሽቻቸው ድነውልኛል . እግዚብኄር ይመስገን .
4. ባለቤቴን ስራ ያስቸግረው ነበር ለእጨጌ ከነገርከዋቸው በሓላ አሁን እግዚበሄር ይመስገን ብዙ ነገር እየተስተካከለለት ነው በመዘንጋት ያልመሰከርኩት ካለ አባቴ እጨጌ ይቅር ይበሉኝ

=Selam Jhonny endet neh
Abate yaderegulignin lememesker new lesira ke Hager wuchi new yalehut ena sira bota chinket neberebign Hulu neger endasebkut alihonem ena abaten lemenkuachew esachewin alasaferugnim testekakilolignal. Mechereshawim bedil hono endimeles yirdugn amen.

=ሰላም ጆኒ እንዴት ነህ ፃዲቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ያረጉልኝን ለመመስከር ነበር ለሊት ላይ ሆዴን በጣም ያቃጥለኛል እና በስዕል አድኗቸው ሆዴን አሽቸ የገብርኤልን ፀበል ጠጥቼ ድኛለሁ ክብር ምስጋና ይድረሳችው

=ሰላም ወንድሜ እንዴት ነህ የምሰራው ስራ ዲዛይን አልመጣ ብሎኝ አባቴን ጠርቻቸው ተስተካክሎልኛል መስክርልኝ